የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነትና ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በአካባቢው ያለው አፈና እንዲቀንስ ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች እንዲፈቱ እንዲሁም ከቀያቸውና ከስራቸው የተፈናቀሉት ዜጎች ወደ ቦታቸውና ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ለመጠየቅ ትናንት ወደ አዲስ አበባ በማምራት ለጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤትና በፌደሬሽን ምክር ቤት ለ16ኛ ጊዜ አቤቴታቸውን ያቀረቡ የአገር ሽማግሌዎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት በየረር ባሪ ጎሳ አባላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የምክር ቤት ድጋፍ አገኙ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አብዲ ሞሀመድ ኦማር ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በጎሳው አባላት የተነሳውን ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ የሶማሊ ክልል አዲሱ ምክር ቤት ድጋፍ እንደሰጣቸው ታውቋል። ከክልሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ አብዲ የየረር ጎሳ አባላትን አልሸባብ እየተባለ ከሚጠራው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርገው በማቅረብ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ፈቃድ ...
Read More »የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ለሶስት አዳዲስ የንግድ የኤፍኤም ራዲዮ ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችለውን ጨረታ አወጣ፡፡
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጨረታው ለይስሙላ የወጣ መሆኑንና የሚሰጣቸው ሰዎች አስቀድመው የተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ባለስልጣኑ አስካሁን ራዲዮ ፋናን ጨምሮ ለአራት ያህል የንግድ ኤፍኤም ጣቢዎች ፈቃድ የሰጠ ሲሆን የረጅም ሞገድ ራዲዮ ጣቢያ እና የግል ቴሌቭዥን ጣቢያ ፈቃድ መስጠት በአዋጅ ቁጥር 533/1999 ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም እስካሁን ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኝነት ሳይታይበት ቀርቶአል፡፡ ባለስልጣኑ ባለፉት ...
Read More »ሳውድ አረቢያና ሌሎች የባህረ ሰላጤው ሃገራት ከግብጽ ጎን መቆማቸው ታወቀ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞውን የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲን በመደገፍና በእርሳቸው ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ጠንካራ አቋም የያዘችውን ካታርን በዲፕሎማሲ ዘመቻ ለማግለል ሳውድ አረቢያና ሌሎች የባህረ-ሰላጤው አገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከአገሪቱ አስወጥተዋል። አዲሱ የግብጽ መንግስት የካታር ልኡካኑን ያስወጣ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም ሳውድ አረቢያ፣ ባህሬንና ዩናይት አረብ ኤምሬትስ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል። የግብጽ የፖለቲካ አካሄድ የአረብ አገራትን እየከፋፈለ ነው። ...
Read More »አሜሪካ እና ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ የተራራቀ አቋም መያዛቸውን ፑቲን ተናገሩ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን ከአሜሪካው አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር ለ2 ሰአታት ከተወያዩ በሁዋላ ሁለቱ አገሮች በዩክሬን ላይ ያላቸው አቋም የተራራቀ መሆኑን ገልጸዋል። አሜሪካ፣ ሩሲያ የአለምን ህግ መጣሱዋን በመግለጽ ከዩክሬን ግዛት እንደትወጣና ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትመለስ ስትሻ፣ ሩሲያ በበኩሉዋ በዩክሬን የሚኖሩ ዜጎቼን ከጥቃት የመከላከል መብት አለኝ በማለት ህግ አለመጣሱዋን ትናገራለች። ክሪሚያ የምትባለው ...
Read More »የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ዜና እረፍት በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ስሜቶችን ፈጥሯል።
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ45 አመቱ ጎልማሳ አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ከቆየ በሁዋላ ትናንት አርፈዋል። የአቶ አለማየሁን እረፍት ተከትሎ የኦህዴድ አባላትና የክልሉ ነዋሪዎች ስለአሟሟታቸው ሚስጢር የተለያዩ መላምቶችን እያቀረቡ በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል። አብዛኛው ህዝብ ግለሰቡ በተቃዋሚዎቻቸው ተመርዘው መሞታቸውን በማመን የአሟሟታቸው መንስኤ እንዲታወቅ ይፈልጋል። የኦህዴድ አባላትም በጉዳዩ ላይ እየተወያዩ ሲሆን ...
Read More »ንግድ ሚኒስቴር ነጋዴዎች ለታክስ ህግ አይገዙም አለ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ.ም. በ ንግድ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ “አስመጪዎቹ ታክስን በሚመለከቱ ለወጡ ሕጎች ተገዢ ባለመሆን፣ የሚያስመጧቸውን ዕቃዎች ከዋጋ በታች ደረሰኝ በመቁረጥ፣ ያለ ደረሰኝ በመሸጥ፣ በሚቆርጡት ደረሰኝ ላይ የገዢን ማንነት አለመጥቀስ፣ ግዢን በሒሳብ ውስጥ አለማካታት፣ ከንግድ ትርፍ የሚገኝን ገንዘብ መሬት ውስጥ መቅበር፣ ወደ ውጭ አገር ...
Read More »በመንግስት የሚደገፉት የመጅሊስ አመራሮች እርስ በርስ እየተገማገሙ ነው
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደሚሉት በድሬዳዋ የተጀመረው በመንግስት የሚደገፈው የሙስሊም መሪዎች ግምገማ ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘቱ አመዝኖ ታይቷል። ከየክልሉ ተወክለው የመጡት መሪዎች አንዱ ሌላውን እንዲገልጽ በማስገደድ ጭቅጭቆች መፈጠራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አክራሪነትን ለመቋቋም በሚል ህዝባዊ ንቅናቄ እንደሚጀምር አስታውቋል። በዚህ ንቅናቄ የሃይማኖትና ፖለቲካ አክራሪዎችን በየቀበሌው ያለውን ህዝብ በመሳተፍ ለመወጋት ...
Read More »በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኘው ብአዴን የአቶ አለምነው መኮንንን ንግግር ለማስተባበልና ምንጩን ለማወቅ እየተዋከበ ነው
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ህዝብ ላይ ያዘነቡትን ጸያፍ ስድብ ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባው ብአዴን፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ በራሳቸው በአቶ አለምነው መኮንን እንዲሁም በብአዴን ሊቀመንበርና በምክትል ጠ/ሚንስትር ደመቀ መኮንን አማካኝነት መግለጫ ቢሰጠም፣ ህዝቡን ለማሳመን ባለመቻላቸው፣ በወቅቱ በስብሰባው ላይ የተገኙ ጋዜጠኞችና ሌሎች ተወያዮች ቀርበው አቶ አለምነው አልተናገሩም እያሉ እንዲያስተባብሉ እየተደረገ ...
Read More »አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን ሳያስረክቡ እንዳስረከቡ ተደርጎ የተነጠቁት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ታይላንድ ባንኮክ ውስጥ በጥብቅ የህክምና ክትትል ወይም (ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት) ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል። ግለሰቡ ያለመሳሪያ ድጋፍ በራሳቸው መተንፈስ እንደማይችሉ ፣ ሰዎችን እንደማያናግሩና በዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ እኩለቀን ላይ አንድ የሆስቲታሉ ሰራተኛ ለኢሳት ተናግረዋል። አቶ አለማየሁ ከኦህዴድ የምክር ቤት ...
Read More »