የአዲስ አበባ ቴልኮም ማስፋፊያ ስራ በተያዘለት የጊዜ ገድብ ሊፈጸም አልቻለም

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮ ቴሌኮም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ፈሶበት  በሥራ ላይ የነበረውን የኖኪያ ኔትወርክ ነቅሎ በመጣል በቀላሉ ለስለላሥራ በሚመች መልኩ በአዲስ መልክ ለመትከል በቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ እየተከናወነ ያለው የአዲስ አበባ የቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማሳካት አለመቻሉን  ምንጮቻችንገልጸዋል፡፡

ሁዋዌ በ800 ሚሊየን ዶላር በያዝነው ዓመት ህዳር ወር 2006 የማስፋፊያ ስራውን በአዲስ አበባሲ ጀምር
በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የተሰጠው ምክንያት ጥራቱን በ4 ጂ ደረጃ ለማሻሻል እና በአዳዲስ አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስፋፋት የሚል እንደ ነበር ምንጮቹ አስታውሰው ፣ ዋናው ምክንያት  ከተማዋን በቀጠና በመክፈል የዜጎችን የሞባይል ስልኮች እና የኢንተርኔት አገልግሎት ለመሰለል ታቅዶ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

መንግሥትየገዛዜጎቹንለመሰለልእንዲያመቸውየክልሎቹንማስፋፊዎችጨምሮ 1 ነጥብ 6 ቢሊየንዶላርየሚከፍል ሲሆንለጊዜውስራየተጀመረውበአዲስአበባብቻመሆኑታውቋል፡፡

የአዲስ አበባው ፕሮጀክት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ሙሉበሙሉተጠናቆየተሻለ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ይሰጣልተብሎተነግሮየነበረ ቢሆንም ሁዋዌኩባንያ የጀመረውሥራባለመሳካቱሌላውቀርቶከወራትበፊት የነበረውንደካማኔትወርክናየኢንተርኔትአገልግሎትመልሶማግኘትየማይቻልበትሁኔታተፈጥሮአል፡፡

ከዚሁ ማስፋፊያሥራጋርተያይዞእንደባንክ፣አየርመንገድ ፣ ትኬት ቢሮዎች በየእለቱ ኔት ወርክ ባለመኖሩ ምክንያት ሥራቸውን ለማከናወን አለመቻላቸውን ፣ነጋዴዎችን ገቢና ወጪ ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ንግድ

ሥራቸው መታወኩንበመናገርላይናቸው፡፡

አንድተጠቃሚለዚህ ዘጋቢእንዳለው «ኢ ቪዲዮየሚባለውንአንተርኔትአያይዘህአንድደቂቃሳትጠቀምተመልሶይቋረጣል፣ እንደገናታገናኛለህ፣እንደገናይቋረጣል፡፡ገንዘብህበዚህመልክእየተዘረፍክሹምምንቶቻችንግንቴሌ የምትታለብላምናትእያሉበአደባባይይደሰኩራሉ» ብሎአል፡፡

ኢትዮ ቴልኮም የኔትወርክችግሮቹንበሙሉከኤሌክትሪክሃይልመቋረጥጋርያያይዛቸዋል።

ኢትዮጵያየዜጎቹዋንየቴሌኮምግንኙነትበመሰለልከሚታወቁጥቂትየዓለማችንአገራትአንዱዋመሆንዋበዓለም አቀፍተቋማትጭምርመረጋገጡየሚታወስነው፡፡