.የኢሳት አማርኛ ዜና

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪ ደላሎች ታግተው ገንዘብ እንደሚጠየቁ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም አስታወቀ

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም በየመን አድርገው በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመግባት ሲሞክሩ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ታግተው የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰባቸውን ቁጥራቸው 3 ሺ 478 የሚሆኑ በጎፈቃደኛ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቀዋል። የ18 ዓመቱ ወጣት አልማይ ፍፁም ”በመኪና ተጭነን ወደ ሳዑዲ ድንበር እንደተቃረብን ፤ መሳሪያ ያነገቡ ታጣቂዎች ወደ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛ ሆኖ፣ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል ማለት እንደማይቻል የቀድሞ ኮሚሽነር አስታወቁ

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት አቶ ጌታሁን ካሳ ”የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሚናውና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ላይ ይጋጠሙት ፈተናዎች” በተሰኘ ጥናታዊ የምርምር ሥራቸው ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተቋም ነፃና ገለልተኛ ሆኖ፣ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል ማለት እንደማይቻል አመልክተዋል፡፡አቶ ጌታሁን ኮሚሽኑ ሰብዓዊ መብትን ለማስተዋወቅና ...

Read More »

በምስራቅ እዝና በሃረሪ ክልል ፖሊሶች መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት እንደ አዲስ ባገረሸው የምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የሃረሪ ክልል ፖሊሶች ግጭት 4 ፖሊሶች በመከላከያ አባላት ታፍነው መወደሳቸውንና እስካሁን የደረሱበት አለመታወቅን የሃረር ወኪላችን ገልጿል። የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከሁለቱ ሃይሎች የተውጣጡ መሪዎችን ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። በሃረሪ ፖሊስና በምስራቅ እዝ የፖሊስ አባላት መካከል ያለው ግጭት የቆየ ሲሆን ፣ አንድ አንድ ...

Read More »

በአርባምንጭ ግንቦት7 ገብቷል በሚል ስጋት ህዝቡ ሲፈተሽ ዋለ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርባምንጭ ምንጮች እንደገለጹት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ አባላት በየአንዳንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ፍተሻ ሲያደርጉ የታየ ሲሆን፣ አንዳንድ ሰዎች ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጣቸው መልስ ” ግንቦት7″ ከተማው ውስጥ ገብቷል የሚል ነው። በከተማውና በዙሪያ ወራዳዎች የሚታየው ፍተሻና ቁጥጥር መጨመሩን ፣ ህዝቡም ግራ ተጋብቶ እንደሚገን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ባለፈው ቅዳሜ የጋሞን ...

Read More »

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጠበቃ የሆኑት ለደንበኞቻቸው ያቀረቡት መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ከ1 እስከ 6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጉ ተከሳሾቹ ሀምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት 7 ቀን 2006 ...

Read More »

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ለአንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች የአደጋ ጥሪ ነው ተባለ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦባማ በአፍሪካ ለሚያደርጉት ጉዞ በተለይ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው አገሪቱ በሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር የሌላት በመሆኑ ከዓለምአቀፍ ማኅበረሰቡ ኢትዮጵያን መጎብኘት ማቆም እንዳለባቸው በማሳሰብ ከፍተኛ ወቀሳ እየተሰነዘረባቸው ነው። በአፍሪካ ስላለው የሰብዓዊመብት አያያዝ ላይ ፕሬዝዳንቱ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል።በአንፃሩ ለፀጥታና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ዓላማ ይዘው ወደ አፍሪካ አህጉር የሚያቀኑት ኦባማ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ነጻነት ቀዳሚው ...

Read More »

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

ሐምሌ ፲፫ (አስራሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል” በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ...

Read More »

አመት በዓሉን ከህወሃትና ከኦህዴድ በአል ባላነሰ ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅት ጀመረ

ሐምሌ ፲፫ (አስራሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህውሃት 40ኛ ዓመቱንና ኦህዴድ 25ተኛ አመቱን ባከበሩበት ማግስት፣ ብአዴንም 35ተኛ አመቱን ከሁለቱ ድርጅቶች ባላነሰ ለማክበር በብዙ መቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ መመደቡን የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ባደረጉት ዝግ ስብሰባ መነጋገራቸውን ምንጮች ጠቅሰዋል። ከሀምሌ ወር, 2007 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ጋዜጠኛ የብአዴንን ታሪክ ለማወቅ የሚረዱትን መጽሃፍት በማሰባሰብ እንዲያነብና የተለያዩ ዶክሜንታሪ፣የጉዞ ማስታወሻዎችንና የመሳሰሉትን መሳጭ ...

Read More »

የዞን 9 ጦማርያን ሌላ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ሐምሌ ፲፫ (አስራሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን ሐምሌ 13/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በእስር ላይ የሚገኙት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና አቤል ዋበላ ለ31ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የዘገበው ጋዜጣው፣ መዝገቡ ...

Read More »

የኢድ አል ፈጥር በአል ተከበረ

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አለም የሚኖሩ ሙስሊሞች 1 ሺ 436ኛውን የኢድ አልፈጥር በአል አክበረዋል። በአሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተከበረ ሲሆን፣ ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ ሲታይ እንደነበረው በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ ታይቷል። በተለያዩ አለም ክፍሎች በአሉ በአንጻራዊ መልኩ በሰላም ሲጠናቀቅ፣ በናይጀሪያ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ከ10 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በግብጽ ...

Read More »