.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ ብሮድካሲቲንግ ኮርፖሬሽን ለቴሌቪዥን ስርጭቱ ገንዘብ ለመሰብሰብ በተንቀሰሳቀሰባቸው ከተሞች ህዝቡ የቴሌቪዥን ግብር አንከፈልም ሲል ተቃውሞውን እየገለጸ ነው

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተጠናክሮ በደረሰው ሪፖረት ህዝቡ “እኛ ኢቲቪን (ኢቢሲን) አይተን አናውቅም ፤ ለውሸት ጣቢያ ፈፅሞ ክፍያ አንፈፅምም ፤ በአይናችን ያየነውን ለሚክድ ሚዲያ እኛ ምንም ድጋፍ አናደርግም፡፡ እንደዚህ የሚባል ጣቢያ አለ እንዴ ፤ ኢቲቪ የሚባል ጣቢያ መኖሩን አናውቅም ነበር ” የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ፣ አንዳንዶች ደግሞ “እኛ ከኢሳት ውጭ ምንም ጣቢያ ሰምተንም አይተንም ...

Read More »

5 በሃይል አማራጭ የሚያምኑ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ውይይት ጀመሩ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማንኛውም አማራጭ ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸውን ውይይት መጀመራቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ውይይቱን የጀመሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን)፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ናቸው። ድርጅቶቹ ” በሂደት ወደ ...

Read More »

ኢህአዴግ በዜጎች ላይ ፍርሃት በመልቀቅ እንዲመረጥ እያግባባ ነው ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች ተናገሩ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘጋቢያችን በላከችው ሪፖርት የገዢው መንግስት ካድሬዎች በየመንደሩ በመዞር የሚደርጉት የምርጫ እንቅስቃሴ የነዋሪዎችን ነጻነት ከማሳጣቱ በተጨማሪ፣ ኢህአዴግ በሚጠራው የመንደር ስብሰባዎች የሚቀር ሰው የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ተብሎ ይመዘገባል። የገዢው ፓርቲ አባላትና የቀበሌ አመራሮች በየሰፈሩ በሚያደርጉት ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ ባለሃብቶችን ያለ ፈቃዳቸው ለዕለቱ የሚስፈልገውን ለቡና፤ዳቦ እና ቆሎ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ በመቀበል በሰፈሩ በመዘዋወር እንዲሰባሰቡ ...

Read More »

በሜሮን አለማየሁና ዳዊት አስራደ ላይ የ2 ሳምንት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም በሰልፉ ወቅት ከተያዘ በኋላ በ25 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ እንደገና የታሰረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የነበረው ዳዊት አስራደ ...

Read More »

በቴፒ 5 ሰዎች ተገደሉ

በጋምቤላና ደቡብ ክልል ድንበር አካባቢ የሪ በምትባል ቀበሌ 7 ሰዎች በተገደሉ ማግስት ሌሎች 5 ሰዎች ደግሞ በቴፒ ከተማ እንድሪስ ቀበሌ ውስጥ ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ በጥይት ተደብድበው መሞታቸውን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሟቾቹ መካከል አባትና ልጅ ይገኙበታል። ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ ገዳዮቹ ፖሊሶች ናቸው። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሰዎቹ ይተገደሉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ያስጠጋሉ፣ ይደግፋሉ ተብለው ነው። ኢሳት ለከተማው ...

Read More »

” ወጣቱ ስርዓቱን እንደማይፈልገው በምርጫ እንቅስቃሴው ወቅት አሳይቷል” አሉ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲዊ አንድነት መድረክ ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም በጃንሜዳ የተጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በህዝቡ በኩል በተለይ ወጣቱ መንቀሳቀሱን ይሁን እንጅ ብዙ ቦታዎች ላይ የምርጫ ሜዳው መዘጋቱን ገልጸዋል። ህዝቡ በስሜት ስብሰባዎችን መሳተፉን የገለጹት ዶ/ር መረራ ፣ በምርጫው መቀመጫ ባይገኝ የህዝቡን ትግል ወደ አንድ እርምጃ ለመውሰድ በሚደረገው ሙከራ በብዙ ቦታዎች ላይ ይህን ለማድረግ የቻልን ይመስለኛል ...

Read More »

በቡሩንዲ የተካሄደው መፈንቅለመንግስት ውጤት አሁንም አልለየለትም

ፕሬዚዳንት ኑኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ለመመረጥ መወሰናቸውን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ መፈንቅለመንግስት ከተቀየረ በሁዋላ፣ አገሪቱ በምን ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ዋና ዋና የሚባሉትን ተቋማት በተለይም የሬዲዮ ጣቢያ፣ አየር መንገዱንና ቤተመንግስቱን በመቆጣጠር መፈንቅለ መንግስቱ እንደከሸፈ ቢያስታውቁም፣ መፈንቅለመንግስቱን የሚደግፉ ሃኢሎች በበኩላቸው፣ ተቋማቱ በእነርሱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ እየገለጹ ናቸው። መፈንቅለመንግስቱ ያልተሳካ መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች በመታየት ላይ ቢሆኑም፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ...

Read More »

የአሜሪካ መንግስት በደቡብ ሱዳን ላገረሸው ጦርነት የሳልቫኪርን መንግስት ተጠያቂ አደረገ

ጁባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ በዩኒቲ ግዛት የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት ጥቃት በሲቪሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ተቃዋሚዎች አጽፋዊ እርምጃ በመውሰድ ጦርነቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ መግለጫው ጠይቋል። የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ የሚፈናቀሉ ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥር ጨምሯል። እስካሁን ባለው መረጃ ከ300 ሺ ያላነሱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተፈናቅለዋል።

Read More »

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ ራሳቸው ሆነዋል። በጠ/ሚኒስትር አቶ ...

Read More »

የዜጎች መታፈን ተባብሶ ቀጥሎአል

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ አገዛዙን ይቃወሙ ይሆናል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በገፍ እየተያዙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ወጣቶችም ከእስር ለማምለጥ መሸሸጋቸውን ለኢሳት እየገለጹ ነው። በተለያዩ ክልሎች የገዢው ፓርቲ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶች የሚታሰሩት ከምርጫው ጋር በተያያዘ ህዝቡን ለአመጽ ያነሳሳሉ በሚል ነው። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መሪ የነበሩት አቶ ማሙሸት አማረ   ዛሬ ...

Read More »