ኔልሰን ማንዴላ 95 አምስተኛ ልደታቸውን አከበሩ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ አፍሪካው የነጻነት አባትና የመጀመሪያው ጥቁሩ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ 95 ኛ አመት የልደት በአላቸውን በሆስፒታል አልጋቸው ላይ ሆነው አክብረዋል።

ማንዴላን እንኳን አደረሰዎት ለማለት በሆስፒታሉ የተገኙት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የማንዴላ ጤና መሻሻል እንዳስደሰታቸው ታናግረዋል። ” እንኳን አደረሰህ” ስላቸው በፈገግታ መልሰውልኛል ብለዋል ጃኮብ ዙማ።

የአገሪቱ ነዋሪዎች የማንዴላን የ67 አመታት የፖለቲካ ህይወት ለመዘከር የ67 ደቂቃ የነጻ አገልግሎት ስራ በመስራት አስበዋል።