በሜሮን አለማየሁና ዳዊት አስራደ ላይ የ2 ሳምንት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ
በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም በሰልፉ ወቅት ከተያዘ በኋላ በ25 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ እንደገና የታሰረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት
አባል የነበረው ዳዊት አስራደ ግንቦት 7/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል።
ሜሮንና አቶ ዳዊት ሚያዝያ 5/2007 ዓ.ም ንፋስ ስልክ ላፍቶ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስት እንዲወጡ ተፈቅዶላቸው የነበር ቢሆንም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በማዛወር በእስር ላይ እንዲቆዩ
አድርጓል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል፡፡
ሁለቱም እስረኞች የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አለኝ በማለቱ ፍርድ ቤቱ ለግንቦት21 ቀጠሮ ሰጥቷል።