.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ መንግስትጋዜጠኞችን ማሰር መቀጠሉን ሲፒጄ ዘገበ

ኢሳት (ታህሳስ 13 ፣ 2008) በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጀት ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ለእስር ማዳረጉ CPJ ገለጠ የጋዜጠኛ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጋዜጠኛው ፍቃዱ ምርካና ቅዳሜ  ጠዋት አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ሀይሎች መታሰሩን አስታውቋል ። ጋዜጠኛው የታሰረበት ምክንያት በግልጽ አለመታወቁን ያስታወቀው ድርጅቱ መንግስት ጋዜጠኛውን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል ። ለደህንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡ ...

Read More »

በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰመጉ አስታወቀ።

ታኀሳስ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃ፣ ከመነሻው ሰላማዊ የነበረውን ተቃውሞ ግብታዊ መልክ እንዲይዝና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንዲባባስ በማድረግ ለዜጎች ሞት፣ አካል ጉዳት እና የህዝብ እና የግል ንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል ሲል ድርጅቱ ገልጿል። ሰመጉ ታህሳስ 11 ቀን 2008 ዓም ” ከአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ...

Read More »

መንግስት ከብቶቻችሁን ሽጣችሁ ራሳችሁን አድኑ ብሎናል ሲሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ

ታኀሳስ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ከ800 ያላነሱ በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች የምግብና የውሃ እጥረት የተከሰተ ሲሆን፣ አርሶ አደሮቹ መንግስት ከብቶቻችንን ሽጠን ራሳችንን አድኑ ቢለንም ከብቶቻችንን የሚገዛን አጥተናል ብለዋል። መማር ማስተማር ተሰተጓጉሏል፤ የጤና ችግሮች አጋጥመውናል፣ አዲስ የሚወለዱ ህፃናት እና ሴቶች በስፋት ተጎድተዋል ሲሉ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡

Read More »

የአባይ ድልድይ አደጋ ላይ ነው ተባለ፡፡

ታኀሳስ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአሁን በፊት የባህርዳር ነዋሪዎች ባህርዳር ላይ የሚገኘው የአባይ ድልድይ ችግር አጋጥሞታል በማለት በልዩ ልዩ ስብሰባዎች ቢያሳስቡም የገዢው መንግስት አመራሮች በቅርቡ ተለዋጭ ይሰራል በማለት ሲሸነግሉ ቆይተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የድልድዩ ወደ ሰሜን መውጫ ክፍል ላይ ያለው ንጣፍ ዝቅ እያለ በመሄዱ ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በቦታው የፌደራልና የክልሉ ፖሊሶች ተመድበው፣ መኪኖች በድልድዩ ...

Read More »

የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጠየቁ

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ የወሰደውን እርምጃ በጽኑ አውግዘዋል። የኦሮሞ ህዝብ በአጋንንት ተመስሎ ተሰድቧልና ተሳዳቢው ባለስልጣን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል። መንግስት ለሞቱት ዜጎች ሃላፊነቱን እንዲወስድና ለህዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አሳስበዋል።በአዲስ አበባ የሚገነቡት ፎቆች የማን ናቸው? ሲሉም ጠይቀዋል።አርጅተናል አልቻልንም ስልጣናችንን እናስረክብ ያሉ አመራሮችም አሉ። ሰፊ ሰአት በሚሸፍነው ስብሰባ የሚከተሉት ሃሳቦች ቀርበዋል። የመጀመሪያው ባለስልጣን ...

Read More »

በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ገዢው ፓርቲ የጠራው ስብሰባ በውግዘት እየተጠናቀቀ ነው።

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር ከተማ ህዝቡ የመንግስትን እርምጃ ሙሉ በሙሉ አውግዟል። በሌላ በኩል መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተከትሎ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ ጠርተዋል። የሰልፉ አላማ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ እንዲሁም መንግስት ...

Read More »

የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት በየአካባቢው እየዞሩ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፖሊሶች እየዞሩ የስርጭት መቀበያ ዲሾችን ከማስወረዳቸው በተጨማሪ ባለስልጣኖችና ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩና በስብሰባ ቦታዎች ሳይቀር ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት አስጠንቅቀዋል። ሰሞኑን ኢሳት በናይል ሳት የሚለቀው ስርጭቱ ከገዢው ፓርቲ በተደረገው አፈና የተቋረጠበት ቢሆንም በዩቴል ሳት 70 ቢ፣ በ75 ዲግሪ ላይ አሁንም ስርጭቱን እንደቀጠለ ነው።

Read More »

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደብድበው ታሰሩ

ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ምሽት የፌደራል ፖሊስ አባላት 6 ኪሎ ግቢ በመግባት 2 ተማሪዎችን ማሰራቸውን ተከትሎ የታሰሩት ተማሪዎች እንዲፈቱ በሰልፍ የጠየቁ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደብድበዋል። ዩኒቨርስቲው ከጠዋት ጀምሮ በፖሊሶች ተከቦ ያረፈደ ሲሆን፣ ከቀኑ 7 ሰዓት ተኩል አካባቢ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው በመግባት በርካታ ተማሪዎችን እየደበደቡ ወስደው አስረዋል። ከአራት ኪሎ ግቢ እስከ ስድስት ኪሎ ግቢ ባለው ...

Read More »

መንግስት በልማት ስም እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የአየር ላይ ካርታ እያስነሳ ነው

ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህንነት ምንጮቻችን እንደገለጹት መንግስት እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጠሎአል። 99 በመቶ የሚሆነው ቦታ በአንድ ብሄር ተወላጆች የተያዘው የብሄራዊ ደህንነት መስሪያ ቤት ኢንሳ፣ ተላልፎ የሚሰጠውን መሬት የአየር ላይ ፎቶግራፍ እያነሳ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የደህንነት ኤጀንሲው ፎቶ የማስነሳቱን ስራ የሚሰራው ትልቅ ለሆነ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚል ሰበብ ሲሆን፣ ዋናው ...

Read More »

በሱሉልታ እና በሌሎችም ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ዋሉ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ 26 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘዋ ሱሉልታ ሁሉም የህብረተሰብ ከፍል የተሳተፈበት ከባድ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄዷል። የጸጥታ ሃይሎች በወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ታጅበው ቅኝት ሲያደርጉ ውለዋል። በህዝቡ ላይ ፍርሃት ለመልቀቅ የተደረገው ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም እና ጎንደር የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆሮ አርፍዷል። የጸጥታ ሃይሎች በርካታ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። ተመሳሳይ ...

Read More »