በየረር ባሬ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከታሰሩት የአገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ አረፉ

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በየረር ባሪ ጎሳዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት 19 አገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ በእስር ቤት ውስጥ ማረፋቸው ታውቋል።

የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች አስከሬን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሟቾቹን በራሳቸው ጊዜ በመቅበራቸው የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሞ አስነስተዋል። ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ልዩሚሊሺያዎችን ወደ አካባቢው በመላክ ላይ እያሉ ፣ ከአዲስ አበባ በተላለፈ ትእዛዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ፈጥኖ በመንቀሳቀስ ልዩ ሚሊሺያውን አግቶ አስቁሞታል። ሚሊሺያውም

ወደ ጅጅጋ እንዲመለስ መደረጉን ለማወቅ ተችሎአል። ይክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ፣ እርሳቸው የሚያዙት ሚሊሺያ በመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ትእዛዝ ወደ መጣበት እንዲመለሱ መደረጋቸው

ያበሳጫቸው ሲሆን፣ እስካሁን ግን ይህ ነው የሚል መልስ አልሰጡም። በክልሉ ፕሬዚዳንትና በተለይም በደህንነት ሚኒስትሩ  ጌታቸው አሰፋ መካከል የተፈጠረው ልዩነት እርስ በርስ እስከ መዘላለፍና

መካሰስ አድርሷቸዋል። አቶ አብዲ የክልሉን የደህንነት ሃላፊ የህወሃቱን መቶ አለቃ አወጣሃኝን ካሰሩ በሁዋላ ልዩነቱ እየሰፋ ሄዷል። አቶ አብዲም በቅርቡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው ከእንግዲህ

የደህንነት ሃይሎችን እንዳይፈሩዋቸው፣ በክልሉ ያሉት ብቸኛ ሰው እርሳቸው መሆናቸውን መናገራቸውን መዘገባችን ይታወቃል።

የህወሃት ባለስልጣናት አቶ አብዲን ለመተካት ፈተና እንደሆነባቸው እየተነገረ ነው። አቶ አብዲ በክልሉ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ባላቸው ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ይደገፋሉ። ይሁን እንጅ በቅርቡ

አልሸባብ ኦጋዴን ውስጥ ገብቶ 33 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን ተከትሎ የመከላከያና የአገር ውስጥ የደህንነት ሃይሉ ፣ ጣታቸውን በአቶ አብዲ ላይ መቀሰር ጀምረዋል።