.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ ወታደሮች የሞርሲና ቦዲ ሴቶችን የደፍራሉ ሲል አንድ የምርምር ተቋም አስታወቀ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ባወጣው መግለጫ በኦሞ ሸለቆ የሚገኙ የሙርሲና የቦዲ ነዋሪዎች አካባቢያቸው ለሸንኮራ ገዳ ምርት ይፈለጋል በሚል በሀይል ቀያቸውን እንዲለቁ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን ገልጿል። ድርጊቱ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መንግስት እርዳታና  እውቅና እየተካሄደ መሆኑም ገልጿል፡፡ የእንግሊዝ መንግስት የልማት ተራድኦ የውጭ ግንኙነት ክፍል ቃል አቀባይ ፣ ” የእኛ ድጋፍ ለዘመናት ...

Read More »

ኤርትራ በሶማሊያ ሰላም እንዳይኖር እየሰራች ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤክስፐርቶች አስታወቁ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪዩተርስ ሚስጢራዊ ሰነድ አገኘሁ በማለት ባወጣው ዘገባ ምንም እንኳ የኤርትራ መንግስት የሶማሊያ ታጣቂ የሆነውን አልሸባብን አልደግፍም ቢልም ፣ ቡድኑ ግን ኤርትራ ታጣቂውን ሀይል መደገፉዋን በመቀጠሉዋ የተጣለባት ማእቀብ እንዳይነሳ አቤት ብሎአል።  ኤርትራ አብዲ ኑር ሰኢድ በተባለ የሶማሊያ ተወላጅ በኩል እርዳታ እንደምታደርግ ማረጋገጡን ቡድኑ ጠቅሷል። በቀረበባት ክስ ላይ ኤርትራ አስተያየቱዋን አልሰጠችም። ሩሲያ እና ጣሊያን በመርማሪ ...

Read More »

ኔልሰን ማንዴላ 95 አምስተኛ ልደታቸውን አከበሩ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ አፍሪካው የነጻነት አባትና የመጀመሪያው ጥቁሩ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ 95 ኛ አመት የልደት በአላቸውን በሆስፒታል አልጋቸው ላይ ሆነው አክብረዋል። ማንዴላን እንኳን አደረሰዎት ለማለት በሆስፒታሉ የተገኙት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የማንዴላ ጤና መሻሻል እንዳስደሰታቸው ታናግረዋል። ” እንኳን አደረሰህ” ስላቸው በፈገግታ መልሰውልኛል ብለዋል ጃኮብ ዙማ። የአገሪቱ ነዋሪዎች የማንዴላን የ67 አመታት የፖለቲካ ህይወት ለመዘከር የ67 ደቂቃ ...

Read More »

በምስራቅ ኦሮምያ በልዩ ሀይሎች የተገደሉ ሰዎች በጅብ እንደተበሉ አንድ የሰብአዊ መብቶች ጠበቃ አስታወቀ

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የምስራው አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ የተሰኘው ድርጅት ለኢሳት በላከው መረጃ ከ10 ቀናት በፊት ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በ ኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በቀምቢ ወረዳ በጋራ ወሎ ቀበሌ በነዋሪዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የ38 አመቱ ጎልማሳ ኢብራሂም ሄኖ፣ የ26 እና 27 አመት ወጣቶች ሙሀመድ ሙሳና ሙሀመድ የሱፍ ሲገደሉ፣ የ25 አመቱ ኑረዲን ...

Read More »

የአውሮፓ የፓርላማ ልኡካን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰቡ መሪዎች እንዲፈቱ ጠየቁ

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝነት በማድረግ ላይ ያለው የልኡካን ቡድኑ መሪ ባርባራ ሎክብሂለር ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የማምለክና የመሰብሰብ መብታቸውን በመጠቀማቸው መታሰራቸው ተገቢ ባለመሆኑ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል። በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያለው የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ የፖለቲካ ልዩነትን ለማፈን እየዋለ መሆኑን የገለጸው የልኡካን ቡድኑ፣  የአገሪቱ ህገመንግስት ጥሩ ቢሆንም የፍትህ ስርአቱ አድሎአዊ መሆኑን ለመመልከት ...

