በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ሊደረጉ ነው

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይካሄዳል። በጀርመን በፍራንክፈርት፣ሙኒክ፣ዱስልዶርፍ እና በርሊን የሚካሄድ ሲሆን፣ በፍራንክፈርት የሚደረገው ተቃውሞ ለ24 ሰአታት ይቆያል።
በጣሊያን ሮማ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ፣ በእንግሊዝ ለንደንና በኖርዌይ ኦስሎ የተቃወሞ ሰልፎች እንደሚደረጉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።