ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሌራ ወረረሽኝ በኢትዮጵያ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱንና በበሽታውም 780 ኢትዮጵያዊያንን መግደሉን ወርልድ ቪዥን በጥናታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል። ከሚያዝያ አጋማሽ እስከ ግንቦት አጋማሽ 2017 እ.ኤ.አ. በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረሽኝ አድማሱን እያሰፋ ነው። በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሊያ ክልሎች በአጠቃላይ 567 የነበረው የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር፣ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
39 የአውሮፓ የፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲደረግበት ጠየቁ
ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ሲሉ፣ 39 የአውሮፓ ፓርላማ አባላት በፊርማቸው ለህብረቱ ፓርላማ ጥሪ አቅርበዋል። በገዥው ፓርቲ የሚመራው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ያወጣው የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ግልጽነት እና ተአማኒነት የጎደለው ነው ሲሉ የፓርላማ አባላቱ ተችተዋል። የፓርላማ አባላቱ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሞ ...
Read More »በኢትዮጵያው የካንሰር ህሙማን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና – ሐምሌ 4/2009) እንደ አለማቀፉ የጤና ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2012 ጥናት ከሆነ ወደ 61 ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በካንሰር ህመም ተይዘዋል። እንደ ጥናቱ ከሆነ ኢትዮጵያውያኑ የተጠቁበት የካንሰር አይነት ደግሞ በህክምናው አለም በቀላሉ መከላከል የማይቻልና በፍጥነት የሚባዛ መሆኑን አመልከቷል። ምናልባትም ችግሩን የከፋ እንዲሆን ያደረገው አንድ መቶ የሚሆን የተለያየ ባህሪ ያላቸው የካንሰር ሴሎችን የያዘ መሆኑ ነው ብሏል ጥናቱ። በኢትዮጵያ የቤተሰብ መምሪያ ስፔሻላይዝድ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የነጻነት በአል አይከበርም አሉ
(ኢሳት ዜና – ሀምሌ 3/2009) ደቡብ ሱዳን ስድስተኛውን የነጻነት ቀንን በፌሽታና በፈንጠዝያ እንደማታከብር የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አስታወቁ። ሳልቫኪር እንዳሉት ሀገሪቱ ከገጠማት ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ጋር በተያያዘ በአሉን በአደባባይ ከፍተኛ ወጭ አውጥታ ላለማክበር ወስናልች። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት በሀገሪቱ እየተባባሰ ለመጣው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ተደርጎ ተቀምጧል። ከዚህ ጋር በተተያያዘም ይላሉ ሳልቫኪር የሀገሪቱ ዜጎችን ...
Read More »በምስራቅ ኣፍሪካ 27 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልፈዋል ተባለ
(ኢሳት ዜና – ሀምሌ 3/20009) የተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ድርጅት በምስራቅ ኣፍሪካ ከተከሰተው ከባድ ድርቅ ጋር ተያይዞ 27 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ኣስታውቀ። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በኣፍሪካ ቀንድ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስደተኛ ዚጎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን በላይ ኣሻቅቧል። ከምስራቅ ኣፍሪካ ብቻ ባለፉት ስምንት ወራት 3 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጝች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሪፖርቱ ...
Read More »ቴዎድሮስ ካሳሁን ኮንሰርት ለማዘጋጀት የመንግስትን ፈቃድ እየጠበቀ ነው
( ኢሳት ዜና – ሃምሌ 3 , 2009 ) ታውቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሚሊንየም አዳራሽ በአዲስ አመት ኮንሰርት ለማሳየት ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ፈቃድ ማስታውቂያ ክፍል ጥያቄ ቢያቀርብም ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግረን ምላሽ እንሰጥሃለን መባሉ ተዘገበ ። ቴዎድሮስ ካሳሁን ጷጉሜ 5 , 2009 አ.ም ለአዲስ አመት ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ ውል መዋዋሉን የድምጻዊው ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ገልጸዋል ። ኮንሰርቱን ...
Read More »በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታቱ ሙከራ አሁንም አልተሳካም
( ኢሳት ዜና -ሃምሌ 3 , 2009 ) በአማራ ክልል አርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት ከሚሊሻ ሃላፊዎችና ከፖሊስ ጋር በተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ዘመቻ ቢጠናከርም አሁንም አለመሳሳቱ ተነገረ ። በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ / ህውሃት / የሚመራው ወታደራዊ እዝ / ኮማንድ ፖስት / በመሳሪያ ምዝገባና በግብር ስም የጠራው ስብሰባ መጨናገፉም ተገልጿል ። በጎጃምና በጎንደር ድንገተኛ የቤት ለቤት ፍተሻ እየተካሄደ መሆኑንም የኢሳት ምንጮች ...
Read More »የአማራና ኦሮምያ ክለብ ደጋፊዎች ህውሃትን ኣወገዙ
(ኢሳት ዜና – ሃምሌ 3 , 2009 ) የኦሮምያና የአማራ እግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች በባህርዳር ስታዲየም የጋራ ትብብር ባማሳየት የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ ህውሃት / አገዛዝን አወገዙ ። የባህርዳር ከተማ ክለብና የኦሮምያ ለገጣፎ እንዲሁም የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት / አውስኮድ / ከሱሉልታ ጋር ሲጫወቱ የየክለቦቹ ደጋፊዎች በወዳጅነት መንፈስ በጋራ ሲጨፍሩ ታይተዋል:: በውድድሩ በባህርዳር ከተማና ለገጣፎ ተጫውተው 0 ለ ...
Read More »ህዝባዊ አመጹ ሊደገም ይችላል የሚል ስጋት አለ
ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር እና ጎንደር ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴው ይጀመራል የሚል ስጋት መኖሩን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች በሸማቾች ተጣበው ታይተዋል። ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከው መረጃ በቅርብ ቀናት አገዛዙ በወልቃይት ዙሪያ ለአመታት ምላሽ ሳይሰጥ የንፁሐንን ደም አፈስሶ በዜጎች ቤት ሀዘን ካስቀመጠ አመታት ሊደፍን ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ፣ አገዛዙ ላይ አጣነው ባሉት ...
Read More »በትግራይ ድንበር የሚገኙ አርሶ አደሮች የባቡር መሬት ካሳ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ፡፡
ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጅቡቲ ወደ መቀሌ በሚዘረጋው የባቡር መስመር እርሻ ቦታቸውን የተነጠቁ አርሶ አደሮች “ተገቢውን የመሬት ካሳ እንከፍላችኋለን” ቢባሉም ለሶስት አመታት ምንም ዓይነት የካሳ ክፍያ ባለማግኘታቸው ከነቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለጹ፡፡ በአማራ ክልል ቆቦ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች በተለይ ለሪፖርተራችን እንደገለጹት፤ከመቀሌ እስከ ትግራይ ድንበር ድረስ ለሚገኘው አካባቢ ደረቅ መሬት በማለት የመሬት ካሳ ...
Read More »