.የኢሳት አማርኛ ዜና

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስርዓቱን በብዛት እየከዱ ነው

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት ባለፉት 20 ቀናት ብቻ ከባድሜ ግንባር ከ 107 ያላነሱ ሰዎች ከድተው ወደ ኤርትራ እና ወደ መሃል አገር አቅንተዋል። ከ15 ቀናት በፊት በባድሜ አካባቢ ሲያጎ በተባለው ቦታ ላይ የሰፈሩ 60 የ 33ኛ ክፍለጦር አባላት በአንድ ሌሊት ሰራዊቱን ጥለው የጠፉ ሲሆን፣ ኤርትራ መድረስና አለመድረሳቸውን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ወታደሮቹ የጠፉት በክፈለጦሩ ...

Read More »

በየረር ባሬ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከታሰሩት የአገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ አረፉ

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በየረር ባሪ ጎሳዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት 19 አገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ በእስር ቤት ውስጥ ማረፋቸው ታውቋል። የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች አስከሬን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሟቾቹን በራሳቸው ጊዜ በመቅበራቸው የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሞ አስነስተዋል። ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ የክልሉ ፕሬዚዳንት ልዩሚሊሺያዎችን ወደ አካባቢው በመላክ ላይ እያሉ ፣ ከአዲስ አበባ በተላለፈ ትእዛዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ፈጥኖ ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ አወገዙ

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ቁጥር ያላቸው በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጆሃንስበርግ ተነስተው የእንግሊዝ ቆንስላ ወደሚገኝበት ፕሪቶሪያ በማምራት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ ከእነሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘችው ዝናሽ ሃብታሙ  ኢትዮጵያውያኑ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ነጻ እናወጣለን ማለታቸውን ገልጻለች በሌላ በኩል ደግሞ በአገር ቤት ...

Read More »

አንድነትና መኢአድ የውህደት ቀናቸውን በሁለት ሳምንት አራዘሙ

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ   የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አስታውሰው፣ ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ...

Read More »

የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት እንደገና ተራዘመ

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል። በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት ሂደቱ በሰባሰብ እንዲራዘም የተደረገው። ዳኞችና አቃቢ ህጎች በቃሊቲ የሚገኘው የችሎት አዳራሽ ለትራንስፖርት የማያመች በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ባመለከተቱት መሰረት አዲሱ ችሎት ሲ ኤም ሲ ሰሚት ...

Read More »

የኤድስ ስርጭትን  እኤአ እስከ 2030 ማቆም እንደሚቻል ተመድ ገለጸ

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣ ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ  ማቆም እንደሚቻል ገልጿል። አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተይዘዋል። በአጠቃላይ ...

Read More »

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር “የሚመለከታቸው አካላት ካልፈቀዱ በስተቀር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት እንደማይቻል” ገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለእንግሊዝ የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ በጻፈው ደብዳቤ፣ አቶ አንዳርጋቸው የህግና የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ” የሚመለከታቸው አካላት” መፍቀድ አለባቸው ብሎአል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ” የሚመለከታቸው አካላት” ያላቸውን አካላት በስም ከመጥቀስ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የመረጃው ምንጮች እንደሚሉት ” የሚመለከታቸው አካላት” የተባሉት የደህንነት ሰዎች ናቸው። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ይህን መልስ የጻፈው፣ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ...

Read More »

የደብረ ታቦር ህዝብ በባለስልጣናት መማረራቸውን ገለጹ 

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የከተማው እና የዞኑ አመራር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ኗሪዎች በመሰረተ ልማት ፤ በመልካም አሰተዳደር ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ አለም ደጉ የተባሉ የደብረ ታቦር ኗሪ ” የጋማ ከብት እና ሰዎች በአንድ ላይ እየጠጡ መሆናቸውንና ይህም ሁኔታ ለውሃ ወለድ በሺታ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ፍስሃ ይ መር  የተባሉ ነዋሪ የማትረባ ፍየል ...

Read More »

የአዲስ አበባ ቴልኮም ማስፋፊያ ስራ በተያዘለት የጊዜ ገድብ ሊፈጸም አልቻለም

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮ ቴሌኮም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ፈሶበት  በሥራ ላይ የነበረውን የኖኪያ ኔትወርክ ነቅሎ በመጣል በቀላሉ ለስለላሥራ በሚመች መልኩ በአዲስ መልክ ለመትከል በቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ እየተከናወነ ያለው የአዲስ አበባ የቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማሳካት አለመቻሉን  ምንጮቻችንገልጸዋል፡፡ ሁዋዌ በ800 ሚሊየን ዶላር በያዝነው ዓመት ህዳር ወር 2006 የማስፋፊያ ስራውን በአዲስ አበባሲ ጀምር በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ...

Read More »

እስራኤል በጋዛ ላይ ያቋረጠችውን ድብደባ እንደገና ጀመረች

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃማስና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት ፣ በግብጽ አደራዳሪነት ለሰአታት ጋብ ብሎ የቆየ ቢሆንም፣ እስራኤል ድብደባውን እንደገና መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል። በግብጽ የቀረበውን የሰላም ስምምነት እስራኤል ብትቀበለውም፣ ሃማስ ግን ስምምነቱ ሽንፈትን እንደመቀበል ይቆጠራል በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል። ይህን ተከትሎም እስራኤል የአየር ድብደባውን እንደገና ጀምራለች። እስካሁን በደረሰው ጥቃት ከ192 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትም ቆስለዋል። በእስራኤል በኩል ...

Read More »