ምርጫ ቦርድ “ኢህአዴግ መቶ በመቶ አሸንፏል” ሲል የመጨረሻ ቡራኬውን ሰጠ

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ ቦርድ ጊዚያዊ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት የ105 ወንበሮችን ጉዳይ ግልጽ ባለማድረጉ አንዳንዶች “ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ለመካፋፈል አስቦ ያደረገው ሊሆን ይችላል” በማለት አስተያየት ሲሰጡ ቢቆዩም፣ ቦርዱ ግን ኢህአዴግ መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፋል በማለት የመጨረሻ ውሳኔውን ሰጥቷል።
ዋናዎቹ የተቃዋሚ ድርጅቶች ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ ምርጫውን ” አሳፋሪ” ነው ሲሉ አጣጥለውታል።በአፍሪካ ምርጫን 100 በመቶ ያሸነፈ የፖለቲካ ድርጅት አለመኖሩን መረጃዎች ያሳያሉ። ከሰሜን ኮሪያ በመቀጠል መቶ በመቶ የምርጫ ውጤት የተገለጸባት አገር ኢትዮጵያ ናት።