.የኢሳት አማርኛ ዜና

ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) በቅርቡ ተግባራዊ የተደርገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ማሳየቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ገለጹ። የአዋጁ መውጣት በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ስጋትን እንዳሳደረ የሚናገሩት እነዚሁ አካላት በተለይ ከአሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ ሃገራት ወደ ሃገር ቤት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ መቀነስ ማስመዝገቡን አስረድተዋል። በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲካሄድ የቆየው ...

Read More »

አልሸባብ ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የቲጌሎ ከተማ ማክሰኞ ተቆጣጠረ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የቲጌሎ ከተማ ማክሰኞ መቆጣጠሩ ተገለጸ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያዎችን መልሶ መያዝ የጀመረው ታጣቂ ሃይሉ በባኩል ግዛት የምትገኘውን የቲጌሎ ከተማ ለመቆጣጠር ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥና የአጥፍቶ መጥፋት ድርጊት መፈጸሙን መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ ትገኛለች የተባለችው የቲጌሎ ከተማ በቅርቡ ...

Read More »

በአሜሪካ ፊላዴልፊያ ግዛት የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) በአሜሪካ አገር በፊላዴልፊያና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሳለፍነው ቅዳሜ (November 12) ኢሳትን ለመደገፍ ያካሄዱት የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አስተባባሪዎች ገለጹ። በዚሁ የገቢ ማሰባሰቢያ ስርዓት ላይ የኢሳት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ገላው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እንዲሁም ኮሜዲያን ክበበው ገዳ የተገኙ ሲሆን፣ በወቅቱም ለጨረታ የቀረበው የአቶ በቀለ ገርባ እና የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ምስል ከ15 ሺ ዶላር ...

Read More »

በቢሮአቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ  የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩትና በቢሮአቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ በተፋጠነ ሁኔተ የቀብር ስርዓታቸው መፈጸሙ ተነገረ። የፓርላማ አባሏ በድንገት ሞተው ቢገኙም ምንም አይነት የአስከሬን ምርመራ ሳይደረግላቸው  ወደ ባህር ዳር ምሽቱን በመኪና ተወስደዋል። የፓርላማ አባሏ ጠንከር ያሉ አስተያየቶችን በመሰንዘር ይታወቁ እንደነበር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ ሲታወጅ ከአማራ ክልል ...

Read More »

በቡሩንዲ የዘር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም ይቻላል ሲሉ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት አሳሰቡ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) በቅርቡ በሃገሪቱ የተካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ ተከትሎ አለመረጋጋት ውስጥ በቆየችው ቡሩንዲ የዘር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም ይቻላል ሲሉ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት አሳሰቡ። በሃገሪቱ ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹት ድርጅቶቹ የአለመ አቀፍ ማህበረሰብ ችግሩን ለማስቀረት አስቸኳይ እርምጃን እንዲወስድ ጥሪ ማቅረባቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። መቀመጫውን በፈረንሳይ በተደረገው የሰብዓዊ መብቶች አለመ አቀፍ ፌዴሬሽን ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር አንድ የኮማንድፖስት አባል ሁለት ወጣቶችንና አንድ ፖሊስ ሲገድል  የወልቃይት ተወላጆችም እየታደኑ ነው ።

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገሪቱን እየመራ ያለው ወታደራዊ እዝ በእንግሊዝኛው ኮማንድ ፖስት በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጽማቸው ግድያዎችና አፈናዎች እየጨመሩ በመምጣት ላይ ናቸው። በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ በዳባት ከተማ ከአካባቢው አርሶአደሮች ተውጣጥቶ ጉጅሌ የሚል መጠሪያ የተሰጠው የኮማንድ ፖስት አባል የሆነው ንጋት ምስጋናው ሁለት የወገራ ደሲያ አካባቢ ተወላጆችን ከእስር ቤት በማውጣት በጥይት ደብድቦ የገደላቸው ሲሆን፣ የአካባቢው ተወላጅ የሆነው ...

Read More »

በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህርዳር ከተማ ተወካይ የነበሩት ወይዘሮ አዲሴ ዘለቀ አሟሟት አነጋጋሪ ሆኗል ።

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ  ሰፈነ ሰላም ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩትና የባህር ዳርን ህዝብ በመወከል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ አዲሴ ዘለቀ ባልታወቀ ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ማለትም ማክሰኞ ህዳር 6 /2009 ዓም. በጽ/ቤታቸው ሞተው ከተገኙ በሁዋላ ፣ ጉዳዩ የባህርዳርን ህዝብ እያነጋገረ ነው። ወ/ሮ አዲሴ በፓርላማው በቆዩበት ወቅት ጠንከር ...

Read More »

በስዊዲን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የርሃብ አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ገዥዎች በዜጎች ላይ የሚያደርሱትን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች በማውገዝ ከትናትና ማክሰኞ ረፋድ ላይ የጀመረው የርሃብ አድማ ለሁለተኛ  ቀንም ቀጥሏል። ከተለያየ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ኢትዮጵያዊያን አስቸጋሪው የአየር ንብረት ሁኔታ ሳይበግራቸው ለወገኖቻቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። በስዊድ ፓርላማ ፊትለፊት በመገኘት የስዊዲን መንግስት አንባገነኑን የህወሃት ኢህአዴግ የሚያደርገውን የገንዘብ እና ማንኛውንም ድጋፍ እንዲያቆም ሲሉ ጠይቀዋል። የድማው ተሳታፊ ...

Read More »

አልሸባብ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ የምትገኘውን የታይገሎ ከተማን በቁጥጥሩ ስር አዋለ

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በበቆል ክልል በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር አዋሳኝ ላይ የምትገኘውን የታይገሎ ከተማን በከፍተኛ ውጊያ አስለቅቆ አልሸባብ ድጋሜ በቁጥጥሩ ስር ማዋሉን ሸበሌ ሚዲያ ዘግቧል። ከቅርብ ወራት ወዲህ ሃይሉን እያጠናከረ የመጣው አልሸባብ ቀድሞ በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ስር የነበረችውን የታይገሎ ከተማን ለማስለቀቅ በመኪና ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት መታገዙን ሪፖርቶች አመላክተዋል። ማክሰኞ እለት በከተማዋ ...

Read More »

አንድ የካናዳ ፓርላማ አባል በኢትዮጵያ ላይ ግፊት እንዲደርግ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ እንደሚጀመሩ አስታወቁ

ኢሳት (ህዳር 6 ፥ 2009) የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊትን አጠናክሮ እንዲቀጥል አንድ ታዋቂ የሃገሪቱ የፓርላማ አባል ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ በቅርቡ እንደሚጀምሩ  ለኢሳት ገለጹ። አሌክስ ነታል የተባሉት እኚሁ የፓርላማ አባል ከተለያዩ አካላት ዘንድ የሚሰባሰበው የድጋፍ ፊርማ ለካናዳ መንግስት ቀርቦ የሃገሪቱ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እንደሚያግዝ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። የፓርማላ አባሉ ...

Read More »