.የኢሳት አማርኛ ዜና

ድንበር ተሻግረው የገቡ ሃይሎች 22 ኢትዮጵያውያንን ገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2011)በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር የተሻገረ የታጠቀ የውጭ ሃይል ጥቃት ከፍቶ 22 ኢትዮጵያውያንን ገደለ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የድንበር ከተማ ገሃንዳሌ ላይ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት 50 ሰዎች ቆስለዋል። ትላንት ጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ወረራ በፈጸመው የውጭ ሃይል ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የገሃንዳሌ ነዋሪዎች አካባቢውን ጥለው መሰደዳቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው ቢኖርም ዜጎችን ከጥቃት መከላከል እንዳልቻለ ግን ተገልጿል። እንደወትሮው የጎሳ ...

Read More »

በአሜሪካ ወህኒ ቤት የ8 አመቱ ታዳጊ ሕይወቱ አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) በአሜሪካ ወህኒ ቤት የ8 አመቱ ታዳጊ ስደተኛ ትላንት ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ። በፈረንጆቹ የገና በአል ሕይወቱ ያለፈው የ8 አመቱ ታዳጊ የጓቲማላው ተወላጅ ፍሊፕ ጎሜዝ በዚህ ወር በአሜሪካ ወህኒ ቤት ሕይወታቸው ያለፈውን ታዳጊዎች ቁጥር ወደ 2 ከፍ አድርጎታል። የታዳጊውን ሕልፈት ተከትሎ የአሜሪካ የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ አሰራሩን በመከለስ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አድርጓል። ሆስፒታል ቆይቶ ሲመለስ ህመሙ የተባባሰበት የ8 አመቱ ታዳጊ ...

Read More »

አመፅና የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን ያወድማል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ17/2011) አመፅና የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን ስለሚያወድም በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ አይደለም ሲል የአርበኞች ግንቦት 7 ገለጸ። የንቅናቄው ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅቱ ከአመፅ ነፃ በሆነ በሰላማዊ መንገድ መታገልን ብቻ የሚጠይቅ ነው ብለዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመፅ እና ትጥቅን መሰረት ያደረገ ትግል ኢትዮጵያን ወደ ውድመት ከመምራት በስተቀር ሌላ ጥቅም የለውም ሲል ማብራሪያ ሰጥቷል። ንቅናቄው ይሕንኑ በመረዳቱም ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአፍሪካ አህጉር ታሪክ የሰሩ ተባሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) እየተገባደድ ባለው 2018 በአፍሪካ አህጉር ታሪክን ከሰሩ ሰዎች የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግንባር ቀደም መሆናቸውን ቢቢሲ ዘገበ። ጋናዊቷ ጋዜጠኛ ኤልዛቤት ኦህኒ ዛሬ ቢቢሲ ላይ ባቀረበችው ዘገባ ዶክተር አብይ አህመድ ጸሃይን በምዕራብ የማውጣት ያህል አይቻልም የተባለውን በአጭር ጊዜ ከውነዋል በማለት ምስክርነቷን ሰጥታለች። በለየለት አምባገነን ስርዓት የምትተቻቸውንና ከኤርትራ ጋር በፍጹም ጠላትነት ውስጥ የቆየችውን ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሌላ ...

Read More »

በወልቃይት ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ የሚመስል ነገር ተሰርቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የማንነት ጥያቄን በሚመለከት የሰጡት መግለጫ በወለቃይት ህዝብ ላይ ጦርነት የማወጅ ያህል ነው ሲሉ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ለኢሳት ተናገሩ። ጥያቄያችን የረጅም ዓመታት ጥያቄ ነው ያሉት  ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ህጉን ተከትለን የማንነት ጥያቄያችንን ካቀረብን  ከሶስት ዓመታት በላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም ወይዘሮ ኬሪያ የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ ...

Read More »

ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን የተሳሳተ ዘገባ አረመ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011)የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ። የቢቢሲ አለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ ኢሳት ለጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ትናንት በላኩት ምላሽ ቢቢሲ ባለፈው ወር ባሰራጨው ዘጋባ ኢሳት ሆን ብሎ የዘር ግጭት የሚጭር ቪድዮ አዘጋጅቶ አሰራጭቷል በሚል በቢሲ ያቀረበው ዘገባ ያስተላለፈው መልዕክት ትክክል አለመሆኑን በመገንዘብ ማስተካከያ መደረጉን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል። በዚህም መሰረት በእንግሊዝኛ፣ ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011) የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፖለቲካ አላማቸው ሲሉ ሕዝብን ወደ ራሳቸው ፍላጎት ለማምጣት ሌሎችን በጠላትነት የሚፈርጁ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም ሲል ታዋቂው የትንተና መጽሔት ፎሪን ፖሊሲ ዘገበ። አንዳንድ በስም የጠቀሳቸው ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ሕዝበኛ ሲሉ ቢያነሷቸውም ዶክተር አብይ አሕመድ እንደ አሜሪካው ትራምፕም ሆነ እንደ ቱርኩ ኤርዶጋን ብራሳቸው ዙሪያ ሰዎችን ለማሰልፍ ተቀናቃኛቸውን በጠላትነት የሚፈርጁ ...

Read More »

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ከዓለማችን 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል ተቀመጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011) ከዓለማችን 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በ97ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጡ። የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርክል የአለማችን 1ኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴት ሆነው ሲመዘገቡ የብሪታኒያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ የአለማችን ሁለተኛዋ ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው ሲል ፎርብስ ዘግቧል። በቢዝነስና ፋይናንስ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ትኩረት የሚያደርገው ፎርብስ መጽሔት የ2018 ተጽዕኖ ፈጣሪ በማለት የ200 እንስቶችn ዝርዝር ይፋ ...

Read More »

በመቀሌ ነገ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011)በመቀሌ ነገ ቅዳሜ ለሁለተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደርግ መሆኑ ታወቀ። እየተካሄደ ያለው የለውጥ ሂደትና በወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ እየተወሰደ ያለው ርምጃ የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ነው በሚል ተቃውሞ ከአንድ ሳምንት በፊት በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የተካሄዱት ሰልፎች ተከታይ የሆነው የነገው ሰልፍ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎበት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የመቀሌውን ሰልፍ በቀጥታ እንዲያሰራጩለት ለተለያዩ የቴቪዥን ድርጅቶች የትብብር ...

Read More »

ከ600 በላይ የአማራ ተወላጆች ተፈናቀሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ600 በላይ የአማራ ተወላጆች ተፈናቅለው ባህርዳር መግባታቸው ተገለጸ። ከካማሼ ዞን ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉት የአማራ ተወላጆቹ በማንነታችን ላይ ያተኮረ ጥቃት እየተፈጸመብን ነው ብለዋል። ለሶስት ወራት በጫካ ውስጥ ተደብቀው ከቆዩ በኋላ ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ባህር ዳር መምጣታቸውን ነው ለአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የገለጹት። ተፈናቃዮቹ ባህርዳር ሜዳ ላይ ወድቀን ቀርተናል የአማራ ክልል መንግስት ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ...

Read More »