በግብጽ በተነሳ ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚገኙ የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት 6 ሰዎች ተገድለዋል። ፓርቲው በበኩሉ የሞቱት ሰዎች 17 ናቸው ይላል።

ግጭቱ የተነሳው ግብጽ መንግስት ፓርቲውን አሻበሪ ብሎ መፈረጁን ተከትሎ ነው።

የፓርቲው መሪዎችና በቅርቡ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈው ስልጣን ላይ የነበሩት ሙሀመድ ሙርሲ ወደ እስር ቤት ከተላኩ በሁዋላ ግብጽ ሰላም ለማግኘት አልቻለችም።

አገሪቱን ከጀርባ ሆኖ የሚመራው ወታደራዊው መንግስት የሆስኒ ሙባረክን መንግስት ለመገልበጥ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን 3 ወጣቶችንም ይዞ አስሯል።

በቅርቡ በፖሊስ አባላት ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች መበራከት አገሪቱ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ትገባ ይሆን የሚለውን ስጋት ፈጥሯል።