መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ አዲስ ፕሬዚደንት በመምረጥ የዚህን ዓመት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ፓርላማ በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ በንባብ የቀረበውን የመንግስት የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫና ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀጣይ ሳምንት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት በሚቀርቡ የድጋፍና የተቃውሞ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወያያል፡፡ ፓርላማው በትላንት ውሎው መስከረም 27 ቀን 2006 ዓም አዲሱ ፕሬዚደንት ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግርን አስመልክቶ ገዥው ፓርቲ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
መንግስት ለኢትዮጵያ የሚዲያ እድገት መዳከም ዋና ተጠያቂ ነው ተባለ
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውይይታቸውን ያደረጉ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ጋዜጠኞች ሚዲያዎቹ በመንግስት የአፈና እና የእጅ አዙር ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የባለሙያዎች የጥናት እና ምርምር ግኝት ስራዎች ላይ ተመርኩዞ ከባለሙያዎች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በቀረቡት ጽሁፎች እንደተገለፀው የኢትዩጵያ ሚዲያዎች አዲስ የሚቋቋሙትም ሆነ ነባር የሕትመት ሚዲያዎች የፋይናንስ ብቃታቸው ዝቅተኛ ...
Read More »ዋልያዎች፦” የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድንን ካሸነፍን እንዲሚሰጠን ቃል የተገባልን ቦነስ ገንዘብ ያንሰናል” በማለት ቅር መሰኘታቸው ተገለጸ።
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱፐር ኤግልስን ካሸነፉ መንግስት እንደሚሰጣቸው ቃል የገባላቸው ቦነስ በቂ እንዳልሆነና ስሜታቸውን የሚያነሣሳ እንዳልሆነ ነው ተጫዋቾቹ የተናገሩት። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀናት በፊት የ22ቱን ተጫዋቾች ስም ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ በቡድኑ ውስጥ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆነው ጌታነህ ከበደ በጉዳት ምክንያት በቡድኑ ውስጥ አልተካተተም። በቀራቸው የደርሶ መልስ ጨዋታ ናይጀሪያን አሸንፈው ለዓለም ዋንጫ ካለፉ የሚሰጣቸው ቦነስ ምን ያህል እንደሆነ ...
Read More »የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው። ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ መድረክ እንድናወጣላቸው ተማጽነዋል። መንግስት ከአሁን ...
Read More »መንግስት የተቃጠሉትን አብያተ ቤተክርስቲያናት ለፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀምባቸው ነው ተባለ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል። ፓርቲው እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ በሚሰጠው ስልጠና የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ለ10 ቀናት ተዘግተዋል።
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ህዝቡ ጉዳይ ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ ባለስልጣናቱ ስልጠና ላይ ናቸው የሚል ...
Read More »ደቡብ ሱዳን የአብየ ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ አለማቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበች
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል:: የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር ማለትም በጥቅምት ወር ይካሔዳል ቢልም ...
Read More »ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጡ።
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሦስተኛው የ ኢህአዴግ ፕሬዚዳንት በመሆን በ አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ምትክ ተሾሙ። የኢህአዴግ/ኦህዴድ አባል የሆኑት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን በመተካት ሁለተኛው ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ በስፋት የተወራ ቢሆንም፤”ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚመረጠው ሰው የማናቸውም ፓርቲ አባል ያልሆነ ገለልተኛ ሰው መሆን አለበት” የሚል መመሪያ በማውጣት የግል ...
Read More »በአፋር የክልል የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እየተካሄደ ነው
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በክልሉ ከመልካም አስተዳደር እና ከሰዎች መፈናቀል ጋር በተያያዘ የሚታየው ችግር እየተባባሰ በሚገኝበት ሁኔታ የክልሉን ባለስልጣናት ለመምረጥ በአዋሽ አርባ ታንከኛ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ስብሰባ እየተካሄ ነው። ከፍተኛ የህወሀት ድጋፍ አላቸው የሚባሉት የአቶ እስማኤል አሊሴሮ ደጋፊዎች በአንድ በኩል ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ሰዎች በሌላ በኩል ሆነው በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን ፣ ፕሬዚዳንቱና ...
Read More »የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግዴታ ስለ አክራሪነት እና ሽብረተኝነት ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በ2006 ዓም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፣ ሽብርተኝነት እና ጸረ ሰላም ሀይሎች ትምህርት ለመስጠት የጀመረውን እቅድ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጀምሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር። ባለፈው አርብ እና ቅዳሜ በአዲስ ...
Read More »