መጋቢት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ ሱዳን መንግስት በቅርቡ የሙርሌ ጎሳ አባላት በጋምቤላ ክልል ጥቃት መፈጸማቸውን ቢያምንም፣ ተወሰዱ ስለተባሉ ህጻናትና ተገደሉ ስለተባሉ ሰዎች ማረጋገጫ አልሰጠም። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወደ ጁባ በማምራት ከመንግስት ጋር መነጋገራቸውን የገለጸው ራዲዩ ታማዙጂ፣ የቦማ ግዛት አስተዳዳሪዎች ጋምቤላ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ለጁባ መንግስት ቢያስታውቁም አሃዙ ላይ ማረጋገጫ አልሰጡም። የደቡብ ሱዳን መንግስት በሙርሌ ጎሳ አባላት በኩል ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ የግብርና ዕድገት ወደ 2.5 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሲመዘገብ የቆየው ሰባት በመቶ የግብርና እድገት በሃገሪቱ ተከስቶ ባለው የድርቅ ምክንያት ወደ 2.5 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ አራት ክልሎች አዲስ ተከስቶ ባለው ድርቅ ዙሪያ ሃሙስ ለፓርላማ ሪፖርትን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ድርቁ በግብርና እድገቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አብራርተዋል። በአፋር ኦሮሚያ፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ከወራት በፊት በአዲስ መልክ ...
Read More »ኢትዮጵያ ለተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ፈቃድ እንድትሰጥ ጥያቄ ቀረበ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ተደርጎ በሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ተደርጓል ያለውን ማሻሻያ ተከትሎ ሃገሪቱ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ፈቃድ እንድትሰጥ ተጠየቀ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የአዋጁ መውጣትን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ተፈጽሟል ባለው ግድያና የጅምላ እስራት ላይ ምርመራ ለማካሄድ ጥያቄን አቅርቦ እንደነበር አውስቷል። ለአዋጁ ...
Read More »የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ የአገሪቱ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳሰበ
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ጉብኘትን እያደረጉ ያሉት የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በሃገሪቱ ቆይታቸው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ የብሪታኒያ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳሰበ። ሪፕሪቭ የተሰኘውና የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ የሚከታተለው ድርጅቱ, ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባለፈው አመት ስልጣን በተረከቡ ጊዜ ለሃገሪቱ ዜጎች መብት መከበር የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ የቦሪስ ጆንሰንን የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣው ...
Read More »በጋምቤላ የደረሰን ጥቃት ተከትሎ ኢትዮጵያ አንድ የልዑክ ቡድን ወደ ደቡብ ሱዳን ላከች
ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) ሰሞኑን በደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ኢትዮጵያ የልዑኩ ቡድን ወደ ደቡብ ሱዳን መላኳን የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ አስታወቀ። የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ማዊን ሚሎል የሃገሪቱ የቦማ ግዛት የብሄራዊ መንግስቱ ታጣቂዎቹ ወደ ጋምቤላ ክልል ሰርገው በመግባት በሰዎች ላይ ግድያና አፈና መፈጸማቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ይህም ሆኖ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ “ቆሼ” አካባቢ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 200 ሊደርስ ይችላል ተባለ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 200 አካባቢ ሊደርስ እንደሚችል ነዋሪዎች አስታወቁ። ለአምስተኛ ቀን በተካሄደ ቁፋሮ የሟቾች ቁጥር 115 የደርሰ ሲሆን፣ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች በበኩላቸው 80 ነዋሪዎች አሁንም ድረስ የገቡበት አለመታወቁን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል። አስከሬን የማፈላለግ ስፍራው ተጓትቷል ሲሉ ቅሬታቸውን ሲገልጹ የቆዩ ነዋሪዎች መንግስት ...
Read More »በአዲስ አበባ የተከሰተውን አደጋ አስመልክቶ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች የሃዘን መግለጫ አወጡ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ላይ በደረሰው አደጋ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫ በማውጣት ሃዘናቸውን ገለጹ። በውጭ አገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በምክትል ዋና ጸሃፊው በአቡኑ ሚካዔል ስም ባወጣው መግለጫ፣ ለሞቱን ሃዘኑን ገልጾ፣ ለቤተሰብ መጽናናንትን ተመኝቷል። ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሞቱትን በጸሎት እንዲያስቡና ለሟች ቤተሰቦች ደግሞ ድጋፍን እንድያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ የአፋር ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንዲቀጥል ተወሰነ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንዲቀጥል ተወሰነ። የጸጥታ ሃይሎች ያለ-ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በጠረጠሯቸው መኖሪያ ቤቶች ላይ ሲያካሄዱ የቆዩት ፍተሻና ብርበራ በአዲሱ ማሻሻያ መነሳቱን ሮይተርስ የመንግስት ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። ህጉ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን አካትቶ አንዲቀጥል ቢወሰንም ለአዋጁ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አልተገለጸም። አመጽ ያነሳሳሉ የተባሉ የተለያዩ ጽሁፎችንና መልዕክቶችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት ...
Read More »ለልማት ተነሺዎች ተመድቦ የነበረው 100 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅም መዋሉን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ለልማት ተነሺዎች መድቦት የነበረው 100 ሚሊዮን ብር በአመራሮችና በጎሳ መሪዎች ለግል ጥቅም ውሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሃሙስ ለፓርላማ አባላት ገለጹ። በሃገሪቱ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለፓርላማው የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስሙን መጥቀስ ባልፈለጉት ክልል 100 ሚሊዮን ብር ለተነሺዎች እንዲደርስ ቢመደብም ለግል ጥቅም ውሏል ሲሉ አስታውቀዋል። አቶ ...
Read More »በጋምቤላ ክልል በሙርሌ ታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ድንበርን ዘልቀው በጋምቤላ ክልል ጥቃት የፈጸሙ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የገደሏቸው ሰዎች ቁጥር 28 ደረሰ። ወደ 1ሺ አካባቢ የሚጠጉ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በክልሉ ጎግ እና ጆር ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናቶች በፈጸሙት በዚሁ ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ህጻናት ቁጥርም 43 መሆኑን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ጋዜጣ የክልሉ ቃል አቀባይ ቶል ቻኒን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በአካባቢው በተፈጸመው ...
Read More »