አንድነት ፓርቲ በወከባ ውስጥ ሆኖ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማዘጋጀት እየጣረ ነው

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው በመጪው እሁድ በመቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ሰልፎችን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በመቀሌ የአንድነት አመራሮች መጉላላት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በጅንካ ደግሞ አካባቢው የሽብርተኞች ጥቃት ኢላማ በመሆኑ ሰልፉን ማድረግ አይቻልም የሚል መመሪያ እስከ ማስተላለፍ ተደርሶ ነበር። የአንድነት አመራሮች ባሳዩት የአቋም ጽናት ሰልፉ እንዲደረግ ፈቃድ ማግኘታቸው ታውቋል።