ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ 2000 ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም -ቀራኒዮ ተራራ ላይ የተሰቀለበት እለት በመላው ዓለም በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ሲከበር ውሏል። ስቅለት፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የክርስቶስን ህማምና ስቃይ በሚያስታውስ መልኩ በተለየ ሀይማኖታዊ ሥር ዓት የሚከበር ታላቅ በዓል ሲሆን፤ እለቱን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያኖችን ከየመን ወደ አገራቸው ለመመለስ የበረራ ፈቃድ እየጠበቀ መሆኑን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእንግሊዝኛ IOM በመባል የሚታወቀው ድርጅት ባወጣው ዘገባ በሚቀጥሉት ቀናት ከየመን ሰንአ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ካርቱም ተከታታይ በረራዎችን ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ የበረራ ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ነው። አይ ኦ ኤም የበረራ ፈቃዱን የሚጠይቀው ከማን እንደሆን አላስታወቀም። ምን ያክል ኢትዮጵያውያን ለመመለስ ፈቃደኛ መሆናቸውንም አላስታወቀም። ይሁን እንጅ በየመን የሚገኙ ስደተኞች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል። ድርጅቱ ...
Read More »የጦር መሳሪያ ሽያጭ መጧጧፉ ተሰማ
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጧጡፎ በመሸጥ ላይ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። በአለፋ ፣ ጣቁሳ፣ መተማ፣ አርማጭሆ፣ ቋራና በሌሎችም በርካታ ወረዳዎች አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ45 ሺ እስከ 60 ሺ ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጦር መሳሪያዎችን በብዛት የሚገዙት አርሶ አደሮች ናቸው። በርካታ ቁጥር ያለው የኢህአዴግ ወታደር በጠረፍ ከተሞች ...
Read More »በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን ለማጥናት 2 ኩባንያዎች ተመረጡ
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በቅርቡ በአባይ ውሃ አጠቃቀምና በአባይ ግድብ ዙሪያ የስምምነት መርሆዎችን በተፈራረሙት መሰረት የግድቡን ውሃ አሞላል እንዲሁም ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ ስለሚያስከትለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖ ጥናት የሚያደርግ ገለልተኛ ኩባንያ ለመምረጥ በተስማሙት መሰረት የፈረንሳይ እና የሆላንድ ኩባንያዎች መመረጣቸው ታውቋል። የፈረንሳዩ ቢአር ኤል ኢንጂነሪንግ የውሃ አሞላሉን የግድቡን ኢንጂሪንግ ስራዎች ሲያጠና የሆላንዱ ዴልታ ራይስ ...
Read More »በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ወክባ እየተፈጸመ ነው ተባለ።
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ እንደገለጸው፤ቀደም ካለ ጊዜ አንስቶ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እስረኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽም የቆየው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ሰሞኑን ደግሞ በከሰዓቱ የእስረኞች መጠየቂያ ክፍለ ጊዜ ጠያቂ እንዳይገባላቸው እገዳ ጥሏል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ይህን እገዳ የጣለው ከኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወላጅ እናት ማረፍ ጋር በተያያዘ በርካታ ህዝብ ሀዘኑን ለመግለጽና ለማፅናናት ወደ እስር ...
Read More »በአዲስአበባ የኤሌክትሪክና ውሃ መቆራረጥ ተባብሶ ቀጥሎአል
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና የመጠጥ ውሃ መጥፋት ባሳለፍነው ሁለት ሳምንታት ተባብሶ መቀጠሉ ህብረተሰቡን ለተለያዩ ወጪዎችና እንግልት እየዳረገ መሆኑንና በዚህ ጉዳይ መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ ማመን የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በተለይ ባለፈው ሳምንት እና በያዝነው ሳምንት የኤሌክትሪክ ኃይል ለረጀም ሰዓታት እንደሚጠፋ ተናግረዋል፡፡ በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጡ በአንድ ጊዜ ...
Read More »በዞን 9 ጸሃፊዎች ላይ ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም ተባለ
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ ዞን 9 በመባል በሚጠሩት ወጣት ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የመንግስት አቃቢ ህግ ጠንካራ ማስረጃ ለማቅረብ አለመቻሉን ጠበቃውን አቶ አምሃ መኮንንን በመጥቀስ ዘግቧል። በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 6 የዞን ዘጠኝ እና 3 ጋዜጠኞች ላለፉት 10 ወራት በእስር ላይ ከቆዩ በሁዋላ፣ ፍርድ ቤቱ በቅርቡ ምስክሮችን የመስማት ሂደቱን ጀምሯል። ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው ሂደት የቀረቡት ምስክሮች ጸሃፊዎችና ...
Read More »የዘይት ክፍፍል ስሌቱ በወር ለአንድ ሰው ሩብ ሌትር ነው ተባለ
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችንን ሰሞኑን ለአማራ ክልል የሚሰጠውን የዘይት ክፍፍል መሰረት አድርጎ በላከው ዘገባ ለ20 ሚሊዮን ህዝብ በወር የተመደበው ዘይት 4 ሚሊዮን 800 ሺ ሊትር ነው። ለክልሎች የሚከፋፈለው ዘይት በህዝብ ቁጥር ልክ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አጠቃላይ ስሌቱ ለአንድ ሰው በወር ሩብ ሊትር ዘይት መሆኑን ጠቅሷል። የክፍፍሉ መጠን ዘይት ባለበት ጊዜ የተሰላ ሲሆን፣ የዘይት አቅርቦት በማይኖርበት ጊዜ ...
Read More »በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሰዎች ፍትህ አጥተው በእስር ላይ ናቸው
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከሁለት አመታት በፊት ጀምሮ የተነሳውን የማንነት ጥያቄ መርታችሁዋል በሚል የተያዙት ከ150 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍርድ ሳይሰጣቸው በአርባ ምንጭ እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ናቸው። ፍትህ አጥተው ከታሰሩት መካከል አንድ ሰው በህክምና እጦት ህይወቱ ማለፉን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአካባቢው የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል። ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ...
Read More »የመንግስት አመራሮችና ጋዜጠኞች ከውጭ እና ከውስጥ የሚለቀቀውን ፕሮፖጋንዳ እንዲያከሽፉ አደራ ተጣለባቸው
መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ኢህአዴግ የኒዮ ሊበራል አፈቀላጤ የሚላቸውን እነ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማንራይት ዎች እና ሲፒጄ የሚያወጡትን መግለጫ ነቅቶ በመጠበቅ አፍራሽ ጎናቸውን እንዲያጋልጡ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት፤ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን አዘጋጆችና አመራሮች ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ከምዕራባዊያን ሀገራት የሚፈልቁ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳዎችን በማጋለጥ ጋዜጠኞች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ...
Read More »