.የኢሳት አማርኛ ዜና

በመርዓዊ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናትና አርሶደአሮች ታሰሩ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ በእናሸንፋለን ቀበሌ በጨቦች ጎጥ  ለአበባ ምርት በሚል የከርሰ ምድር ውሃ ለማውጣት መንግስት እንቅስቃሴ መጀመሩን የተቃወሙ ቁጥራቸው ከ200 እስከ 300 የሚደርስ አርሶ አደሮች፣ እድማያቸው ከ9 እስካ 12 የሚደርስ ታዳጊዎች፣ ሴቶችና ወጣቶች በገፍ ተይዘው በመርዓዊ ከተማ እና በዱርቤቴ እስር ቤቶች መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ባለፈው ሃሙስ ፕሮጀክቱን የተቃወሙ አርሶደሮች ...

Read More »

በሻኪሶ ከ200 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች ታስረዋል ሲል አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ ሊግ አስታወቀ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኦሮምያ በጉጂ ዞን በሻኪሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ቁጥራቸው 200 የሚጠጋ ተማሪዎች በአዶላ ከተማ መታሰራቸውን ገልጿል። ብዙዎቹ ወጣቶች ከጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት እና ድብደባ መቁሰላቸውን ሊጉ ገልጿል። የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት እርምጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ሊጉ መንግስት እስረኞችን እንዲፈታ፣ ለቆሰሉት አስፈላጊው የህክምና ...

Read More »

የጨፌ ኦሮምያ የክልሉን መሪ ይመርጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ሲጀመር ባለፉት ተከታታይ ቀናት ለውይይት ቀርቦ የነበረውን ሪፖርት ያለምንም ተቃውሞ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሞት የተለዩትን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለመተካት አዲስ ፕሬዚዳንት የሚመርጥ ሲሆን፣ ካፒታል የተባለው በአገር ውስጥ የሚታተመው የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ቀድም ብሎ በሰበር ዜና የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ አስቴር ማሞ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚሾሙ ...

Read More »

የሃረሪ ሬዲዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም አዘጋጅ ታሰረ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ጀማል ዳውድ ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን፣ ለእስር የዳረገውም መልእክቶችን በሞባይል ስልክ ልኸሃል ተብሎ ነው። ይሁን እንጅ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች እንደገለጹት ጋዜጠኛ ጀማል የታሰረው በክልሉ ውስጥ የሚታየውን ዘረኝነት አጥብቆ በመቃወሙና ሌሎችን ጋዜጠኞች ታነሳሳለህ ተብሎ ነው። የክልሉ ፖሊስ አደገኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና የተዛባ ዜና በመጻፍ ወንጀል ለመክሰስ ...

Read More »

በሶማሊ ክልል ከ400 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር ሲወጣ ተያዘ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የደረሰው ዜና እንደሚያመለክተው ባለፈው ሳምንት ውጫሌ በሚባለው የጠረፍ ከተማ ላይ ከ400 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ በአይሲዙ መኪና ተጭኖ በህገወጥ መንገድ ሲወጣ በፌደራል ፖሊሶች ተይዟል። ሾፌሩና እና አብረው የነበሩ ሰዎች መጥፋታቸው ሲታወቅ ሁለት የፌደራል ፖሊሶች ገንዘቡን ለፌደራል መንግስት ለማስረከብ ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸው ታውቋል። ገንዘቡ የማን እንደሆነ ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

Read More »

የኬንያ መንግስት በአገሪቱ የሚገኙ የሶማሊያ ስደተኞች ወደ ካምፖች እንዲገቡ አዘዘ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኬንያ ይህን ህግ ያወጣችው የሶማሊያ ስደተኖች የጸጥታ ችግር ፈጥረውብኛል በሚል ነው። ሁሉም የሶማሊያ ስደተኞች ካኩማ እና ደደሃብ ወደሚባሉት የስደተኞች ካምፖች እንዲገቡ ይህን ባማያደረጉ ስደተኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መንግስት ገልጿል። አለማቀፍ ተቋማት ተቃውሞቸውን እየገለጹ ቢሆንም፣ የኬንያ መንግስት ግን በውሳኔው ለመጽናት የቆረጠ ይመስላል። በኬንያ በአልሸባብ የሚቀነባበሩ ፍንዳታዎች የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ ይታወቃል። አገሪቱ ...

Read More »

ለገጠሩ ወጣት የምንሰጠው መሬት ባለመኖሩ እየተሰደደ ነው ሲሉ አቶ ሃለማርያም ተናገሩ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይህን ያሉት ኢህአዴግ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ በገመገመበት ወቅት ነው። ስራ ፈጠራውም ሆነ ሳይታረሱ የኖሩትን ወል መሬቶችን እያደራጁ ለወጣቱ አርሶደአር መስጠት አላዋጣም ያሉት አቶ ሃይለ ማርያም ፣ በገጠር መሬት የማከፋፈል ስራ ከተሰራ በሁዋላ የምንሰጠው መሬት በማጣታችን ስራ ካገኘው  ይልቅ የተሰደደው ወጣት ይበልጣል ብለዋል፡፡ አቶ ...

Read More »

መንግስት በእስልምና ትምህርት ቤቶች ውስጥ ህገመንግስት ለማስተማር ሞክሮ እንደነበር ገለጸ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ለዲፕሎማቶች እና ለሚኒስትሮች በተሰጠው ስልጠና ላይ እንደተገለፀው እስላማዊው መጅሊስ እራሱን የመምራት አቅም አልነበረውም ተብሎአል፡፡ ቀድሞ የነበረው መጅሊስ ሰነፍ የነበረና የራሱን ትምህርት ቤት ለመምራት ብቃት ያለነበረው ነው ያሉት የመንግስት ከፍተኛው ባለስልጣን፣ መጅሊሱ ብዙ ስህተቶችን ፈጽሟል ብለዋል። መጅሊሱ ያስመጣቸው የተለያዩ የውጭ ሰዎች ማስተማር ሲጀምሩ ወጣት ኢስላሚስቶቹ ተንጫጩ ያሉት ...

Read More »

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ልማት ሕዝብን ተጠቃሚ የማድረጉ ጉዳይ በሕዝብ ጥያቄ እንደተነሳበት አንድ ጥናት አመለከተ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በአዋጅ በፈረሰ ስያሜ የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት አዲስአበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች አደረግነው ባሉት ጥናት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው ልማት አብዛኛውን ሕዝብ ተጠቃሚ የማድረጉ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ እምነት አለኝ ያለው ሕዝብ እጅግ አነስተኛ መሆኑን አመለከቱ፡፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንትና ዕትም የፊት ገጽ ላይ “ዜጎች የኢኮኖሚ ዕድገቱ በመንግስትና ሕዝብ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ይሰልላል ተባለ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ይሰልላል ብሎአል። ድርጅቱ ባወጣው ባለ 100 ገጽ ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለስርአቱ አደገኛ ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን  በውጭና በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎችን ለመሰለል ከተለያዩ አገሮች ቴክኖሎጂዎችን ማስገባቱን ” ገልጿል። የመንግስት ድርጊት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ በነጻነት ...

Read More »