የባለራእይ ወጣቶች የህዝብ ግንኙት ሀላፊ ከእስር ተለቀቀ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ግንቦት14፣ 2005 ዓም በደህንነቶች ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ በማእከላዊ እስር ቤት ያለ ፍርድ ሲሰቃይ የነበረው የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ በ5 ሺ ብር ዋስ ከእስር መፈታቱ ታውቋል።

ወጣት ብርሀኑ ግንቦት27 ለ3ኛ ጊዜ ሜክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ክስ ለመመስረት ባለመቻሉ ቀጠሮ ተጠይቆበት እንደገና ወደ እስር እንዲመለስ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

ፍርድ ቤት በቀረረበት ወቅት ዳኛው ፖሊስ በ ወጣት ብርሀኑ ላይ ክስ መመስረት ካልቻለ በ 2 ቀናት ውስጥ  ክሱን እንደሚዘጉት መናገራቸው ይታወሳል።