በደራ ወረዳ በመሬት መደርመስ ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ ትራንስፖርት ተቋረጠ

ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍቼ ወደ ጉንዶመስቀል የሚሄደው መንገድ ውቄና አንኮ ድልድይ አካባቢ በመቆረጡ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል።
መንገዱ በአፋጣኝ ባለመጠገኑ ነዋሪዎች መጉላላታቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። በተለይ አምቡላንሶች በሽተኞችን ይዘው ለመጓዝ ባለመቻላቸው ችግር እየተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።