ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በአፍሪካ አስደንጋጭ ነው የተባለው የውጭ ዕዳ ክምችት ካለባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ሆና ተፈረጀች። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2015 አም የሃገሪቱ የዕዳ ክምችት ይፋ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ መጽሄት የሃገሪቱ የዕዳ ክምችት 22 ቢሊዮን አካባቢ እንደነበር በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት አስፍሯል። ይሁንና በተያዘው የፈረንጆች 2016 አም ይኸው የዕዳ ክምችት ወደ 36 ቢሊዮን ዶላር ኣካባቢ መድረሱ ሲገለጽ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ፍትሃተ ጸሎት በካናዳ ቤተክርስቲያን ተካሄደ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ጀግና አትሌት ሻንበል ምሩፅ ይፍጠር ፍትሃተ ጸሎት በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ተከናወነ። በዚህ ሳምንት አስከሬን ወደ ትውልደ ሃገሩ ኢትዮጵያ እንደሚሄድም ለማወቅ ተችሏል። ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ታህሳስ 13, 2009 ምሽት ካናዳ ቶሮንቶ ህይወቱ ያለፈው ታላቅ አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር በርካታ ኢትዮጵያውያን በታደሙበት እጅግ ደማቅና ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ማክሰኞ ታህሳስ 18 2009 ጸሎተ ፍትሃቱ የተካሄደ ሲሆን፣ ...
Read More »የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላት ላይ በአዲስ አበባ የተመሰረተው ክስ ለሁለተኛ ጊዜ ታየ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) በኮ/ል ደመቀ ዘውዱና በሌሎች የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላት ላይ በአዲስ አበባ የተመሰረተው ክስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ማክሰኞች እለት የታየ ቢሆንም፣ ኮ/ል ደመቀ አሁንም በጎንደር ወህኒ ቤት ይገኛሉ። አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አቶ አለነ ሻማ፣ አቶ ጌታቸው አደመ፣ እንዲሁም ነጋ ባንቲሁን፣ ማክሰኞ ታህሳስ 18, 2009 ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ተለዋጭ ቀጠሮ ለጥር 4 ፥ 2009 ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ እንዲደረግ ለትውልደ-ኢትዮጵያውያኑ ጥሪ ቀረበ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) በውጭ ሃገር ያሉ የኢትዮጵያ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ለ3 ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሃገር የመላክ ማዕቀብ ጥሪን አስተላለፉ። 17 የሚሆኑት የሲቪልና የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያውያን ለንግድም ይሁን ለቤተሰብ ድግማ የሚልኩት የውጭ ምንዛሪ እንዳይላክ ማድረግ በሃገሪቱ ያለውን አምባገነን አገዛዝ ለማድከም ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ መግለጫው አመልክተዋል። ድርጅቶቹ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪው መላካቸውን ለ3 ወራት ካቆሙ ...
Read More »በአፋር የሎጊያ ከተማ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ማክሰኞ በአፋር ክልል በሌጊያ ከተማ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከመማር ማስተማር ሂደት ችግና ከመልካም አስተዳዳር እጦትና ጋር በተያያዘ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ሰልፉን ተከትሎ ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽመዋል። ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ። አካባቢው በወታደሮችና በልዩ ሃይል አባላት እየተጠበቀ መሆኑን የደረሰን መረጃ ...
Read More »ኢህአዴግ “ገምግሞ ከስልጣን ያወረዳቸውን ባለስልጣናት” ወደ ትምህርት ሊልክ ነው
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በጥልቅ ትሃድሶ ስም በሙስና የተዘፈቁ ያላቸውን 479 የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች የወረዳ እና የቀበሌ ባለስልጣናት ወደ ትምህርት ሊላከቸው መሆኑን ምንጮች ገለጹ። “ኢህአዴግ ህዝብን ያስቸገሩ እና ያመረሩ ፣ የመልካም አሰተዳደር ችግር ያለባቸው እና ስርአቱን አደጋ ውስጥ የጣሉ ናቸው” በሚል ከአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች የተለዩትን ባለስልጣናት ማባረሩ “አመራሮቹ ወደ ተቃዋሚዎች ገብተው ለስርዓቱ ...
Read More »በለገዳዴና ለገጣፎ አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታሰሩ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ትናንት ሰኞ ከምሽት ጀምሮ ወታደሮች በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ለገጣፎ፣ ለገዳዲ እና ሌሎችም አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በእሬቻ በአል ወቅት ወረቀት ሲበትኑ የነበሩትን አጋልጡ እየተባሉ የአካባቢው ሰዎች ስቃይ ሲደርስባቸው ቆይቷል። በእስር ላይ የነበሩ 10 ሺ ወጣቶች መለቀቃቸው እንደተነገረ የተጀመረው የእስር ዘመቻ፣ ትናንት ምሽት ተጠናክሮ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ በጽኑ ታሞ ባቱ ሆስፒታል ገባ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታህሳስ18 ቀን 2009 ዓ.ም በፀና ታሞ በአንፑላንስ ተጭኖ ዝዋይ በሚገኘው ባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል። በተደጋጋሚ ጊዜያት ከቤተሰቦቹ እና ሕጋዊ ጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ሲደረግ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት በሚገቡበት ወቅት በአቅራቢያው የሚገኙትን ...
Read More »በጎንደር በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 15 ሰዎችን ጭኖ ከጎንደር ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪ ጠዳ ከተማ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ 10 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 4 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ሲኖ ትራክ እየተባለ በሚጠራ የጭነት ተሽከርካሪ ተመትቶ ሳይገለበጥ እንዳልቀረ ወኪላችን ገልጿል። አብዛኞቹ ሟቾች ነገ የሚከበረውን ወንቅሸት ገብርኤል ለማክበር በመጓዝ ...
Read More »የቱርክ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ባለንብረቶች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የባንክ ብድርና የታክስ ክፍያ ሳይከፍሉ ከሃገር መኮብለላቸው ተሰማ
ኢሳት (ታህሳስ 18 ፥ 2009) ሁለት የቱርክ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ባለንብረቶች ከመንግስት የወሰዱትን ወደ አንድ ቢሊዮን ብር የባንክ ብድርና የታክስ ክፍያ ሳይከፍሉ ከሃገር መኮብለላቸው ተሰማ። ለሁለት የቱርክ ባለሃብቶች ብድር ሰጥቶ የነበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ግለሰቦቹ ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ ጥያቄውን ለኢሚግሬሽን ቢሮ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ጥያቄው በቶሎ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት ባለሃብቶች ወደ ሃገራቸው ቱርክ መሄዳቸው ታውቋል። ሳይፈቲን እና ኢማም አልቲንባ የተሰኙት ሁለት የቱርክ ...
Read More »