የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግጭቱ የተነሳው በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የመዘጋጃ ሰራተኞች እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። ህዝቡ ድንጋይና ዱላ በመያዝ ፖሊሶችን ደብድቦ ያባረረ ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ተደራጅተው በመምጣት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትተው የተወሰኑትን ደብድበው አስረዋል። ፍጥጫው ዛሬም ደረስ የቀጠለ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪ ቤቶቻችን አይፈርሱም በማለት በአቋሙ እንደጸና ነው። የቆሰሉት ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በቁጫ ወረዳ አንድ ወጣት ራሱን እናቱንና ከብቶቹን በእሳት አጋየ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ በቦላ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ9ኛ ክፍል ተማሪ ኢዮብ ኢማን የካቲት 21 ቀን 2006 ዓም ከምሽቱ 3 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ራሱን ጨምሮ እናቱን፣ 8 የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን በእሳት አጋይቷል። ወጣቱ የካቲት 3 ቀን የቁጫ ወረዳ ባህላዊ ዘፈን ከጓደኞቹ ጋር እየዘፈነ በሄደበት ወቅት አንድ የፖሊስ ባልደረባ ” ...
Read More »በኬንያ የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ መቱ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአድማው መነሻ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተጣለውን አዲስ የፓርኪንግ ክፍያ ተከትሎ ነው። ባለ ታክሲዎቹ መኪኖቻቸውን ለማቆም ከፍተኛ የሆነ ከፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። ባለ ታክሲዎች ባደረጉት አድማ አብዛኛው ሰራተኛ ብእግሩ ስራ ለመግባት ተገዷል። ባለስልጣናቱ በበኩላቸው እርምጃው በናይሮቢ የሚታየውን መጨናነቅ ለመቀነስ ነው ይላሉ።
Read More »በጅቡቲ መንገድ ላይ በአድማ ቆመው የነበሩ ከባድ መኪኖች ዛሬ ስራ ጀመሩ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ የከባድ መኪና ሾፌሮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሶስት ቀናት በፊት አንድ ሾፌር እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደሉን ተከትሎ የተጀመረው አድማ ዛሬ ተጠናቆ መኪኖች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን የሆኑት አቶ ካሳሁንና ኮሚሽነር ግርማይ ከሾፌሮች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ገዳዩን አድነው እንደሚይዙት ቃል በመግባት ሾፌሮች ስራ እንዲጀምሩ መክረዋል። ሾፌሮች በበኩላቸው ባልደረባቸው የተገደለበት ሁኔታ እጅግ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የስምሪት ሃላፊ ሾመ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 በመጥለፍ ጄኔቫ በማሳረፍ ጥገኝነት መጠየቁን ተከትሎ፣ ካፒቴን ዮሃንስ ሃይለማርያምን አዲስ የስምሪት ሃላፊ አድርጎ ሾሟል። የቀድሞው ሃላፊ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን በምን ሁኔታ እንደለቀቁ ባይታወቅም፣ ስልጣናቸውን የለቀቁት በጠለፋው ማግስት መሆኑ ጉዳዩ ከሃይለመድህን አበራ ጠለፋ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ። በሌላ ...
Read More »በምእራብ ጎጃም የእርሻ መሬታቸውን ለአበባ እርሻ ለመስጠት ፈቃደኛ ያለሆኑ አርሶአደሮች ታሰሩ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ ቺቦቼ ቀበሌ የእርሻ መሬታቸውን ለአበባ ልማት በሚል እንዲያስረክቡ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ ከ40 ያላነሱ አርሶአደሮች በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አርሶደሮቹ በአሁኑ ጊዜ ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የሜጫ ወረዳ በግብርና ምርቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአበባ እርሻ እየተባለ በርካታ አርሶአደሮች መሬታቸውን ...
Read More »ፑቲን ጦራቸው በዩክሬን ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱን ተናገሩ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሩስያው ፐሬዚዳንት ቭላድሜር ፒቲን ዩክሬን የሚገኘው ጦራቸው በአገሪቱ የሚገኙ ሩስያውያንን ከመጠበቅ ውጭ ምንም እርምጃ አለመውሰዳቸውን ለጋዜጠኖች ተናግረዋል፡፡ በአገሪቱ የሚገኙት ሩሲያውያን እርዳታቸውን ከጠየቁ፣ አገራቸው በዩክሬን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ግልጽ አድርገዋል። የሩሲያ ጦር የዩክሬንን ግዛት መውረሩን ተከትሎ በምእራባዊያን እና በሩሲያ መካከል ሰሞኑን የተፈጠረው ውዝግብ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ፑቲን በሩሲያ ላይ ...
Read More »ሼክ ሁሴን ሙሀመድ አላሙዲ በአለም 61ኛው ባለሃብት ተባሉ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዮጵያና ሳውድ አረቢያ ወላጆች የተወለዱት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን፣ በያዝነው አመት አጠቃላይ ሀብታቸው 15 ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ፎርቢስ መጽሄት ይፋ አድርጓል። ሼክ አላሙዲን በነዳጅ፣ በማእድንና በግንባታ ስራዎች ከፍተኛ ሀብት ማካበታቸው ተመልክቷል። ባለሀብቱ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢነቨስትመንት ያላቸው ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጠሩ በሚያስቀምጡዋቸው ቦታዎች መንግስት እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑ ...
Read More »12 ሺ ቶን ቡና በተጭበርበረ ሰነድ ወደ ውጭ አገር መላኩ ታወቀ
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በቡና አስተዳደር ላይ የሚታየውን ችግር አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ 12 ሺ ቶን ወይም 1 መቶ 20 ሺ ኩንታል ቡና በተጭበረበረ ሰነድ ወደ ውጭ ተልኮ መሸጡን አመልክቷል። ኮሚሽኑ ቡናው በማን በኩል ተሰርቆ እንደተላከ እያጣራ መሆኑን የዘገበው ሪፖርተር፣ የሽያጩ ገንዘብም ወደ አገር ውስጥ አለመግባቱን ገልጿል። ዛሬ ባለው የአለም ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት ከተመረጡ ጋዜጠኞች ጋር ሊነጋገሩ ነው
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታህሳስ 2006 መጨረሻ የኢትዮጵያ ፕሬስ እና የኢትዮጽያ ዜና አገልግሎት ድርጅቶች ያጠኑትና ሰባት የግል መጽሔቶች ላይ ያተኮረ ጥናት ይዘት ላይ የሚወያይና ከፍተኛ የመንግስት ባለልጣናት የሚገኙበት ለጋዜጠኞች የተዘጋጀ ስብሰባ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በአዳማ እንደሚካሄድ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የመንግስት ድጋፍ ያላቸው የጋዜጠኛ ማህበራት ከመንግስት የኮምኑኬሽን ጽ/ቤት ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት በተነገረለት ስብሰባ ላይ ከ100 በላይ የመንግስትና ...
Read More »