Read More »

የሥነ-ምግባር መኮንኖች ተወቀሱ

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጽያ የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ትግሉን እንዲያግዙና የሥነ ምግባር ትምህርቶችን በየተቋሞቻቸው እንዲያሰርጹ በመንግስት መ/ቤቶች የተቋቋሙ የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች በባለሙያዎች የተሠጣቸውን ተልዕኮ እየተወጡ አለመሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሥነ-ምግባር መኮንን ተብለው በየመንግስት መ/ቤቶች የተቀመጡት እነዚሁ ባለሙያዎች በየተቋማቸው ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመዋጋት እንዳልቻሉ ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ በይፋ አምነው ተቀብለዋል፡፡ የፌዴራል የሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን በጠራው በዚሁ ስብሰባ ላይ ...

Read More »

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ ያነሱትን የአስተዳደር መሻሻል ጥያቄ ሳይመልስ እስከ መጪው መስከረም አጋማሽ ድረስ እንዲዘጋ የአመራር ቦርዱ ወሰነ።

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሌጁ ተማሪዎች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ይዘው ወደ ፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ከትናትና በስቲያ ያመሩ ቢሆንም ፤የስራ አመራር ቦርዱ ያለው ችግር እስኪጣራ ድረስ ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑን እና ተማሪዎችም ከሐምሌ 8 ቀን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ በደብዳቤ አሳውቋል። ተማሪዎቹ ከትናንት በስቲያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግበው ወደ መንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አቅንተው- ...

Read More »

የደብረብርሀን ነዋሪዎች ፍትህ አጣን አሉ

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሺዋ ዞን የደብረ ብርሃን ከተማ ኗሪዎች የመንግስት ሹማምንት የሚያደርሱባቸውን በደሎች በመዘርዝር ለመንግስት አቅርበዋል። ክልሉ በቅርቡ በጀመረው የህዝብ ብሶቶችን መስሚያ መድረኮች ላይ ነዋሪዎች ” በአደባባይ እንደበደባለን ፤እንታሰራለን፤ በአገራችን በሰላም ለመኖር አልቻልንም” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡በተደጋማሚ በሚደርስባቸው በደል አገር ጥለው የሚሰደዱ ዜጎች መበራከታቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ሹመት የሚሰጠው በዘመድ ዝማድ ነው ያሉት አንድ ተናጋሪ ፣ ...

Read More »

በኦጋዴን 500 ሰዎች መታሰራቸው ተዘገበ ኦጋዴን ፕሬስ ቱደይ የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በያዝነው ወር ብቻ 500 ሲቪሎች፣ ከጅጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ዋርዴር እና ጎዴ በደህንነት ሀይሎች ተወስደው እስር ቤት ገብተዋል። አዲሱ የእስር ዘመቻ የተከፈተው በቅርቡ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና ወታደሮች ከድተው እጃውን ለኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ከሰጡ በሁዋላ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ከታሰሩት መካከል በርካታ ህጻናትና ሴቶች ሲገኙበት፣ አብዛኞቹም ጅጅጋ አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸው ታውቋል። ሙሀመድ ...

Read More »

በአማራ ክልል በ12 ወረዳዎች ባለፉት 10 አመታት 13 ሺ 64 ሰዎች ከነፍስ ግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተገድለዋል

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 11 ሺ 93 ስዎች ከነፍስ ግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ባካሄደው  የዳሰሳ ጥናት በ10 አመታት ውስጥ ከነፍስ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ሺ 64 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 11 ሺ 93 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። በጥናቱ ውስጥ እንደተመለከተው ድብደባ መፈጸም ቀዳሚነቱን ሲይዝ  አካል ማጉደል እና ነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች  ተከታታዮችን ደረጃዎች ...

Read More »