ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪዩተርስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ አስከፊ በተባለው ረሃብ 400 ሺ ህጻናት ከፍተኛ አደጋ አንዣቦባቸዋል። አንድ አስረኛ የሚሆነው ህዝብ ራሱን መመገብ በማይችልበት ደረጃ መደረሱን ዘጋባው አመልክቶ፣ የአለማቀፉ ማህበረሰብ የሚሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን ችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል። በአሜሪካ የህጻናት አድን ድርጅት ፕሬዚዳንት ካሮሊን ማይልስ አፋርና አማራ ክልሎችን መጎብኘታቸውን ለዜና ምንጩ ገልጸው፣ በምግብ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኦሮምያና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ
ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥር 13 ቀን 2008 ዓም በአውስትራልያ ብሪዝቤን ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በአይነቱ ልዩ የተባለለት ነው። ህብረ ብሄራዊነት በተንጸባረቀበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳታፊዎቹ በጋራ የኢትዮጵያን መንግስት ያወገዙ ሲሆን፣ በተለይም ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ ማፈናቀልና እስራት፤ በጎንደር ገበሬዎችን በማፈናቀል ለሱዳን መሬት ቆርሶ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ...
Read More »የብሪታንያ መንግስት እንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥሪ እንዲያቀርብ ሪፕሪቭ የተሰኘ ተቋም ጠየቀ
ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) የብሪታኒያ መንግስት ከቀናት በኋላ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔን በመጠቀም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥሪዎን እንዲያቀርብ ሪፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሃሙስ አሳሰበ። በዚሁ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የብሪታኒያውን የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሚኒስትር የሆኑት ጀምስ ዱድሪጅ ወደ አዲስ አበበ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሃላፊው ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ ተከትሎም የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ...
Read More »ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንደሚቆም ገለጹ
ኢሳት ዜና (ጥር 12 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በኢትዮጵያ መንግስትና በጸጥታ ሃይሎቹ በህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፅኑ ማውገዙን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት ምንጊዜም ከኢትዮጵያውያን ጎን እንደሚቆም ገለጹ። የህብረቱ ፓርላማ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ 140 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እንዲያይ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አመጽና ከግንቦት 2007 ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደከፋ የረሃብ ቀውስ ሊቀየር እንደሚችል ተገለጸ
ኢሳት (ጥር 12 ፥2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ የሚገኘው የድርቅ አደጋ በተያዘው የፈረንጆች አዲስ አመት ወደከፋ የረሃብ ሰብዓዊ ቀውስ ሊለወጥ እንደሚችል ካሪታስ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የሰብዓዊ እርዳታ ተቋም ሃሙስ አሳሰበ። በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ጉዳትን እያደረሰ የሚገኘው ይኸው የድርቅ አደጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ አለም አቀፍ ርብርብ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ መድረሱንም ድርጅቱ ገልጿል። በሃገሪቱ ያለው የድርቅ አደጋ አስከፊ ገጽታን ከመያዙ በፊት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ
ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የመከረው የአውሮፓ ፓርላማ ባሰራጨው መግለጫ በኢትዮጵያ የመንግስት ሃይሎች በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን ግድያ አውግዟል። በዚሁ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ከተገደሉ ሰዎች በተጨማሪ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የአውሮፓ ፓርላማ ገልጿል። በተለያዩ አለም አቅፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በኢትዮጵያ የፓርቲ አካላት ይፋ የተደረገው የ 140 በላይ ...
Read More »የአውሮፓ ፓርላማ በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ የእርምጃ ሃሳቦችን አጸደቀ
ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) የአውሮፓ ፓርላማ በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ለሰዓታት የፈጀ ክርክርን በማካሄድ ለውይይት የቀረቡ በርካታ የእርምጃ ሃሳቦችን ሃሙስ አጸደቀ። ይኸው የፓርላማ አባላቱ ያጸደቁት ሃሳብ የተለያዩ አንቀጾች ሲኖሩት የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ መወሰድ ስለሚገባው እርምጃዎችና ፖሊሲዎች ግብዓት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ተከትሎ የተካሄደው ይኸው ልዩ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል አሁንም ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2012) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ያገረሸ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቋውሞ በምዕራብና በምስራቅ የኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች መቀጠሉ ተገልጿል። የሰሞኑ በመኢሶ ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ እልባት ያላገኘ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞዎችም በወለጋ አካባቢ በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የተቋረጡ የከፍተኛ ትምርት ተቋማት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ እየተደረገ ያለው ጥረትም ተማሪዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ ምክንያት አለመሳካቱ ተገልጿል። በእስር ላይ የሚገኙ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ጠንካራ የተባለውን ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ አሳለፈ
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 7ቱ ዋና ዋና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽድቀዋል። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቀኝ አክራሪዎች ብቻ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለህጉ መጽደቅ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የሰነበቱት የህብረቱ የፓርላማ አባል ሚስ አና ጎሜዝ በውሳኔው መደሰታቸውን ተናግረዋል። “በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው፣ በተለይ ዋና ዋና የሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች የውሳኔው ሰነድ ...
Read More »በጋምቤላ በተነሳው ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎዱ
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ምንጮች እንደገለጹት ጥር 11 ፣ 2008 ዓም 11 ሰዓት አካባቢ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በተነሳው ግጭት በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል።ግጭቱ ወደ ከተማው በመስፋፋቱ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ፣ መኪኖችም ተሰባብረዋል። የግጭቱ መንስኤ በትክክል አልታወቀም። የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፈደራል አባላት ከተማዋን መቆጣጠራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ለጊዜው የቆመ ቢመስልም በማንኛውም ሰአት ...
Read More »