.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአዲስ አበባ ህዝብ ለቀረበት ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አንድነት ፓርቲ ጠየቀ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በህገ ወጥ መንገድ የሚቀለበስ ሰላማዊ የትግል ስልት ባለመኖሩ የአዲስ አበባ ህዝብ ለቀረበለት የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ምላሹን እንዲሰጥ ጠይቋል። የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ህገ ወጥ ደብዳቤ በመጻፍ ሰልፉን ማከናወን አትችሉም ማለቱ ከህግ በላይ መሆኑን እንደሚያሳይ ፓርቲው ገልጿል። መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ...

Read More »

የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ውሎ የተከሳሾችን ጥንካሬ ያሳየ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተከሳሽ ቃላቸውን በመስጠት ላይ ያሉት የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በፍርድ ቤቱ ውስጥ የሚያሰሙት ንግግር የብዙዎችን ታዳሚዎች ቀልብ እየሳበ መምጣቱን እና በእስረኞች ላይ የሚታየው ጽናት የሚያስገርም መሆኑን ችሎቱን የሚከታተሉ ታዳሚዎች ገልጸዋል። ትናንት ቃላቸውን የሰጡት የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ የሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ  ትግል በዝርዝር አቅርበዋል። በእስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን በደልም የታዳሚውን ስሜት ...

Read More »

በካይሮ የፖሊስ አዛዡ ተገደሉ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግብጽ የካይሮ ዩኒቨርስቲ አካባቢ በፈነዱ 3 ቦንቦች  አንድ የፖሊስ አዛዥ ሲገደሉ ሌሎች አምስት ሰዎችም ቆስለዋል።የጥቃቱ አላማ በፖሊሶች ላይ ማነጣጠሩን የሃገሪቱ ቴሌቪዥን ገልጿል። የእስላማዊ ወንድማማቾች ፓርቲ ህገወጥ ተብሎ እንዲፈርስ ከተደረገና የፓርቲው ሊቀመንበርና ከዚሁ ፓርቲ በመውጣት ግብጽን ሲመሩ የነበሩት ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ከታሰሩ በሁዋላ በግብጽ ተደጋጋሚ ፍንዳታዎች እየደረሱ ነው፡፡ ወታደራዊ ስልጣናቸውን የለቀቁት ፊልድ ...

Read More »

የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመታረቅ ከፈለገ ከጉያችን ያሉ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ምን ይሆናሉ ብለን አንሰጋም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ጌታቸው አረዳ እንደተናገሩት ” የኤርትራ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ሰላም ቢመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የለበትም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከጉያችን ስላሉ ምን እንሆናለን የሚል ስጋት የለብንም” በማለት ተናግረዋል። የታጠቁ የኤርትራ ሃይሎች እርምጃ የማይወስዱት በድንበር አካባቢ የኤርትራ ሰራዊት በብዛት ስላለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ የኤርትራ ...

Read More »

ውሃ ፣መብራት፣ቴሌ አሁንም ሕዝቡን እያስመረሩት ነው

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የመጠጥ ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቆራረጥ በያዝነው መጋቢት ወር ተባብሶ በመቀጠሉ ነዋሪዎች ለአላስፈላጊ ኪሳራ ከመዳረጋቸው ጋር ተያይዞ በነዋሪው ዘንድከፍተኛ ምሬት መፍጠሩን ዘጋቢያችን ገልጿል። በያዝነው  ወር የኤሌክትሪክ ኃይል ቢያንስ በሁለት ቀን አንድ ጊዜ ለሰዓታት የሚጠፋበት ሁኔታ በተደጋጋሚ መስተዋሉን ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን በዚህም ምክንያት ለአንድ ፍሬ ...

Read More »

በሀረር የታሰሩ ሰዎች በዋስ እንዲለቀቁ ቢወሰንም ፖሊስ እንደማይለቅ አስታወቀ

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በከተማዋ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የታሰሩ 7 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲለቀቁ ዳኛ የሱፍ ውሳኔ ያስተላለፉ ቢሆንም፣ እስረኞቹ አስፈላጊውን ክፍያ ከፈጸሙ በሁዋላ ከእስር ለመውጣት ሲዘጋጁ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ክንፈ አብዱል ፈታ ” ፍርድ ቤት አቃቢህግና መርማሪ ፖሊስ ባልተገኘበት ሁኔታ ስለሆነ ውሳኔ ያስተላለፈው አትፈቱም” በማለቱ ዛሬ መለቀቅ የነበራቸው እስረኞች ሳይለቀቁ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን አማጽያን የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶችን እንደሚቆጣጠሩ አስታወቁ

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ ማህበረሰብ አማጽያኔኑን ከመንግስት ጋር ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል ቢከርምም ፣ አማጽያኑ ግን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን ከስልጣን አስገድዶ ለማውረድ ሲሉ የነዳጅ ማውጫ ቦታዎችን ለመቆጣጠር መወሰናቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ነጭ ጦር እየተባለ የሚጠራው ከአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻር ጋር ጥምረት ያለው ቡድን ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኘውን የ ፓሎችን የነዳጅ ጉድጓዶች ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረ ነው። ማቻር ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የአንድነት ፓርቲን የሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከንቲባ ጽህፈት ቤቱ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎች ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ ለፓርቲው በጻፉት ደብዳቤ ” የአዲስ አበባ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነስርአት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ  የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ” አልተቀበንነውም ብለዋል። የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ...

Read More »

በጉጂና በቦረና መካከል የተፈጠረውን ግጭት የአገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተው ማብረዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ20 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሞት ምክንያት የሆነውን በጉጂ ዞን የተከሰተውን የጎሳ ግጭት ለማስቆም የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎች ወደ አካባቢው ተንቀሳቀስው የሁለቱን ጎሳዎች ሰዎች ካነጋገሩ በሁዋላ ላለፉት 4 ቀናት የተካሄደው ግችት ሊቆም ችሎአል። ምንም እንኳ ግጭቱ ቢቆምም ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው። ለግጭቱ መነሳት ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የአካባቢው ባለስልጣናት እስካሁን ተጠያቂዎች አለመሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ...

Read More »

በሀረር ከተማ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ድበደባ እየተካሄደባቸው ነው

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስር ቤት ምንጮች እንደገለጹት በሀረር ከደረሰው ተደጋጋሚ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተቃውሞቸውን አሰምተዋል በሚል የታሰሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፌደራል ደህንነት መርማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ እየተካሄደባቸው ነው:፡ ፖሊስ ጋራጅ ውስጥ የታሰሩት ወጣቶች ከምግብ ተከልክለው ከዘመድ እንዳይገናኙ ተደርገው ” እመኑ” በሚል ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው። ታከሉ ሙላቱ፣ ታገሰ ሙላቱና አዳነ የሚባሉ የጫማ ንግድ ድርጅት ባለቤቶች ...

Read More »