.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኦነግ የወጣቶች ክንፍ በማደራጀት ውጊያ ሊያካሄዱ ነበር የተባሉ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የወጣቶች ክንፍን በማደራጀት ከመንግስት ጋር ውጊያን ሊያካሄዱ ነበር የተባሉ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው ተዘገበ። ተጠርጣሪዎቹ በተለምዶ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት የእምነት ስነስርዓት የሚያካሄዱ በመምሰል ለወጣቶች ክንፍ አባላት ሲመለምሉና ሲያደራጁ መቆየታቸውን ከሳሽ አቃቤ ህግ በክሱ አቅርቧል ሲል ሪፖርተር ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ መንግስት ...

Read More »

ብሪታኒይ ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ድጋፍ ላይ ተቃውሞ መጀመሩን የዜና አውታሮች እየዘገቡ ነው

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) የብሪታንያ መንግስት ለኢትዮጵያ በሚሰጠው የደህንነትና የጸጥታ ድጋፍ ዙሪያ አዲስ ተቃውሞ መቅረብ መጀመሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ሃገሪቱ ዜጋዋን አስሮ ለሚገኝ ሃገር በአየመቱ ወደ አንድ ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ በመመደብ የጸጥታ ሃይሎች ልዩ ስልጠናን እንዲያገኙ ማድረጓ የብሪታኒያ የተለያዩ አካላት በመቃወም ላይ መሆናቸውን ዴይሊ ሜይል የተሰኘ ጋዜጣ በሳምንቱ መገባደጃ ባወጣው ሪፖርት አስነብቧል። የብሪታኒያ መንግስት አጋር አድርጎ ድጋፍ ከሚሰጣቸው ...

Read More »

የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) የአንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ሃያሲ፣ ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ የመታሰቢያ ፕሮግራም ባሳለፍነው ቅዳሜ ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ዓም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ዋለ። አዘጋጅ ኮሚቴው እንደገለጸው ከሆነ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት ዘመኑ ለሃገርና ለህዝብ ላበረከተው አስተዋፅዖ ለማመስገንና ህያው ስራዎቹ ለመዘከር በማሰብ የተዘጋጀ ፕሮግራም ሲሆን፣ ዝግጅቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ስኬታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁ ለኢሳት ገልጸዋል። የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ...

Read More »

በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የታሰበው የዕርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ መንግስት ትዕዛዝ ሰጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) ኢትዮጵያውያን የድርቅ ተጠቂዎችን ለመታደግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) ከሌሎች ለጋሾች ጋር ያስተባበረው የዕርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ መንግስት ትዕዛዝ ሰጠ። የኢሳት ምንጮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ለአዲስ አበባው የኦቻ (OCHA) ተጠሪ ማሰባሰቢያውን የሰጡት የጠ/ሚኒስትሩ ልዩ መልዕከተኛ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ናቸው። 10.2 ሚሊዮን በቀጥታ በድርቁ ተጠቂ በመሆናቸው ሌሎች 8 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ በሶፍትኔት ...

Read More »

ለህዳሴ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠሩ ስብሰባዎች በተቃውሞ ተበተኑ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብና ለኮንዶሚኒየም በሚል በአሜሪካና በአውሮፓ ከተሞች የተንቀሳቀሰው የመንግስት ተወካዮች ተቃውሞ ቀረበባቸው። ስብሰባዎችም በተቃውሞ ተበተኑ። በአሜሪካ ፔንስልቬንያ ግዛት የፊላዴልፊያ ከተማ እንዲሁም በጣሊያን ቱርኒ በሳምንቱ መጨረሻ የተጠሩት ስብሰባዎች ያለውጤት በተቃውሞ መበተናቸውን ለኢሳት በቪድዮ የደረሰው ዜና ያስረዳል። በኢትዮጵያ የተከሰተውን ርሃብ እንዲሁም በኦሮሚያ የቀጠለውን ግድያና እስራት እያነሱ ተቃውሞ ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን፣ የአንድ ብሄር የበላይነት በሃገሪቱ አለ ሲሉም ...

