በቡሩንዲ የዘር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም ይቻላል ሲሉ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት አሳሰቡ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009)

በቅርቡ በሃገሪቱ የተካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ ተከትሎ አለመረጋጋት ውስጥ በቆየችው ቡሩንዲ የዘር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም ይቻላል ሲሉ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት አሳሰቡ።

በሃገሪቱ ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹት ድርጅቶቹ የአለመ አቀፍ ማህበረሰብ ችግሩን ለማስቀረት አስቸኳይ እርምጃን እንዲወስድ ጥሪ ማቅረባቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

መቀመጫውን በፈረንሳይ በተደረገው የሰብዓዊ መብቶች አለመ አቀፍ ፌዴሬሽን የአፍሪካ ሃላፊ የሆኑት ፍሎረንት ጊል በብሩንዲ በየዕለቱ እየታየ ያለው ሁኔታ በሃገሪቱ የዝር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል ማሳያ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ፒየሬ ንኩሩንዚዛ ህገ-መንግስቱ ከምፈቅድላቸው ውጭ ለሶስተኛ ጊዜ በምርጫ ተወዳድረው ለድል መብቃታቸው በመቃወም በቡሩንዲ ፖለቲካዊ ውጥረው መቀስቀሱ ይታወሳል።

በቡሩንዲ ያለውን ውጥረት ምክንያት በማድረግ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ባለፉት ጥቂት ወራቶች ውስጥ የተገደሉ ሲሆን፣ በመዎዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች የገቡበት አለመታወቁን ኢቴካ የተሰኘ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አስታውቋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ የቡሩንዲ ዜጎች በተለያዩ እስር ቤቶች የስቃይ ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኝ የገለጹት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማቱ በሃገሪቱ አለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲሰማራ ጥሬን አቅርበዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪ አካላት በበኩላቸው በሃገሪቱ ባካሄዱት ጥናት የዘር ማጥፋት ድርጊት ሊፈጸም ይቻላል የሚል ስጋት መኖሩን ሲገልጹ ቆይተዋል።

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከተለያዩ አካላት እየቀረበ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ የራሱን ማጣራት ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።

ይሁንና በቡሩንዲ በቅርቡ ከፍርድ ቤቱ አባልነት ራሷን ማግለሏ በምርመራው ሂደት ላይ ተፅዕኖን ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል።

የብሩንዲ ባለስጣናት እየቀረበባቸው ያለን ቅሬታ ያሰባበሉ ሲሆን፣ በሃገሪቱ ለአንድ አመት ያህል ጊዜ የዝለቀው ፖለቲካዊ ውጥረት የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ማህብራዊ እንቅስቃሴ ክፉኛ መጎዳቱም ይነገራል።