ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ሱዳንዋ ዋና ከተማ ጁባ ማንነቱ ባልታወቀ ነፍጥ ባነገተ ታጣቂ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ሲገደል ሌሎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል። ማክሰኞ ዕረፋዱ ላይ በጁባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት ደጅ ላይ ዳቦ በመሸጥ ይተዳደሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችን የገደለውና ያቆሰለው ግለሰብ እስካሁን አልተያዘም። የአካባቢው ነዋሪዎች የሩምታ ተኩሱን ተከትሎ እንቅስቃሴያቸው የተገታ መሆኑንና ከቤት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በደራ ወረዳ በመሬት መደርመስ ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ ትራንስፖርት ተቋረጠ
ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍቼ ወደ ጉንዶመስቀል የሚሄደው መንገድ ውቄና አንኮ ድልድይ አካባቢ በመቆረጡ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል። መንገዱ በአፋጣኝ ባለመጠገኑ ነዋሪዎች መጉላላታቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። በተለይ አምቡላንሶች በሽተኞችን ይዘው ለመጓዝ ባለመቻላቸው ችግር እየተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
Read More »የደቡብ ክልል አመራሮች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው
ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታደለ ቱፋ የተጻፈውን የጋሞን ህዝብ ማንነት የሚያንቋሽሸውን መጽሃፍ ፣ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የገንዘብ ደጋፍ በማድረግ አስጽፈውታል በሚል ምክንያት ፣ በአርባምንጭና በተለያዩ የጋሞ ወረዳዎች የተቃውሞ ሰለፎች መደረጋቸውን ተከትሎ፣ በከፍተኛ አመራሩ እና በታች አመራሩ መካከል ያለው አለመግባባት ይፋ ሆኗል። ለኢሳት የደረሰው የድምጽ ማስረጃ ከመጽሃፉ ጋር በተያያዘ ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን አሁንም በመተማ በኩል መፍለሳቸውን አላቋረጡም
ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያዋ የድንበር ከተማዋ መተማ አሁንም ኢትዮጵያዊያን መሰደዳቸውን አላቋረጡም ሲል ዘጋርዲያን ዘገብዋል። መንግስት ጥበቃውን አጠናክሮ በአካባቢው ብዙ ሰራዊት ቢያሰማራም በቀን ከ100 እስከ150 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞ ድንበር አቋርጠው ይሰደዳሉ። መተማ ከተማ ወደ መቶ ሽህ የሚገመት ነዋሪዎች ያላት ስትሆን የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሌ ስደተኞች መተላለፊያ ናት።ከተማዋ መንግስት በወሰደው የጥበቃ ማጠናከር ሳቢያ ገቢዋ መቀዝቀዙንም ፣ 80% ...
Read More »ፍርድ ቤቱ በነፃ ያሰናበታቸውን እስረኞች ከእስር ቤት አልወጡም
ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት በነጻ እንዲሰናበቱ ከተፈረደላቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት መፈታት ባለመቻላቸው ...
Read More »አዲስ አበባ መስተዳድር ከንቲባ በአማካሪዎች ብዛት ተጨናንቀዋል
ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመስተዳድሩም ምንጮች እንደገለጹት የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በአማካሪዎቻቸው ብዛት ተጨናንቀዋል። አማካሪዎቹ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሹሙ የሚመጡ በመሆኑ፣ ከንቲባው ግራ ተጋብተዋል። አማካሪ የሚባሉት ሰዎች በጸሃፊያቸው በኩል አስፈቅደው ወደ እርሳቸው ቢሮ ከገቡ በሁዋላ ” እኔ እኮ የዚህ ዘርፍ አማካሪዎ ነኝ” ሲሉዋቸው፣ ከንቲባው በመደናገጥ ” ከስራ ብዛት ነው ያላወኩዎት” በማለት ይቅርታ እየጠየቁ ...
Read More »ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤጅንግ የዓለም ሻምፒዮና ትንሽዋ ልዕልት የ24 ዓመቷ ገንዘቤ ዲባባ ለኢትዮጵያ በ1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር ርቀቱን 4:08.09 በሆነ ሰዓት በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ባለፈው ወር ፈረንሳይ ሞናኮ ውስጥ በርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ገንዘቤ ዲባባ ያስገኘችው ድል መላውን ኢትዮጵያዊ ያኮራ ውጤት ሲሆን ውድድሩን ገንዘቤ ዲባባ በመሪነት ስታጠናቅቅ ኬንያዊቷ ፎይዝ ቺፕቲንግ ተከትላት ...
Read More »በዝናብ እጥረት የዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 19 2997) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ ያለው ድርቅ የምግብ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተረጂዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት የተጨማሪ የ230 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል ። ለምግብ እጥረት አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መካከል 4.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በተያዘው አመት አስቸኳይ የምግብ እርዳታን እንደሚፈልጉ ...
Read More »በነባሩና በአዲሱ የድርጅቱ አመራር መካካል ልዩነት መኖሩን ብአዴን ገለጸ
ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ እንደገለጸው፣ ለረጅም ጊዜ በአመራርነት ቆይቶ ስልጣኑን በመተካካት ሂደት ባስረከበውና ቁልፍ ስልጣኑን በተረከበው መካካል የመግባባት ችግር መኖሩን ገልጿል። ነባሩ አመራር ሁሉንም ሃላፊነት አስረክቦ ድርጅቱን የመልቀቅና ራሱን ገለል አድርጎ ለመኖር ይፈልጋል ያለው ብአዴን፣ በዚህም ላይ ነባሩ አመራር በአዲሱ አመራር እንደማይረካና ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርብም ገልጿል። ቁልፍ ስልጣን የተረከበው አዲሱ ...
Read More »ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ
ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ 4 ነብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጋር የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በተያዘው አመት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የተረጅዎች ከግምት ውጪ ላሻቀበው የተረጅዎች አሀዝ ብቻ 230 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ 4 ነጥብ 7 ...
Read More »