ኢሳት ዜና (ሰኔ 17 2007) በቀጣዩ ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተቃውሞ እንደገጠማቸው የእንግሊዙ ዘጋርዲያ ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዛሬ ረቡእ ዘገበ። አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚዳንቱ በሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና የምትታወቅ ሃገርን ለመጎብኘት መወሰናቸው ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ላይ መሆናቸውንም ጋዜጣው አስነብቧል። የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አንድ ኢህአዴግን ከድተዋል የተባሉ ጎልማሳ በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ሰሃራ በረሃ አቅራቢያ ተገደሉ፣ ሌሎች አምስት ወጣቶችም በአደጋው አልቀዋል
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያሬድ ንጉሴ የተባለ ባለፈው ወር አውሮፓ የገባ አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ለኢሳት እንደገለጸው በቅርቡ 25 ኢትዮጵያውያንና 2 ኤርትራውያን ሆነው ከሱዳን ወደ ሊቢያ ሲጓዙ፣ ደንጎላ በምትባል ቦታ ላይ በሱዳን የመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት የመጣ ኢትዮጵያዊ የደህንነት ሰራተኛ የ48 አመት ጎልማሳ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ከመኪና አስወርዶ በሽጉጥ እንደገደለው ገልጿል። “ወታደሮችን የጫነው መኪና” ከጎን በኩል ...
Read More »ኢትዮጵያ በተፈጸሙ ግድያዎችንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንድታጣራ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ባለፉት ጥቂት ወራት በተቃዋሚ መሪዎች ላይ የተፈጸመው ግድያና በመላ አገሪቱ በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ረገጣ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ላይ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነው ብሏል። የአፍሪካ ህብረትና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን መርምረው ሪፖርት አለማድረጋቸውንም ድርጅቱ ወቅሷል። ምርጫው እስከሚካሄድበት ጊዜ ድረስ ከ500 በላይ የመድረክ አባላት ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ሪፕሪቭ ዘመቻ ጀመረ
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝ አገር የሚገኘው ሪፕሪቭ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስቲር ዴቪድ ካሜሩን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። አቶ አንዳርጋቸው ለአንድ ሳምንት መታሰራቸው ረጅም መሆኑ ሳያንስ ለአንድ አመት ታስረው መቆየታቸው ለማሰብም የሚከብድ ነው ሲል የህግ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቀው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል። በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሪፐሪቭ ዌብሳይት በመግባት በፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻው እንዲሳተፉ ...
Read More »በያዝነው ወር መጨረሻ የሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተለጠጠ እንደነበር ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ አረጋገጡ፡፡
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ሰሞኑን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ዕቅዱ የተለጠጠ መሆኑን አምነው ሙሉ በሙሉ ላለመሳካቱ ምክንያት ያሉዋቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል፡፡ የመጀመሪያው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በባህርይው መዋቅራዊ ለውጥን ታሳቢ ያደርጋል፡፡ ይህ ዕቅድ በራሱ ተለጥጦአል ብለዋል፡፡ የፋይናንስ ምንጭ ማፈላለጉ በራሱ ትልቅ ጫና ነበረው ያሉት ...
Read More »ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው የስምንት ወራት እስራት ሲፈረድባቸው ሜሮን አለማየሁ ለሰኔ ሃያ አራት ተቀጠረች
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይሲስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ለመቃወም በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ድርጊቱን ለማውገዝ በስፍራው ተገኝታ የነበረችው ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ ከ3 አመት ልጇ ጋር ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ያለ ማዘዣ በፖሊስና በደኅንነት ኃይሎች ተወስዳ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በሁዋላ ሰኔ 17/2007 ዓ.ም ቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ...
Read More »ምርጫ ቦርድ “ኢህአዴግ መቶ በመቶ አሸንፏል” ሲል የመጨረሻ ቡራኬውን ሰጠ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ ቦርድ ጊዚያዊ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት የ105 ወንበሮችን ጉዳይ ግልጽ ባለማድረጉ አንዳንዶች “ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ለመካፋፈል አስቦ ያደረገው ሊሆን ይችላል” በማለት አስተያየት ሲሰጡ ቢቆዩም፣ ቦርዱ ግን ኢህአዴግ መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፋል በማለት የመጨረሻ ውሳኔውን ሰጥቷል። ዋናዎቹ የተቃዋሚ ድርጅቶች ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ ምርጫውን ” አሳፋሪ” ነው ሲሉ አጣጥለውታል።በአፍሪካ ምርጫን 100 በመቶ ...
Read More »ፍርድ ቤት አቶ ማሙሸት አማረ ዋስትና ተከልክለው ወደ ቅሊንጦ እንዲላኩ ወሰነ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ችሎቱን የተከታተሉት በአቶ ማሙሸት የሚመራው መኢአድ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለኢሳት እንደገለጹት አቶ ማሙሸት፣ ሰኔ 10፣ 2007 ዓም በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ፍርድ ቤት የወሰነ ቢሆንም፣ ፖሊስ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቦታል። ፖሊስ፣ አቶ ማሙሸት ቢፈታ በምስክሮቼ ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ሊያደርስባቸው ይችላል የሚል ይጋባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ ...
Read More »የአዲስ አበባ ባለታክሲዎች በግዳጅ ቦንድ እንዲገዙ ታዘዙ።
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ የግል ባለንብረቶች ወደ አዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤቶች ታፔላ ለመቀየር በሄዱበት ወቅት ከተለመደው የታፔላ ማስቀየሪያ አገልግሎት ክፍያ ውጪ ባልተጠበቀ ሁኔታ የ1ሺ ብር ቦንድ ካልገዛችሁ የሚል ግዳጅ ተጥሎባቸዋል ። “አሁንስ ወዴት እንሂድ? ለማን አቤት እንበል?” በማለት የታክሲ ባለንብረቶች ሲያማርሩ ተሰምተዋል። ታክሲዎች ለ3 ወራት ያክል ...
Read More »በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ሊደረጉ ነው
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይካሄዳል። በጀርመን በፍራንክፈርት፣ሙኒክ፣ዱስልዶርፍ እና በርሊን የሚካሄድ ሲሆን፣ በፍራንክፈርት የሚደረገው ተቃውሞ ለ24 ሰአታት ይቆያል። በጣሊያን ሮማ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ፣ በእንግሊዝ ለንደንና በኖርዌይ ኦስሎ የተቃወሞ ሰልፎች ...
Read More »