መንግስት ከብቶቻችሁን ሽጣችሁ ራሳችሁን አድኑ ብሎናል ሲሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ

ታኀሳስ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ከ800 ያላነሱ በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች የምግብና የውሃ እጥረት የተከሰተ ሲሆን፣ አርሶ አደሮቹ መንግስት ከብቶቻችንን ሽጠን ራሳችንን አድኑ ቢለንም ከብቶቻችንን የሚገዛን አጥተናል ብለዋል።
መማር ማስተማር ተሰተጓጉሏል፤ የጤና ችግሮች አጋጥመውናል፣ አዲስ የሚወለዱ ህፃናት እና ሴቶች በስፋት ተጎድተዋል ሲሉ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