ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤጅንግ የዓለም ሻምፒዮና ትንሽዋ ልዕልት የ24 ዓመቷ ገንዘቤ ዲባባ ለኢትዮጵያ በ1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር ርቀቱን 4:08.09 በሆነ ሰዓት በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
ባለፈው ወር ፈረንሳይ ሞናኮ ውስጥ በርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ገንዘቤ ዲባባ ያስገኘችው ድል መላውን ኢትዮጵያዊ ያኮራ ውጤት ሲሆን ውድድሩን ገንዘቤ ዲባባ በመሪነት ስታጠናቅቅ ኬንያዊቷ ፎይዝ ቺፕቲንግ ተከትላት በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።