.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሶማሊያ በአንድ ታዋቂ ሆቴል ውስጥ ቦንድ ፈነዳ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞቃዲሹ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ጃዚራ ሆቴል ውስጥ በሁለት መኪኖች የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተዋል። ፍንዳታው ከመድረሱ በፊት በጠባቂዎች እና ፍንዳታውን ባደረሱት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። በአሁኑ ፍንዳታ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ አልታወቀም። ባለፈው ሳምንት በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። አልሸባብ አሁንም የደቡብ የሶማሊያ አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። የኢትዮጵያ ጦር ...

Read More »

የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት ሊከሰሱ ነው

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሳዑዲ መንግስት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጽያዊያን ማባረሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ ኤጀንሲዎች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በኢትዮጽያ በአጠቃላይ 470 የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች የሚገኙ ሲሆን 100 ያህሉ በህገወጥ የሰዎች ...

Read More »

ኢትዩጵያ ህጻናትን ወደ ውጭ በጉዲፈቻ ስም በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑዋና መረጃዎች አመለከቱ

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት። በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት የህይዎት ታሪክ ላይ የሚጻፈው ” ...

Read More »

ኢህአዴግ በሶስት ድርጅቶች ላይ አዲስ ዘጋቢ ፊልም እያዘጋጀ መሆኑ ተሰማ

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመሰራት ላይ ያለው አዲስ ፊልም ኦነግ ፤ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የሚያወግዝ ነው። ኢህአዴግ በዚህ ሰአት ፊልሙን ለምን ለመስራት እንደፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚገምቱት ከሆነ ግን ገዢው ፓርቲ በድርጅቶች እንቅስቃሴ ስጋት እየገባው ነው። እየተሰራ ባለው ፊልም ውስጥ ኢሳትንም ለመወንጀል እየታሰበ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል። ዘጋቢ ፊልሙ እስካሁን ባለመጠናቀቁ እና ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች ለድርድር ወደ አዲስ አበባ ቢያመሩም ጦርነቱ አልቆመም

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ለውይይት በአዲስ አበባ ይገኛሉ። ማቻር የሰላም ድርድሩን የተቀበሉት የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ አገራቸውና የኢጋድ አባላት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት አማጽያኑን እንደሚወጉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው የሚለውን ዘገባ መሪው አስተባብለዋል። ለፕሬዚዳንት ሙሰቬኒ ...

Read More »

የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት እየተከበረ ነው

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎርጎሪያን ካላንደር የሚቆጥሩ አገሮች አዲስ ዓመታቸውን በልዩ ድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ። በጎርጎሪያን ቀመር መሰረት ኢየሱስ  በዳዊት ከተማ በኢሩሳሌም በምትገኘው ቤተ-ልሔም ከተወለደ 2014 ዓመት ሆኖታል ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ አዲስ ዓመትን ከሁሉም ቀደም ብላ የተቀበለችው አገር  ኒውዚላንድ ነች። ቤጅንግን ጨምሮ የምስራቅ እስያዎቹ  ጃካርታ እና ሲንጋፓር አዲስ ዓመቱን በደመቀ ሁኔታ ተቀብለዋል ።

Read More »

በተቀነባበረ የመብራት ሀይል ሙስና ኢትዮጵያ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ተደረገ

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል። የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት ሃይል የቦርድ ሰብሰባ የሆኑት  ዶ/ር ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ከደቡብ ሱዳን ማስወጣት መጀመሩን አስታወቀ

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 1 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከቦርና ቢንቲዩ ግዛት መውጣታቸውን እና 650 የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ ቀሪዎቹ ደግሞ ዋና ከተማዋ ጁባ መግባታቸውን ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ እንዳሉት ሁኔታዎች እየከፉ የሚሄዱ ከሆነ ቀሪዎቹን ዜጎች የማውጣት እቅድ አለ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በግጭቱ ውስጥ ከሞቱት 1 ሺ ሰዎች መካከል ...

Read More »

በገጠር መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ውስጥ በብልሹ አሰራር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየባከነ ነው

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በባለስልጣኑ ውስጥ በብልሹ አሰራር   በትግራይ ክልል 37 ሚልየን 832 ሺ 770 ብር 35 ሳንቲም ለብክነት ተዳርጓል፡፡ በኦሮምያ ክልል ከ17 ሚልየን 892 ሺ ብር በላይ ፤ በደቡብ ክልል ከ23 ሚልየን 19 ሺ ሰባ ሶስት  ብር አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ባክኗል። በመተማ አብረሃጅራ ፕሮጀክት ብቻ ...

Read More »

ለስኳር ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልተገኘም ተባለ

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርትር እንደዘገበው በአምስት አመቱ የልማት እቅድ መሰረት 10 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለመገንባትና 3 ነባር ፋብሪካዎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የተጓተተውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ለማጠናቀቅ እቅድ ቢወጣም ፣ ሶስቱ ነባር ፋብሪካዎች ከህንድ በተገኘ 640 ሚሊዮን ዶላር ብድር ግንባታቸው እየተካሄደ ሲሆን፣ ለአዳዲሶቹ በቂ ገንዘብ አልተገኘም። የስኳር ኮርፖሬሽኑ 75 ቢሊዮን ብር ከመንግስት ግምጃ ቤት በሚገኝ ፋይናንስ ...

Read More »