ወደ ደቡብ ሱዳን ይጓዝ የነበረ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሄሊኮፕተር ደብረዘይት ላይ ተከሰከሰ።

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው የተመድ ሠራተኞችን ጭኖ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲጓዝ የነበረው ሄሊኮፕተር በመከስከሱ በርካታ የተመድ ወራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የ ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው አደጋው መድረሱን በማረጋገጥ የጉዳቱ ዝርዝር መጠን እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ፈረሀን ሀቅ-ሄሊኮፕተሩ  የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በጆንገሊ ለዘረጋው  ፕሮጀክት ድጋፍ ለማድረግ ወደ ደቡብ ሱዳን እየተጓዘ እንደነበር ገልጸዋል።

ሄሊኮፕተሩ የሩሲያ ስሪትና  የፒ.ኤን፣ኤን ኤች ኩባንያ ውጤት መሆኑን ቃል አቀባይ ጠቁመዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአደጋው ስለደረሰው ዝርዝር ጉዳት የተሰጠ መግለጫ የለም።