.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንደገና ባገረሸው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ንጹሃን ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይም ርምጃ መወሰዱ ታውቋል። በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ እንደገና ግጭት ማገርሸቱን መንግስት በሳምንቱ መጨረሻ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዲስ ባገረሸው ግጭት ባለፈው ሳምንት ብቻ 20 ሰዎች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ቃል ...

Read More »

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከህወሃት ስራ አስፈጻሚ አባልነት ታገዱ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)ከሁለት ወራት በላይ የዘለቀው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤትን ወይዘሮ አዜብ መስፍንን አገደ። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፓርቲውን ሊቀመንበርና ሌላ አንድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝቅ ማድረጉን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን አስታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊቀመንበርነትን ላለፉት አምስት አመታት የያዙት አቶ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን አስወግደው በጋራ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩና በተለያዩ ማህበረሰቦች የተደራጁ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን አስወግደው በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በጋራ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ። በዚህም በግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመታደግ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ በጋራ ያስተባበሩትና ለተፈናቃዮች መደገፊያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት ነገ በሴንትፖል ሚኒሶታ እንደሚካሄድ ታውቋል። በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩትና በተለያዩ ማህበረሰቦች ተደራጅተውና ሳይደራጁ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በአንድነት ለመንቀሳቀስ ...

Read More »

ሮበርት ሙጋቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ መድረክ ላይ ታዩ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)ሮበርት ሙጋቤ ከሁለት ቀናት የቁም እስር ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ መድረክ ላይ መታየታቸው ታወቀ። ስልጣኑን ለጊዜው የተቆጣጠረው ወታደራዊ ሃይል ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው በሰላማዊ መንገድ እንዲለቁ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁም ታውቋል። ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ለነገ ተዘጋጅቷል። የስልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ አንድ አመት የቀራቸው ዶክተር ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ የመሪነቱን ስፍራ ለባለቤታቸው ለማመቻቸት ምክትላቸውን ከወር በፊት ከስልጣን ማባረራቸው ...

Read More »

አዘዞ በሚገኘው የ24ኛው ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ተፈጸመ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010) ጎንደር አጠገብ አዘዞ በሚገኘው የ24ኛው ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አስታወቀ። ዛሬ ንጋት ላይ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት የካምፑ የተወሰኑ ቤቶች በቃጠሎ መውደማቸውን ንቅናቄው አስታውቋል። በተያያዘ ዜና ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ከባድ ተሽከርካሪ /ቦቴ/ ላይ በተወሰደ ርምጃ ተሽከርካሪው ከጫነው ነዳጅ ጋር መውደሙን አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ገልጿል። የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ...

Read More »

የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ ችግሮችን እንዳባባሰ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010) የትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተከሰቱ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ችግሮቹን እንዳባባሰ ተገለጸ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የችግሮቹ ዋነኛ ምንጭ ትንሽ የሚባሉ ተማሪዎች ናቸው ሲል የሰጠው ሰበባዊ መግለጫ ለችግሩ መባባስ በምክንያትነት ተቀምጧል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌጤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያጋጠሙ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ በተቋማቱ የተፈጠረው ችግር በ20ና 30 ተማሪዎች ማሳበባቸው ችግሩን እንዳባባሰው ነው ለኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ...

Read More »

በባህር ዳር የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)ከባህርዳር ከነማ ጋር ውድድሩን ሊያካሂድ ባህርዳር የገባው የአክሱም ከነማ እግር ኳስ ቡድን ያረፈበት ሆቴል ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ውጥረት መንገሱ ተሰማ። ማምሻውን የልዩ ሀይል ፖሊሶች ተጫዋቾቹን ከሆቴሉ ለማስወጣት እየሞከሩ መሆናቸው ታውቋል። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ነገ ይካሄዳል ተብሎ ስለሚጠበቀው ጨዋታ ግን የተባለ ነገር የለም። በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ /ባቱ/ ከተማ በግለሰቦች መካከል ተቀስቅሷል የተባለ ጸብ ወደ ሌሎች ...

Read More »

በሻኪሶ ዛሬ ከባድ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)በሻኪሶ ዛሬ ከባድ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ለተቃውሞ የወጡት ሜድሮክ ኢትዮጵያ በአካባቢው የሚያከናውነውን የወርቅ ማውጣት ስራ ለተጨማሪ 10 አመት እንዲታደስለት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የሰልፈኞቹ ለተቃውሞ መውጣት ምክንያቱ ይህ ነው ይባል እንጂ ዋነኛ ጥያቄያቸው ግን የወያኔ ስርአት ይብቃን የሚል ነው። ሜድሮክ ኢትዮጵያ በሻኪሶ የወርቅ ማዕድን ለማውጣት ከህወሃት መንግስት ጋር የተፈራርመው የ20 አመት ውል ...

Read More »

የሕወሃት አመራር የጸረ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ አለበት ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010) የሕወሃት አመራር የጸረ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ያለበትና ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጋርም ያለው ግንኙነት ችግር ያለበት መሆኑን የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ገለጸ። በውዝግብና በቀውስ ውስጥ የቀጠለው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ሳያጠናቅቅ ሁለተኛውን መግለጫ አውጥቷል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በመካከላቸው ግለሂስ በማካሄድ ላይ ናቸው። በኢትዮጵያ የዘር መድሎ አገዛዝ እያራመደ ያለው ሕወሃት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ በግምገማና በግለሂስ ላይ ይገኛሉ። መስከረም 22/2010 የጀመረውና ...

Read More »

የዚምባቡዌ ወታደራዊ አዛዦች ከሚኒስትሮችና ከሮበርት ሙጋቤ ጋር በድርድር ላይ ናቸው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር7/2010)በዚምባቡዌ የሀገሪቱን ስልጣን የተቆጣጠሩት ወታደራዊ አዛዦች ከሚኒስትሮችና በቁም እስር ላይ ከሚገኙት ሮበርት ሙጋቤ ጋር በድርድር ላይ መሆናቸው ታወቀ። ድርድሩን በዋናነት የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ሳድክ እየመራው መሆኑ ታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት በበኩሉ የወታደራዊው ሃይል ስልጣኑን በሃይል መቆጣጠሩን እንደማይቀበለው አስታውቋል። በዚምባቡዌ ወታደራዊ አዛዦች የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ዛሬ ወታደራዊ አዛዦቹ ከሚኒስትሮች እንዲሁም በቁም እስር ላይ ከሚገኙትና ሀገሪቱን ለ37 አመታት ከመሩት ...

Read More »