.የኢሳት አማርኛ ዜና

አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር እና አርባ ምንጭ ያካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ስለነበረው ሰልፍ በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ሲገልጽ ” ለ ስምንት አመታት የተዘጉ ልሳኖች ተከፈቱ ፤ መከራና ስቃይ ፣ የኑሮ ውድነት ያንገበገባቸው ፤ስራ አጥነት ያማረራቸው ፤ የፍትህ እጦት ያስነባቸው ወገኖች በአደባባይ ተገኝው ድምፃቸውን አሰሙ ብሎአል። • የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ • መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር • መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም! • ...

Read More »

በሲጃራ ሙስና የተጠረጠሩት የትንባሆ ሞኖፖል ኃላፊ ነፃ መባላቸውን የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ተቃወመ።

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፀረ-ሙስና ኮሚሽን- የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል ድርጅት የሥራ ኃላፊ በተጠረጠሩበት የእምነት ማጉደል ወንጀል በፍርድ ቤት በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም- ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታወቀ። ሪፖርተር እንደዘገበው ፤የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል ድርጅት ያለቀላቸው ምርቶች ግምጃ ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ በሻና 787,531.50 ሳንቲም በሚያወጣ 210 ካርቶን ኒያላ ሲጋራ በመሰወር ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ...

Read More »

በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች አለመረጋጋት እየታየ ነው

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ አባላት በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ በከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘወትር አርብ የሚደረገውን የጁመአ ስግደት አስታኮ የተቃውሞ ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱ ይታወቃል። የፖሊስን መግለጫ ተከትሎ የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ሌሊቱን የተቃውሞ መርሀግብሩን መሰረዛቸውን ...

Read More »

በአፋር አንድ ሰው በፌደራል ፖሊሶች ተገደለ

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሪሞዲያቶ ወረዳ አባ በርሀቤ ቀበሌ አቶ ሀሰን በረከት የተባሉ ነዋሪ የተገደሉት አንድ ሾፌር የቤት እንስሶቻቸውን መግደሉን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ መሀል ነው። አቶ ሀሰን ካሳ እንዲሰጣቸው ሹፌሩን በሚጠይቁበት ወቅት ጉዳዩን በትክክል ያልተረዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት በግለሰቡ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለውታል። በቅርቡ በአፋር እና በፌደራል ፖሊሶች መካከል የተጀመረው ግጭት ለግለሰቡ መገደል ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ተብሎአል። ...

Read More »

የቀድሞ የአዲስአበባ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ስራአስኪያጅ በኮበለሉ በአንድ ወራቸው ተያዙ

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያለመከሰሰ መብታቸው በፓርላማ እንዳይነሳ ከተወሰነ በኋላ እንደገና ፓርላማው ውሳኔውን በማጠፍ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳውና ወዲያውኑ ባልታወቀ ሁኔታ ከአገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡ የኦህዴድ አባልና የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ ከመሬት ጋር በተያያዘ ያለመከሰሰ መብታቸው እንዲነሳ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በወከባ ውስጥ ሆኖ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማዘጋጀት እየጣረ ነው

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው በመጪው እሁድ በመቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ሰልፎችን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በመቀሌ የአንድነት አመራሮች መጉላላት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በጅንካ ደግሞ አካባቢው የሽብርተኞች ጥቃት ኢላማ በመሆኑ ሰልፉን ማድረግ አይቻልም የሚል መመሪያ እስከ ማስተላለፍ ተደርሶ ነበር። የአንድነት አመራሮች ባሳዩት የአቋም ጽናት ሰልፉ እንዲደረግ ፈቃድ ማግኘታቸው ...

Read More »

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ሶስት ሕጎችን በማሻሻል ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዚህ ሕግ መሠረት የሕዝብ ገንዘብ ዘርፈው ወደውጪ አገር ፈርጥጠዋል የሚባሉ ሰዎች ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል ፡፡ የሚሻሻሉት ሕጎች የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ፣ የተሻሻለውን የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ እና የሙስና ወንጀሎችን እንደገና ለመደንገግ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ናቸው፡፡ ረቂቅ ...

Read More »

ወደ ደቡብ ሱዳን ይጓዝ የነበረ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሄሊኮፕተር ደብረዘይት ላይ ተከሰከሰ።

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው የተመድ ሠራተኞችን ጭኖ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲጓዝ የነበረው ሄሊኮፕተር በመከስከሱ በርካታ የተመድ ወራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የ ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው አደጋው መድረሱን በማረጋገጥ የጉዳቱ ዝርዝር መጠን እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ፈረሀን ሀቅ-ሄሊኮፕተሩ  የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በጆንገሊ ለዘረጋው  ፕሮጀክት ድጋፍ ለማድረግ ወደ ...

Read More »

የአማራ ክልል የህዝብ እና የመንግሰት ሃብት በከፍተኛ ሁኔታ እየባከነ ነው፡፡

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2005 የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ሪፖርት የህዝብና የመንግስት ሃብት አጠቃቀም አሳሳቢ የሆነ ክፍተት እንዳለባቸው ተጠቅሷል፡፡ መስሪያ ቤቱ  በመጠናቀቅ ላይ ባለው አመት በኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ፤ በገጠር መንገዶች ባለስልጣን ፤ በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጅንሲ ፤በባህል እና ቱሪዝም ና ፓርኮች ልማት ቢሮ የክዋኔ ኦዲት ሰርቷል።  251 ሚሊየን ...

Read More »

በቦረናዎች እና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ እንደቀጠለ ነው

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዞኑ ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር ምንም አይነት ትብብር እንደማያደርጉ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጀምሮ ያሉ ባለስልጣናት ከቦረና ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ቢያደርጉም ችግሩ አልተፈታም። ውዝግቡ የተጀመረው መንግስት ገሪ እየተባሉ የሚጠሩትን የሶማሊ ጎሳ አባላት በቦረና ዞን ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ነው። በቅርቡ የ50 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት ከመከሰቱ በፊት መንግስት ” የገሪ ጎሳ አባላትን” በቦረና ...

Read More »