.የኢሳት አማርኛ ዜና

በቡራዩ ከ500 በላይ ቤቶች ፈረሱ

ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው እለት የአዲስ አበባ መስተዳድር በቡራዩ አካባቢ በወሰደው እርምጃ፣ ከ500 በላይ ቤቶችን ያፈረሰ ሲሆን በርካታ ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አመዲና ጎጥ በተባለ አካባቢ የሚኖር አንድ መስፍን የተባለ ወጣት ወላጆቼ በሰሩት ቤት መኖር ካልቻልኩ ምን ህይወት አለኝ በሚል ራሱን ማጥፋቱም ታውቋል። የቀበሌው ሊቀመንበር ህዝቡን ሰብስቦ ለማነጋገር ቢመክሩም ህዝቡ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚቃወሙ ሰልፎች እንደቀጠሉ ነው

ህዳር ፲፩(አስራ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የላቸውም በሚል የሳውዲ ፖሊሶች እና ወጣቶች በኢትዮጵያውያን ሴቶች፣ ህጻናትና ወንዶች ላይ የፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በተለያዩ የውጭ አገራት የሚካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች እንደቀጠሉ ሲሆን ፣ በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ በርን በተካሄደው ተቃውሞ ኢትዮጵያውያኑ ስሜታቸውን ለመቆጣጠር ተስኖአቸው ታይተዋል። ኢትዮጵያውያኑ የሳውዲን መንግስትና የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ሳውዲ ኢምባሲ ...

Read More »

የስዊድን የጦር ፍርድ-ቤት አቃቢ-ህግ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡

ህዳር ፲፩(አስራ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጦር ፍርድ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቅርቡ በኦጋዴን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበርና የፕሬዚዳንቱ የግል ዌብሳት ማኔጀር እና አማካሪ የነበረው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በኦጋዴን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የጦር ፍርድ ቤቱ ዋና አቃቢ ህግ ክሪስተር ፒተርሰን በ10 ...

Read More »

የፌደራል ፖሊሶች በሳውድ አረቢያ የሚፈጸመውን ግፍ ለመቃወም አደባባይ በወጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

ህዳር ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የሳውዲን መንግስት ለመቃወም በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞዋቸውን ለመግለጽ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ታስረው የነበረ ሲሆን እስከ ምሽት ድረስ 40 የሚሆኑት ተለቀዋል። ሰልፉን ያዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ 15 የአመራር አካላትም በእስር ላይ እንደሚገኙና ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ...

Read More »

በሰዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ተባብሶ ቀጥሏል።

ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮያውያን በሰልፍ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ውለዋል። በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ተባብሶ መቀጠሉን ተጠቂዎቹ ለኢሳት ገለፁ። በሪያድ  ወደማጎሪያ ካምፕ ውስጥ  የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ስፍራ ሆነው ለ ኢሳት በስልክ እንደገለፁት፤ በትናንትናው ዕለት ብቻ  በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከባድ መኪናዎች እየተጫኑ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ስደተኞቹ-ለሳዑዲ ፖሊሶች፦” ወደ ሦስተኛ አገር የማታሻግሩን ከሆነ ወደ ...

Read More »

የኢትዩጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በኢትዩጵያ እየደረሰ ስላለው በደል አምላክ መፍትሄ እንዲያመጣ ለመለመን የሁለት ወራት የጾም እና የጾለት ጊዜ በመላው አለም እንዲደረግ አወጀች፡፡

ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዳር እና የታህሳስ ወራትን  በሙሉ በጾም በጾሎት ምእመኑ እግዚኦታ እንዲያሰማ ቄስ አለሙ ሺጣ የኢትዩጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ጽሓፊ በአምላክ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኢትዩጵያ በአሁኑ ስዓት እየተሰተዋለ ላለው ችግር ፣በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ሐገራት እንዲሁም በአለም ለሚታየውና ለሚሰማው በደል- ሀይማኖቱ በሚጠይቀው ስርዓት እጆችን ወደ አምለክ እንድናነሳ እና እንድናለቅስ የምንገደድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ በሳዑዲ አረቢያ ግፍ ከተፈፀመባቸው ዜጎች ጎን እንደሚቆም አስታወቀ።

ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሸንጎው ከፍተኛ የአመራር ምክርቤትቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱመንግስት የጸጥታ ሀይሎችእየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ እንዳጤነው ገል ል። ሸንጎው  ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን  በመግለጽ  ከጎናቸው እንደሚቆምምአረጋግጧል። በተመሣሳይ የ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢህአፓ) ሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሁሉ ...

Read More »

መንግስት ሁኔታው በርዷል በማለት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በኩል ቢናገርም፣ ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን ግን ችግሩ መክፋቱን እየገለጹ ነው።

ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሴቶች ካምፕ ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ይነጋራሉ። ቀን በጸሀይ ማታ ደግሞ በብርድ እንድናሳልፍ እየተገደድን ነው የምትለው ሌላዋ እስረኛ ሳሚራ፣ ህጻናት እና እናቶች በምግብ እጦት እየተጎዱ ለበሽታም እየተዳረጉ ነው ትላለች። ባለፉት አራት ቀናት የወለዱ እናቶች መኖራቸውን የምትገልጸው ሳሚራ፣ የሳውዲ ፖሊሶች ወላዶችን የት እንደወሰዱዋቸው እንደማታውቅ ገልጻለች። ሀብታም የተባለቸውም እንዲሁ እርሷ በምትገኝበት ቦታ ላይ ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ አርብ ለሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ለኢሳት እንደገለጸው ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍል ፣ የሰላማዊ ሰልፍ መጠየቂያ ደብዳቤውን እንደማይቀበል ቢገልጽም፣ ፓርቲው ተቃውሞውን በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ለማድረግ ወስኖ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ተባብሮ ተቃውሞ ማዘጋጀት ሲገባው፣ ፓርቲው እንዳያዘጋጅ መከልከሉ እንዳስገረመው ወጣት አሬድ ገልጿል። ኢትዮጵያውያን ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍም ...

Read More »

በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የፖለቲካና ሲቪክ ተቋማት በሳውዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል አወገዙ

ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ፣ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ካንውነስል፣ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ፣ ሂውማን ራይተስ ሊግ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም መድረክ ድርጊቱን የሚያወግዙ መግለጫዎችን ለኢሳት ልከዋል።  

Read More »