መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢሳት እንደገለጹት በክልል ከተሞች ስኳርን በቀበሌዎች ለማከፋፈል የተደረገው ሙከራ በአላመስራቱ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ለልጆቻችን ሻሂ እና ሌሎች ጣፋጭ ምግቦችን ማዘጋጀት አልቻልንም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ቀደም ብሎ በቀበሌ በኪሎ 15 ብር ይሸጥ የነበረውን ስኳር፣ በ30 ብር ማግኘት እየተሳናቸው መምጣቱን ተናግረዋል። መንግስት ላለፉት 2 አመታት ዘይትና ስኳር በየቀበሌዎች ሲያከፋፍል መቆየቱ ይታወቃል።
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ በአለም ላይ በኢንተርኔት ስርጭት ከመጨረሻዎቹ ተርታ ተመደበች
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለማቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ማህበር ባወጣው መረጃ በአለም ካሉ አገራት ጊኒ ቢሳው፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ማእከላዊ አፍሪካና ኒጀር የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል። በተቀራኒው ደቡብ ኮሪያ፣ ስዊድን፣ አይስላንድ፣ ዴን ማርክ፣ ፊንላንድ ፣ ኖርዌይ፣ ኔዘርላንድስ እንግሊዝና ሆንግ ኮንግ ከ አንድ እሰከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትን ለግል ባለሀብቶች እንዲለቅ ግፊት ቢደረግበትም ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ በ2005 የስራ አፈጻጸምና የ2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል። በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ ...
Read More »በአርባምንጭ የቴክኖሎጂ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምዘና ፈተና ጋር በተያያዘ በተማሪዎችና እና በዩኒቨርስቲው አስተዳደር መካከል በተፈጠረ ልዩነት ከ3 ሺ በላይ ተማሪዎች ዩኒቭረስቲውን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው በቤተክርስቲያናትና በሰዎች ቤት ተጠልለለው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ተማሪዎቹ ከእረፍት በተመለሱበት ማግስት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ የምዘና ፈተና ውሰዱ መባላቸውን ተቃውመው ተጨማሪ የጥናት ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው ችግር መፈጥሩን ገልጸዋል። የዩኒቨርስቲው ዲን በተማሪዎችላይ የተለያዩ ታፔላዎችን ...
Read More »የአባይ ግድብ መሰረቱ ችግር ሊኖረው ይችላል ተባለ
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉበርግ የአለማቀፍ አጥኚዎች ቡድንን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው መንግስት በማስገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ መሰረቱ ችግሮች ሊኖሩበት ስለሚችል መንግስት እንደገና እንዲያስጠና መክሯል። ግድቡ በታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በደንብ መጠናት አለበት ሲሉ የባለሙያዎቹ ቡድን አስተያየቱን ሰጥቷል። የግድቡን መሰረት ለማጠንከር መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ያስፈልጋል በማለት ያመለከቱት ባለሙያዎች፣ “ድክመት ቀጠና ” ተብሎ በተለየው አካባቢ ...
Read More »ከ200 በላይ ስደተኞች አሁንም አልተገኙም
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ደሴት አካባቢ በጀልባ መስጠም ከሞቱት መካከል የ11 ሰዎች አስከሬን ቢገኙም፣ ከ200 በላይ ሰዎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም። ፖፕ ፍራንሲስ በስፍራው ተገኝተው አደጋውን ከተመለከቱ በሁዋላ ሀዘናቸውን ገልጸዋል፣ ችግሩን ዝም ብለው የሚያዩትን አገራትም ወቅሰዋል። ብዙ የጣሊያን ባለስልጣናት የህጻናቱን አስከሬን እያዩ ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው ሲያለቅሱ ታይቷል። እስካሁን ድረስ አስከሬናቸው የተሰበሰበውና የጠፉት ሰዎች ...
Read More »የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር የብቃት መመዘኛ ፈተና ዙሪያ መግባባት ባለመቻላቸው ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስተላለፈው ውሳኔ በተማሪዎቹና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባትን በመፍጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርሰቲውም የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ግቢ ለቀው መውጣታቸውን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ እንዲወስዱ ሲጠይቃቸው ተማሪዎቹ በቂ የዝግጅት ጊዜ ...
Read More »የህንድ ኩባንያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልን ሊያስተዳድር ነው
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽንን የሥራ ሂደት ለማስተዳደር አንድ የህንድ ኩባንያ ተመረጠ፡፡ ፖወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ኦፍ ኢንድያ የተባለው ኩባንያ የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ሀይል ለማስተዳደር የሁለት ዓመት ኮንትራት ተሰጥቶታል፡፡ መንግስት ድርጅቱን ለውጭ ኩባንያ መስጠት የወሰነው በድርጅቱ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉና የተሻለ ስራን በሀገሪቱ ለማስተዋወቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ ድርጅቱን ለውጭ ...
Read More »ደቡብ ክልል ለዋልታ 19 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ፈቀደ
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ብሔራዊ መንግስት መስተዳደር በክልሉ ያሉ ከተሞችን አስመልክቶ ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራት ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል 19 ሚሊዮን ብር ለመፍቀድ ስብሰባ መቀመጡን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ በፖለቲካ ውሳኔ ለመንግስታዊው ዋልታ የመረጃ ማዕከል ሊሰጥ የታቀደው ፕሮጀክት የደቡብ ክልል መገናኛ ብዙሀንን ቅር ማሰኘቱ ታውቋል፡፡ የክልሉ መገናኛ ብዙሀን በቂ መሳሪያና የሰው ሀይል እያለው ስራውን ግልጽነት በጎደለው ሁኔታ ለዋልታ እንዲሰጥ ...
Read More »በሙስና ከተጠረጠሩ ግለሰብ 7 ሚሊዮን ጥሬ ብር ተያዘ
መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበሪያ ሀላፊ ከነበሩት ግለሰብ ሰባት ነጥብ አራት ሚሊዮን ጥሬ ገንዘብ መያዙን የፌደራል ስነ ምግባር ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጹ፡፡ ሀላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ስዩም 12 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎችን በሌላ ሰው ስም ገዝተው ለተገዙት መኪኖች ውክልና በመውሰድ መኪኖቹን ለሌሎች ሰዎች ሸጠዋል የሚል መረጃ ቀርቦባቸዋል፡፡ ከመኪናዎቹ በተገኘ የሽያጭ ...
Read More »