Read More »

በቶሪኖ የተጠራው የመንግስት ስብሰባ በተቃውሞ ተበተነ

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ሚያዚያ 3፣ 2008 ዓም በጣሊያኑዋ የቶሪኖ ከተማ መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ለመጨጥ እንዲሁም አወዛጋቢ የሆነውን የኮንዶሚኒየም ሽያጭ ለማከናወን እና የውጭ ምንዛሬ ለመሰብሰብ የጠራው ስብሰባ በከተማዋ በሚገኙ ኢትጵያውያን ተቃውሞ እንዲሰረዝ ተደርጎአል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ገና ከመነሻው ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ መሰረታዊ የሚባሉ የመብት፣ የእኩልነትና የኢኮኖሚ አስተዳደር ጥያቄዎችን አንስተው ተቃውአቸውን አሰምተዋል፡፡ አንድ አራተኛው የኢትዮጵያ ...

Read More »

የወልቃይት ጠገዴና ፀለምት ተወላጆች በኒዉዚላንድ ኦክላንድ የጠሩት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኒዉዚላንድ ኦክላንድ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያዉያኖች አጋርነታቸዉንና ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም በሚለዉ የማንነት ጥያቄ ከወልቃይት ጠገዴና ፀለምት ሕዝብ ጋር መሆናቸዉንና ድጋፋቸዉን ለመስጠት ያላቸዉን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡ ስብሰባዉንም በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት አቶ አረፈዐይኔ መኮንን በአገር ዉስጥ የወልቃይት ጠገዴና ፀለምት የማንነት ሕዝብ ጥያቄ ሕገመንግስቱ በሚፈቅደዉ መሰረት የማንነታቸዉን ጥያቄ 50 ሺ የሚሆኑ አባወራ አስፈርመዉ ...

Read More »

6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ህጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ረሃብ አለማቀፍ ትኩረት እያገኘ ነው፡፡ ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የተመለከተ ዘገባ አቅርበዋል፡፡ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስትን ላለማስከፋት ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን ሁኔታው አስፈሪ መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ አሁን ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ሲመለከቱ፣ ስጋታቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀምረዋል፡፡ 6 ሚሊዮን ህጻናት ለከፋ ረሃብ መዳረጋቸውን የአለማቀፉ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበር ጥያቄ እንዳስነሳ የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ዘገበ

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነቶችንና አመለካከቶችን በተገቢው ሁኔታ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው በሃገሪቱ ተቃውሞ ኣየተባበሱ መምጣቱን የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ አርብ ዘገበ። በተለያዩ ክልሎች መጠኑን እያሰፋ የመጣው ይኸው ተቃዎሞ በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበርና በዴሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄዎች ላይ ጥያቄ አስነስቶ እንደሚገኝም ጋዜጣው አስነብቧል። በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ በትንሹ 266 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ያወሳው ጋዜጣው አስተዳደራዊ ጥያቄን ...

Read More »

በውጭ ብድር ላይ የተመሰረተው የልማት ፕሮጄክት ኢኮኖሚውን ሊያንኮታኩት ይችላል ተባለ

  ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ብድር ላይ ተመስርቶ እያካሄደ ያለው የልማት ፕሮጄክቶች የሃገሪቱ ኢኮኖሚን አደጋ ውስጥ መክተቱንና ሊንኮታኮት እንደሚችል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አሳሰቡ። መንግስት ከቻይና ብቻ ለመሰረተ-ልማቶች ማካሄጃ 17 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ መበደሩን ያስታወቁትና በለንደን ዩንቨርስቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ ገዳ ሃገሪቱ በአሳሳቢ የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውስጥ መሆኗን እንደገለፀ ዘ-ኢስት አፍሪካን መጽሄት ዘግቧል። ሃገሪቱ ለውጭ ንግድ ከምታቀርበው ...

Read More »