የደብረ ታቦር ህዝብ በባለስልጣናት መማረራቸውን ገለጹ 

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የከተማው እና የዞኑ አመራር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ኗሪዎች በመሰረተ ልማት ፤ በመልካም አሰተዳደር ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህ አለም ደጉ የተባሉ የደብረ ታቦር ኗሪ ” የጋማ ከብት እና ሰዎች በአንድ ላይ እየጠጡ መሆናቸውንና ይህም ሁኔታ ለውሃ ወለድ በሺታ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ፍስሃ ይ መር  የተባሉ ነዋሪ የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሱዋም ትሞታለች እንደተባለው ኢትዩጰያም ሞታለች  ደብረ ታቦርም ሞታለች በማለት የኑሮ ውድነት የፈጠረውን ጫና ተናግረዋል

ያምሮት አሰፋ የተባሉ እናት ደግሞ ” እኔን የሚበድለኝ የቀበሌ ሹም ነው፡፡እኔ ገንዘብ እንዳልሰጥ ፣ ቢራ እንዳላጠጣ ድሃ ነን ፤ ካርታ እና ፕላን እያለኝ ለባለሃበት የሚፈርድ መንግስት በመሆኑ መሬቴን ተቀምቻለሁ ብለዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የሚዲያ አካላት በተገኙበት የከተማው እና የዞኑ አመራር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ አቶ ሲሳይነው ተስፋ የተባሉ ኗሪ

“24 ስዓታት የመንቀሳቀስ መብት የለንም፣ ከምሺቱ ሶሰስት ስዓት በኃላ በልዩ ሃይል ፖሊስ እንደበደባለን፡፡ መለሰ አካደሚ እና ፋውንዴሺን ከአበል እና  ከደሞዝ እየተጠቆረጠ በግዴታ ያለፍላጉታችን ይወሰድብናል፡፡

ይህንንም ያልፈፀመ አሸባሪ ይባላል” ሲሉ ተናግረዋል።

ብአዴን በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ለሚቀጥለው ምርጫ እንዲደራው ህዝቡን እያወያየ ቢሆንም፣ ህዝቡ ግን በስርአቱ መማረሩን ከመግለጽ አልተቆጠበም።