የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት በየአካባቢው እየዞሩ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፖሊሶች እየዞሩ የስርጭት መቀበያ ዲሾችን ከማስወረዳቸው በተጨማሪ ባለስልጣኖችና ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩና በስብሰባ ቦታዎች ሳይቀር ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት አስጠንቅቀዋል።
ሰሞኑን ኢሳት በናይል ሳት የሚለቀው ስርጭቱ ከገዢው ፓርቲ በተደረገው አፈና የተቋረጠበት ቢሆንም በዩቴል ሳት 70 ቢ፣ በ75 ዲግሪ ላይ አሁንም ስርጭቱን እንደቀጠለ ነው።