ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሁሉም ጣቢያዎቹ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሠራተኞችን ከስራ ማባረሩን ለማወቅ ተችሎአል፡፡ ድርጅቱ ሰራተኞችን ከሰኔ 17 ጀምሮ ያሰናበተ ሲሆን፣ ሰራተኞች አስቀድሞ ያልተነገራቸው በመሆኑና ያለአንዳች ካሳ በመባረራቸው ለከፍተኛ የኢኮኖሚና የስነልቦና ችግር ተዳርገዋል። ድርጅቱ በሁመራ በቡሬ እና ከ100 በላይ በሚሆኑ ሌሎች ጣቢያዎች የሚገኙ ሰራተኞችም ማበረሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የድርጅቱ ሰራተኞች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሞጆዎች በውሀ ተጠማን አሉ
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በከተማዋ ውሀ ከጠፋ 20 ቀናት አልፈዋል። በአብዛኛው የከተማ ክፍል ውሀ አለመኖሩን ነው ነዋሪዎች የሚናገሩት በጉዳዩ ዙሪያ የሞጆ ከተማ ባለስልጣናትን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በአዲስ አበባም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች የውሀ እጥረት መከሰቱን መዘገባችን ይታወቃል።
Read More »ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ጉብኝታቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ተጠየቁ
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ዛሬ በሚጀምሩት የሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካና ታንዛኒያ ጉብኝት በችግር ተዘፍቀው የሚገኙትን የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሀንንና የሰአብአዊ መብቶች ተሟጋቾችን እንዲደግፉ ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል። በአፍሪካ መገናኛ ብዙሀንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሚያደርጉባቸው ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋልና ታንዛኒያ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ እና በፕሬስ ነጻነት ዙሪያ የተሻለ ሁኔታ ቢኖርም በሌሎች የአፍሪካ ...
Read More »የደኅንነት ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለሚወስዱት ዕርምጃ በሕግ አይጠየቁም ተባለ
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተቋምን በሚኒስቴር ደረጃ እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ የደኅንነት ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለሚወስዱት ዕርምጃ በሕግ እንደማይቀጡ ተመለክቷል። ሪፖርተር እንደዘገባው ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በ1987 ዓ.ም. በወጣ አዋጅ የተቋቋመ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ በርካታ አገራዊ፣ አካባቢያዊ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ለውጦች መታየታቸውና እነዚህ ለውጦች በኢትዮጵያ ደኅንነት ላይ ያላቸውን ፋይዳ ባገናዘበ ...
Read More »አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙ
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምእራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማና አካባቢዋ ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጁን 23 ቀን 2013 ባደረጉት ልዩ ዝግጅት ታዋቂውን የነፃነት ተፋላሚና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ገብረመድህን አርአያን የዘመናችን አሉላ አባ ነጋ በማለት በክብር ሰየሙዋቸው። በዚህ ለእርሳቸው ታስቦ በተደረገው ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ እንግዶቹ ለአቶ ገብረመድህን አርአያ ...
Read More »በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። – እማኞች እንደሚሉት ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ ...
Read More »የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ስራ የሚ ለቁ ዳኞች ቁጥር መጨመሩን ተናገሩ
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ኔታነህ ሰሞኑን ለፓርላማ የመ/ቤታቸውን የ11 ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ዳኞች በርካታ ችግሮች የተጋረጠባቸው በመሆኑ መስሪያቤቱን እየለቀቁ ነው ብለዋል። የዳኞች መኖሪያ ቤት ችግርን በዘለቄታነት ለመፍታት ሕንጻ ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት የተወሰነ መጓተት እንደሚታይበት ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው እስከዚያ ድረስ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ መንግስት የኪራይ ቤት መስጠቱን እንዲቀጥል የተላለፈውን ...
Read More »የግብርና ኢንቨስትመንትን የሚመራ ኤጀንሲ በመቋቋም ላይ ነው
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጽያ መንግስት የግብርናውን ኢንቨስትመንት የሚያደራጅና የሚመራ የግብርና መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ በማቋቋም ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡ አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ በመንግስት በኩል የግብርናን ኢንቨስትመንት በማጠናከር ሰፋፊ የግብርና ልማቶች በአገሪቱ እንዲኖሩ መንግስት ፍላጎት እንዳለው በመጥቀስ ይህን የማጠናከር ስራ ለማከናወን አደረጃጀቱ እንዲስተካከል መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የኤጀንሲው ማቋቋሚያ ...
Read More »በአማራ ክልል የተከሰተው የተምች ወረርሺኝ በቁጥጥር ስር አልዋለም
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በስምንት ዞኖች ከፍተኛ የሆነ የተምች ወረርሺኝ በመከሰቱ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ችግሩን ለመከላከል እስካሁንም አጥጋቢ እርምጃ አለመወሰዱን አርሶ አደሮች ይናገራሉ። ክልልሉ የግብርና ቢሮ የኤክስቴንሺን የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ላንተይደሩ ተስፋየ እንደተናገሩት በክልሉ በሚገኙ በ64 ወረዳዎች በ434 ቀበሌዎች የተከሰተው የተምች ወረርሺኝ በ62 ሺ 87 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት አድርሷል። ...
Read More »በ2005 ዓም ኢትዮጵያ ከወደቁ አገራት ምድብ ተመደበች
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት በእያመቱ በሚያወጣው የወደቁ አገራት ሪፖርት ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር ፌልድ ስቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያ እንደ አለፉት አመታት ሁሉ ዘንድሮው የወደቁ ወይም በመውደቅ ላይ ካሉ 20 አገራት መካከል አንዷ ሆና ተመድባለች። የህዝብ ቁጥር ፣ የስደተኛ ቁጥር፣ የህዝብ ብሶት፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ያልተመጣጠነ እድገት፣ የመንግስት ህጋዊነት፣ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የደህንነት ጥበቃ፣ የሊህቃን መከፋፈልና ...
Read More »