በኬንያ የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ መቱ

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአድማው መነሻ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተጣለውን አዲስ የፓርኪንግ ክፍያ ተከትሎ ነው። ባለ ታክሲዎቹ መኪኖቻቸውን ለማቆም ከፍተኛ የሆነ ከፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

ባለ ታክሲዎች ባደረጉት አድማ አብዛኛው ሰራተኛ ብእግሩ ስራ ለመግባት ተገዷል።

ባለስልጣናቱ በበኩላቸው እርምጃው በናይሮቢ የሚታየውን መጨናነቅ ለመቀነስ ነው ይላሉ።