ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሬውተርስ የግብጽ መንግስታዊ የዜና ማሰራጫን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤ ሊቢያ ውስጥ ታግተው የነበሩና በግብጽ ጦር ጥረት ከታገቱበት የተለቀቁ 27 ኢትዮጰያውያን ዛሬ ሀሙስ ካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ ገብተዋል። ኢትዮጰያውያኑ በግብጽ አውሮፕላን ተጉዘው ካይሮ ሲደርሱ በግብጽ ፕሬዚዳንት በአብደል ፋታህ አል-ሲሲ እና በሌሎች ከፍተኛ የግብጽ ባለስልጣናት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤የአቀባበል ሥነ-ስር ዓቱ በግብጽ ሚዲያዎች የቅጥታ ስርጭት እንዲታይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢሳት አዲሱ ስርጭቱ መቋረጡን ተከትሎ የችግሩን ምንጭ ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው
ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በቅርቡ በዩቴልሳት ስርጭቱን በአዲስ መልክ ማሰራጨት ቢጀምርም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምክንያቱ በውል ባልተወቀ ሁኔታ ስርጭቱ ተቋርጧል። እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቱ እንዲገለጽላቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቓል። የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የኢሳትን ስርጭት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው በማለት መገምገሙን መዘገባችን ይታወሳል። ኢሳት ...
Read More »ሰመጉ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን አስታወቀ
ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) የአሁኑ ሰመጉ ሚያዚያ 26 ቀን 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ በአዋሳና አዲስ አበባ በሚገኙ የድርጅቱ ፅህፈት ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል። መንግስት በተለያዩ ወቅቶች ላይ በድርጅቱ ላይ አፍራሽ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የጠቀሰው ሰመጉ፣ ሚያዚያ 24 ቀን 2004ዓም የሰመጉ የሃዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ በስራ ቀን ከጠዋቱ ...
Read More »የአዲስ አበብ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ መስቀል አደባባይ ላይ የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ እንደማያስተናግድ ገለጸ
ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ቢያቅድም ፣ ማካሄድ እንደማይችል ተነግሮታል። አስተዳደሩ ‹‹መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በርካታ የተከማዋ ነዋሪ የሚተላለፍበት እና የከተማው ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነው” በማለት ጥያቄውን አለመቀበሉን ገልጿል። መንግስት በቅርቡ በደቡብ አፍሪካና በአይ ኤ ኤስ ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በዲዛይንና ችግርና በሙስና ታክስ ከፋዩን ህዝብ ከፍተኛ ወጪ እያስወጡት ነው
ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ብቻ በዲዛይንና በሙስና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመባከኑ፣ ግብር ከፋዩ ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረጋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት በፌደራል የውሃ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት አማካሪነት እና በፌደራል ውሃ ስራዎች ቁጥጥር ድርጅት ተቋራጭነት የግንባታ ስራው እየተካሄደው ባለው የርብ መስኖና ግድብ ፕሮጀክት ጥልቅ የዳሰሳና አዋጭነት ጥናት ...
Read More »የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደቡብ ሱዳንና ኤርትራን ሊጎበኙ ነው
ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳሚ ሹክሪ ወደ ጁባ በማቅናት ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የሚመክሩ ሲሆን፣ ወደ ኤርትራም በማቅናት በሽበርተኝነት፣ እና በአካባቢው ባሉ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ የግብጹ አል ሃራም ዘግቧል። ጉብኝቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ መንግስት ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመራቸውን ባስታውቁ ማግስት እንዲሁም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የአባይን ግድብ በተመለከተ አዲስ የትብብር ማእቀፍ በተፈራረሙ ማግስት ...
Read More »በየመን የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤደንን ለመያዝ በሃውቲ ሚሊሺያዎችና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሃዲ መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን፣ 80 ሲቪሎች በጦርነቱ መሃል መገደላቸው ተዘግቧል። የሃውቲ ሚሊሺያዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ታማኞችና በአረብ አገራት ጥምረት የአየር ሃይል ጥቃት የተነሳ እስካሁን የኤደንን ከተማ ለመያዝ አልቻሉም።የከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።
Read More »በመተማ በተቃውሞ ላይ የተሳተፉ 2 ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ
ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም የመተማ ከተማ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በሄዱ ቤት አፍራሾችና የወረዳው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም፣ የፌደራል ፖሊሶች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ 2 ነዋሪዎች በጥይት ተመትተው ሲገደሉ፣ 3 ደግሞ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ቆስለዋል። ከ50 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ባላስልጣናቱ ...
Read More »በቅርቡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታሰሩት ወጣቶች በሃሰት እንዲመሰክሩ ጫና እየተደረገባቸው ነው
ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ለመዘከርና ቁጣቸውን ለመግለጽ ገዢው ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወጣቶች መንግስትን ሰድባችሁዋል በሚል ታፍሰው ከታሰሩ በሁዋላ፣ “ተቃውሞውን ያስነሱት በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ናቸው” ብላችሁ ካልመሰከራችሁ አትለቀቁም መባላቸውን የእስረኞች ቤተሰቦች ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ወጣቶች ማታ ማታ በደህንነት ሃይሎች እየተጠሩ በታሰሩ ...
Read More »74ኛው የድል በአል ተከበረ
ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 74 ኛ አመት በአዲስ አበባ ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት ተከብሯል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ሽንፈትን የተከናነበው ጣሊያን፣ ከ40 አመት በሁዋላ ራሱን በዘመናዊ መሳሪያ፣ በገንዘብና በሰው ሀይል አደራጅቶ ኢትዮጵያን ቢወርም፣ አባት አርበኞች ለ5 አመታት በዱር በገደሉ ባደረጉት ተጋድሎ፣ የፋሽስት ሙሶሎኒን ጦር ድል በማድረግ የአገራቸውን ነጻነት አስመልሰዋል። ኢትዮጵያ ...
Read More »