ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማዕድን ሚኒስትር በመሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉትት ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሾሙ ምንም የሚያውቁት ነገር እንዳልነበር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከ16 ዓመታት በላይ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውስጥ ከኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትር ዴኤታ ባሉት የሀላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ የቆዩትና እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር 2010 የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተለያየ አደረጃጀት ይዞ ለሁለት ሲከፈል ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የደቡብ አፍሪካ ታላቁ የሰራተኛ ማህበር ለገዢው ፓርቲ ድጋፍ እንደማያደርግ አስታወቀ
ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ300 ሺ በላይ አባላት ያሉት የደቡብ አፍሪካ የሜታል ሰራተኞች ማህበር ደቡብ አፍሪካ ነጻ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ በስልጣን ላይ ያለውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሲደግፍ ቆይቷል። ማህበሩ ለማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ድጋፉን እንደማይሰጥም አስታውቋል። የፕሬዚዳንት ዙማ መንግስት ሙስናንና ድህነትን በመዋጋት በኩል በቂ ስራ አልሰራም በሚል እየተተቸ ነው። የሰራተኛው ማህበር ከታዋቂው ነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ...
Read More »በጅጅጋ ከተማ ታቆሽሻላችሁ ተብለው ከታሰሩት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-9ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ለማክበር ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ከተማ ያቆሽሻሉ ተብለው ተይዘው ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ ከምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት እንዲገቡ ከተደረጉት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በመሞታቸው በታሰሩበት አካባቢ እንዲቀበሩ ተደርጓል። ሟቾቹ በደንብ ባለመቀበራቸውና የአንዳንዶችን አስከሬን ጅብ አውጥቶ ስለበላው፣ ሌሎቹ ከእስር ቤቱ ራቅ ብለው በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ኢሳት ከክልሉ ...
Read More »የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ከስልጣን ተነሱ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልልን ላለፉት ስምንት ዓመታት ተኩል በፕሬዚደንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አያሌው ጎበዜ ከኃላፊነታቸው ተነሱ፤ በምትካቸው ምክትል ፕሬዚደንቱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተሹመዋል፡፡ አቶ አያሌው ከኃላፊነታቸው የተነሱት እየተካሄደ ባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ዙር ፤ አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአቶ አያሌው መውረድና በአቶ አንዳርጋቸው መተካት ...
Read More »በጉንዶ መስቀል በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው ሲያገለግሉ የነበሩ ባለስልጣናት ምርመራ ተካሄደባቸው
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በጉንዶመስቀል ከተማ በመስተዳድሩ ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩት መካከል ከ108 በላይ ሰዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች የተለያዩ የሃለፊነት ቦታዎችን ወስደዋል በሚል የአካባቢው ፖሊስ ምርመራ በማድረግ ላይ ነው። ፖሊስ እስካሁን ባደረገው ምርመራ 13 ሰዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥረው ለአመታት ደሞዝ ሲቀበሉ መቆየታቸውን በማረጋገጥ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መርቶታል። በቀሪዎቹ ...
Read More »ደቡብ ሱዳን በእርስ በርስ ግጭት እየታመሰች ነው
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በቀድሞው ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል የተነሳው ውዝግብ የዲንቃና የኑዌር ጎሳዎችን እርስ በርስ እንዲዋጉ እያደረጋቸው መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። የሪክ ማቻር ደጋፊዎች ጆንግሌ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን መቆጣጠራቸው ተሰምቷል። ምንም እንኳ የአገሪቱ መሪ መፈንቅለ መንግስቱን ማክሸፋቸውን ቢናገሩም፣ በሌሎች አገሪቱ ክፍሎች አሁንም ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው። ከስልጣን የተባረሩት ሪካ ማቻር ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪር ስልጣን ...
Read More »የአለማቀፉ ፍርድ ቤት በኬንያው መሪ ላይ የጀመረውን ምርመራ አቋረጠ
ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና አቃቢ ህጓ ምርመራውን ለማቋረጥ የተገደዱት ሁለቱ ዋና ምስክሮችን ለማግኘት ባለመቻላቸው ነው። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከ6 አመት በፊት በተነሳውና ከ1 ሺ 200 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የምርጫ ማግስት ረብሻ አነሳስተዋል በሚል ነው። በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ላይ የተጀመረው ክስ ይቀጠል አይቀጥል የታወቀ ነገር የለም። የአፍሪካ መሪዎች ክሱ እንዲቋረጥ ሲወተውቱ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ ክሱን እየተከታተሉ አገሪቱን ለመምራት አይችሉም ...
Read More »የጌዲዮ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች በረሀብ መጠቃታቸውን የሚያመለክት ደብዳቤ ተፈራርመው ለዞኑ መስተዳድር አቀረቡ
ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 9 ወረዳዎች ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ረሀብ በመከሰቱ የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡ ያለበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ የተፈራረሙበትን ደብዳቤ ዛሬ ለዞኑ መስተዳድር አስገብተዋል። በከፍተኛ ደረጃ ተደናገጡት የዞኑ ባለስልጣናት መረጃው ይፋ እንዳይወጣ ለማድረግ ዛሬ ቀኑን ሙሉ በስብሰባ ተወጥረው መዋላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ የገጠሩ ህብረተሰብ በከፍተኛ ሁኔታ በመራቡ መንግስት ...
Read More »የግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል “መጪው አመት ህዝብን የመታደግ እርምጃ የሚወሰድበት አመት ይሆናል” አለ
ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዝባዊ ሀይሉ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ” ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ ድርጅት መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ” ነበር ብሎአል። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሀይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባለፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የአገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች ...
Read More »የቆዳ ፋብሪካዎች የጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅርቦት ችግር ገጥሞናል አሉ።
ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ያሉት የቆዳ ፋብሪካዎች የግብዓት ፍላጎታቸው በዓመት ከ40 ሚሊዮን በላይ የበግና ፍየል ሌጦና ከ2 ሚሊየን በላይ የበሬ ቆዳ ሲሆን፥ እየቀረበላቸው ያለው የቆዳ መጠን ከ16 እስክ 17 ሚሊየን ሌጦ እና በቆዳ ደግሞ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በታች ነው። ከዚህ በመነሳት ሃገሪቱ ከዘርፉ የምትጠብቀውን ገቢ ማሳካት አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስትቲዩት ...
Read More »