በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ገዢው ፓርቲ የጠራው ስብሰባ በውግዘት እየተጠናቀቀ ነው።

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር ከተማ ህዝቡ የመንግስትን እርምጃ ሙሉ በሙሉ አውግዟል።
በሌላ በኩል መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተከትሎ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ ጠርተዋል።
የሰልፉ አላማ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ እንዲሁም መንግስት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬት እንዳይሰጥ ለመቃወም ነው፡
ሰልፉ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አድርጎ፣ በቸርቺል አደባባይ የሚያልፍ ሲሆን መዳረሻው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ በሚጀመረው ሰልፍ በርካታ ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።