.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአዲስ አበባ ከንቲባ የከተማዋን የጸጥታ ጉዳይ ለኦሮምያ ምክር ቤትም ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባንና የኦሮምያን የጸጥታ ሁኔታ ለማስተሳሰር፣ የኦሮምያን ልዩ ሃይልና የፌደራል ፖሊሶችን በጋራ በአዲስ አበባ ለመጠቀም ሲባል፣ መስተዳድሩ የጸጥታ ጉዳዮችን ለጨፌ ኦሮምያም ጭምር ሪፖርት እንዲያደርግ ታዟል። የእቅዱ ዋና ነዳፊ የሆኑት የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አባይ ጸሃየ፣ ጸጥታን በተመለከተ የኦሮምያ ምክር ቤት ሪፖርት እንዲቀርብለት፣ የልማት ጉዳዮችን በተለይ መሬትን በተመለከተ ደግሞ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሪፖርት እንዲቀርብለት ...

Read More »

እንግሊዝ ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ማቋረጡዋን አስታወቀች

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉምበርግ የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እንግሊዝ በኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመደጎም ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ያቋረጠችው፣ መንግስት መጪውን ምርጫ ተከትሎ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን ማሰሩንና መዋካቡን በመቀጠሉ ነው። የእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ጸሃፊ ጀስቲን ግሪኒንግ ፣ እንግሊዝ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑዋን ተከትሎ፣ ቀድም ብሎ ይሰጥ የነበረው የማህበራዊ አግልግሎት ድጋፍ እንደተቋረጠ ለእንግሊዝ ከፍተኛው ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን ራሳቸውን ከምርጫ ክርክር አገለሉ

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአለማቀፍ ታዛቢዎችና በኢትዮጵያውያን በቂ ትኩረት ያልተሰጠውን የግንቦት 16 ቀን 2007 ምርጫ ክርክር የሚሳተፉለትን መሪዎች ሲያፈላል የነበረው ኢህአዴግ፣ ለመጀመሪያው ዙር የክርክር መድረክ የሚሆኑትን ሰዎች ሲመርጥ፣ አቶ በረከት ራሳቸውን አግልለዋል። ኢህአዴግ 23 አመራሮችን ለክርክር በእቅድ የያዘ ቢሆንም፣ ከእነዚህ ወስጥ በመጀመሪያው ዙር መጣሪያውን ያለፉት አቶ  ሬዲዋን ሁሴን  እና አቶ ደሰታ አስፋው ብቻ ናቸው። 21ዱ አመራሮች ...

Read More »

በአማራ ክልል የተሰሩ የገጠር መንገዶች ጥራት ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ችግሩን አምኗል፡፡

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓም. በሚቆየው የአማራ ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በቀረበው  የግማሽ አመት ሪፖርት፣  ከየዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት በቀረቡት ጥያቄዎችንና ቅሬታዎች በክልሉ በተገነቡ የገጠር መንገዶች አሰራር ላይ ተገቢው ክትትልና ቁጥጥር ባለመደረጉ መንገዶች ተገቢውን ...

Read More »

በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ህዝብ በውሃ እና መብራት ማጣት እየተሰቃየ ነው

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳው ውሃ ከ15 ቀን በላይ በመጥፋቱ ከጉረቤት ቀበሌያት እየተቀዳ የሚመጣው ንፅህናው ያልተጠበቀ አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 10 ብር እየተሸጠ ሲሆን ፣  ይህንኑ ውሃ በአህያ ጋሪ ከተማ ውስጥ ለመግዛት ነዋሪዎች ቀድመው ለመክፈል ይገደዳሉ ። አንዲት የጪኮ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችና በሰው ቤት የቀን ስራ ሰርታ የምትተዳደር ሴት  ” እቤቴ የአንድ አመት ልጅ አለኝ ልጄ ...

Read More »

የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በዋሽንግተን ዲሲ  ለደረሰባቸው የኢትዮጰያውያን ተቃውሞ የብልግና ምላሽ ሰጡ።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠማቸው። ፕሬዚዳንቱ በተገኙበት ሆቴል የተገኙ ኢትዮጰያውያን ፦” ሰውዬው እጃቸው በደም የተጨማለቀ፣ የሱማሌ ክልል ወጣቶችን በመግደል በዘር ማጥፋት ክስ የተመሰረተባቸውና  እና ለዚህም  በዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ የሚገባ  ወንጀለኛ መሆናቸውን በማውሳት ከፍ ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል። በደረሰባቸው ድንገተኛ ተቃውሞ  የተበሳጩ የመሰሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት ...

Read More »

በኢትዮጰያ ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰልፎች  ቢታገዱም ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች መግለጹን ቀጥሏል።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች  የሚገኙ ግድግዳዎችና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በየእለቱ “ጭቆና በቃን! ነጸነትና ፍትህ እንፈልጋለን!  ለነጸነት ትግል ተነስ!” በሚሉ መፈክሮች አሸብርቀው መታየታቸው የተለመደ ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ  እነኚሁ  የፍትህና  የነጻነት ጥያቄዎች በመገበያያ የብር ኖቶች ላይ ሳይቀር በስፋት  እየተስተዋሉ መሆናቸው  የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሂደቱ በዚህ ከቀጠሉ  የብር ኖቶች በሙሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመፈክር ጽሁፎች ...

Read More »

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ መንደር  ነዋሪዎች በውሀ፣ በመብራትና በስልክ ችግር ክፉኛ እያማረሩ ነው።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎቹ  ምሬታቸውን ለኢሳት ሲግልጹ፦” አቶ ሀይለማርያምን  ከልባችን አውጥተን ከጣልነው ቆይተናል” ብለዋል። በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን   የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ የሆነችው  የአረካ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት  በጠቅላላ የወላይታ ዞን  ነዋሪዎች በውሀ፣በመብራትና በስልክ ችግር  መማረር ከጀመሩ ረዥም ጊዜያት ሆኗቸዋል። በተለይ ካለፉት ሁለት ወራት  ወዲህ የአቶ ሀይለማርያም የትውልድ መንደር በሆነችው  በአረካ አገልግሎቱ ጠቅላላ የቆመበት ...

Read More »

የኢትዮጰያ መንግስት  በተያዘው ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች እርዳታ  እንደሚያስፈልገው ማሳወቁን ተመድ ገለጸ።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመድ የመንግስትን ሪፖርት ዋቢ አድርጎ ባወጣው መግለጫ ዘንድሮ  በኢትዮጰያ 2.9 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። ከተረጅዎቹ መካከል 38 በመቶው  ከኦሮሚያ፣ 31 ከመቶው ደግሞ ከሶማሌ፣ 12 በመቶው ከትግራይ እና 6 በመቶው ካማራ ክልሎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል። ለተረጅዎቹ ድጋፍ ለማድረግ  386 ሚሊዮን ዶላር  እንደሚያስፈልግ ያመለከተው ተመድ፤ ይሁንና  የረድኤት ድርጅቶች የፈንድ እጥረት እንዳለባቸው ...

Read More »

መንግስት- የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት  አባላት  ናቸው ባላቸው ሁለት  የመቀሌ ነዋሪዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መሰረተ

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን ሲመለምሉና  መንግሥትንና ተቋማቱን ሲሰልሉ  ተደርሶባቸዋል፣ እና  የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምሕት)  ቡድን ምልምሎች  ናቸው>>  ባላቸው ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሠረተ፡፡ <<የወንጀሉ ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር>> ተብለው  ክስ የተመሠረተባቸው፣ ነዋሪነታቸው በትግራይ ክልል ...

Read More »