ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣናቱ ማንኛውንም ቃለምልልስ ለኢሳት ቢሰጡ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ። የባለስልጣኖች አንደኛው መገምገሚያም ለኢሳት መረጃ በመስጠት እንደሚወሰን ከኢህአዴግ የመረጃ ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክቷል። መመሪያው ለህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለ ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች መተላለፉ ታውቋል። የመንግስት ባለስልጣናት ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ህጋዊነት እያላበሱትና ሌሎችም ዜጎች አንዲናገሩበት እያደፋፈሩ ነው የሚል ምክንያት መሰጠቱ ታውቋል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞቿን ከደቡብ ሱዳን እያስወጣች ነው
ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና የተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር ወኪሎች ለድርድር አዲስ አበባ በሚገኙበት በዚህ ሰአት ፣ የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲ ሰራተኞች በሙሉ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ፣ የአሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞች በተዘጋጀላቸው አውሮፕላን ለቀው ይወጣሉ። ከጃንዋሪ 4 ጀምሮም ምንም አይነት አገልግሎት በኢምባሲው በኩል እንደማይሰጥ ግልጽ አድርጓል። የመንግስት ታጣቂዎች በተቃዋሚዎች የተያዙትን ቦታዎች ...
Read More »የጣሊያን የድንበር ጠባቂዎች የ1 ሺ ሰዎችን ህይወት ማትረፋቸው ተገለጸ
ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአብዛኛው የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ዛምቢያ፣ ማሊና ፓኪስታን ዜጎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች መርከብ ጉዳት ከመድረሱ በፊት የጣሊያን ጠባቂዎች ደርሰው እንዳዳኑዋት ቢቢሲ ዘግቧል። ከሶስት ወራት በፊት ላምፓዱሳ እየተባለች በምትጠራዋ የጣሊያን ግዛት አቅራቢያ ከ400 በላይ ሰዎች መስጠማቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። የአሁኑ እርምጃም ይህን ትችት ለማምለጥ የተወሰደ ይመስላል። በአደጋው ከተረፉት መካከል 40 ...
Read More »በግብጽ በተነሳ ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ
ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚገኙ የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት 6 ሰዎች ተገድለዋል። ፓርቲው በበኩሉ የሞቱት ሰዎች 17 ናቸው ይላል። ግጭቱ የተነሳው ግብጽ መንግስት ፓርቲውን አሻበሪ ብሎ መፈረጁን ተከትሎ ነው። የፓርቲው መሪዎችና በቅርቡ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈው ስልጣን ላይ የነበሩት ሙሀመድ ሙርሲ ወደ እስር ቤት ከተላኩ በሁዋላ ግብጽ ሰላም ለማግኘት ...
Read More »በህወሀት ውስጥ የሚገኙ አክራሪ የሚባሉት ቡድኖች የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ
ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ አዛዦች ለኢሳት እንደገለጹት የህወሀት ባለስልጣናት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ለመተካት የተሻለ ቦታ ላይ የነበሩትን ጄ/ል አበባው ታደሰን አድማ ለማድረግ አስበዋል በሚል ሰበብ ማእረጋቸውን እንደያዙ የሚሰጣቸው ሃላፊነት እንዲቀነስና ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ አድርገዋል። ለዚህም ስራ ጄኔራል ማሞ ሀይለማርያም እና ጄኔራል ሰሐረ መኮንን ተባባሪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሶስቱ ጄኔራሎች “ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ...
Read More »ለ18 ዓመታት በስራ ላይ የቆየው ሕግ ሕገመንግስትን ይጥሳል ተባለ
ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴሬሽን ምክርቤት ላለፉት 18 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ጉዳያቸው የታየበት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8 ተራ ቁጥር 1 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7 ተራቁጥር 1 ሕገመንግስቱን እንደሚጥሱ በመወሰን የመላኩ ፈንታን አቤቱታ ውድቅ ...
Read More »በስደት ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሩዋንዳው የደህንነት አዛዥ ተገደሉ
ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ በስደት ላይ የሚገኙት የሩዋንዳ የደህንነት ዋና አዛዥ የነበሩት ፓትሪክ ካሪጋያ የተገደሉት ጆሀንስበርግ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ነው። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እንዳለው የሩዋንዳ መንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ካሪጋያ የተገደሉት በገመድ ታንቀው ሳይሆን አይቀርም። የ53 አመቱ ሚ/ር ካሪጋያ ላለፉት 6 አመታት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በስደተኝነት ቆይተዋል። ኮሎኔል ካሪጋያ ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ከተጋጩ በሁዋላ ...
Read More »በደቡብ ክልል የይርጋ ጨፌ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መምህራኑ አድማውን የጀመሩት ያለፍላጎታችን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደሞዛችን እየተቆረጠብን ነው በሚል ነው። መምህራኑ ለይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር፣ ለጌዲዮ ዞንና ልክልሉ ትምህርት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ” ከ ሀምሌ 2005 ዓም ጀምሮ ለህዳሴ ግድብ የሚቆረጠው ገንዘባችን እኛ ያለፈቀድነውና ያልተስማማንበት በመሆኑ ጥቅምት 28፣ 2006 ጀምሮ ስራችንን በአግባቡ እየሰራን የመብት ጥያቄያችንን ለሚመለከተው ሁሉ ስናቀርብ ...
Read More »በኢትዮጵያ የተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እየከለከሉን ነው ሲሉ 18 የቻይና ኩባንያዎች አመለከቱ
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል። ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው ጋዜጣው፣ በእነዚህ የመሠረተ ልማት ዘርፎች ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ግጭቱ እንደቀጠለ ነው
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲሲቷ አፍሪካዊት አገር የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት በሺ የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ የሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ተደራዳሪዎች በአዲስ አበባ ቢገኙም አሁንም ጦርነቱ ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ድርድር የተኩስ አቋም ስምምነት እንዲፈረም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር በበኩላቸው የተኩስ ማቆም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ አለመሆናቸውን ገልጸዋል። በደቡብ ...
Read More »