(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በሰሜን ሸዋ አጣዬ የሰላም ባስ አውቶብስ በህዝብ ተቃውሞ እንዳይንቀሳቀስ ተደረገ። ከትላንት በስቲያ የሆነው ዛሬም ድረስ አልበረደም። የአጣዬን ከተማ መሃል ለመሃል የሚከፍለው ድልድይ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ሰፍቶ በፌደራል ፖሊስና በታጠቁ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደተካሄደ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። መነሻው ድልድዩን ሊያቋርጥ የተቃረበን የሰላም ባስ አውቶብስን ነዋሪው በማስቆሙ ነው። ምክንያቱ ደግሞ የህዝብ ሀብት ተዘርፎ የተመሰረተው የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በትራምፕና በቤተሰቦቻቸው ዙሪያ የተፈጸሙ የተለያዩ ቅሌቶችን አንድ መጽሀፍ አጋለጠ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በአንድ ጋዜጠኛ ተጽፎ በቅርቡ ለገበያ የሚቀርበው መጽሀፍ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና በቤተሰቦቻቸው ዙሪያ የተፈጸሙ የተለያዩ ቅሌቶችን አጋለጠ። መጽሀፉ የተለያዩ ሚስጥሮችን ማጋለጡ ቀድሞውንም በቀውስ የተሞላውን ኋይት ሀውስ የበለጠ ነዳጅ ቸልሶበታል። መጽሀፉ ዋና መነጋገሪያ ከሆነባቸው ጉዳዮች አንዱ የቀድሞው የኋይት ሀውስ ዋና ዕቅድ ነዳፊ ስቲቭ ባነን በሰኔ ወር 2016 በትራምፕ ልጅና በሩሲያ መንግስት ሰዎች መካከል በትራምፕ ህንጻ ውስጥ የተደረገው ውይይት ...
Read More »ኢብራሂም ሻፊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ፣መምህርና የፖለቲካ ጉዳዮች ጸሐፊ ኢብራሂም ሻፊ በስደት በሚኖርባት ኬኒያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በሌላ በኩል አንጋፋው የህክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር ዕደማርያም ጸጋ ተሻለ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኢብሮ በአጭሩ የሚጠራበት ስሙ ነው። መምህር ሆኖ አገልግሏል። የስፖርት ጋዜጠኝነቱ በሰፊው ይነሳለታል። የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ትንተናዎችም ይታወቃል። በሰብዓዊ መብቶች መከበር ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግም አስተዋጽኦው የጎላ ...
Read More »አዲስ የጣራ ክዳን ፋብሪካ ሊገነባ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) የሕወሃት ንብረት የሆነው ኢፈርት ከሁለት ኩባንያዎች ጋር በፈጠረው የሶስትዮሽ ግንኙነት አዲስ የጣራ ክዳን ፋብሪካ 2 ቢሊየን በሚጠጋ ብር ሊገነባ ነው። የኢፈርት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አዜብ መስፍን ስምምነቱን ከሲንጋፖሩ ኩባንያ ኩስቶና ፈርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ከተባሉ ኩባንያዎች ጋር ተፈራርመዋል። ፋብሪካውን በመቀሌ ወይም አቤዲ በተባሉ የትግራይ አካባቢዎች ለመገንባት የቦታ መረጣ እየተካሄደ ይገኛል። በስምምነቱ መሰረት መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከሁለቱ ኩባንያዎች ጋር ...
Read More »በመንግስት የተሰጠው መግለጫ ሲሰረዝና ሲደለዝ ዋለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት የሚገኙ ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞች ለሀገራዊ መግባባት ሲባል እንዲፈቱ ተወስኗል በሚል በመንግስት የተሰጠው መግለጫ በመንግስት ሲሰረዝና ሲደለዝ መዋሉ ታወቀ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ገጽ ላይ ሰባት ጊዜ እየተሰረዘና እየታረመ መጻፉ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የመንግስት መግለጫን ተከትሎ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ሌሎች ወገኖች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰቆቃው ...
Read More »(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በአዲስ አበባ በሳህሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዳግም ግጭት ተቀሰቀ። በቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የድረሱልን የደወል ድምጽ በመሰማቱ በርካታ ምዕመናን በአካባቢው ተገኝተው የተቃውሞ ድምጽ ማሰማታቸው ታውቋል። ለተቃውሞው ምክንያት የሆነው የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ድብደባ ደርሶባቸው እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ተመልሰው ወደ መቅደስ እገባለሁ በማለታቸው ነው። ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት መከበቧም ተነግሯል። በሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ምዝበራ እየተፈጸመ ነው በመባሉ ...
Read More »የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤና አቶ በቀለ ገርባን ለማስገደል ትዕዛዝ ተላልፎ ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2010) በቂሊንጦ ወህኒ ቤት የሚገኙት የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እሳቸውንና አቶ በቀለ ገርባን ለማስገደል ትዕዛዝ ተላልፎ እንደነበር አስታወቁ። የቂሊንጦ እስርቤት የደህንነትና ጥበቃ ሃላፊ በነበሩት ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ ተላልፎ የነበረው ትዕዛዝ በእስር ቤቱ ፖሊሶች እምቢተኝነት ሳይሳካ መቅረቱንም አስታውቀዋል። ይሄ መረጃ የወጣው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ማስረሽ ሰጤ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሰዎች ...
Read More »የሕወሃቱን እጩ ለማስመረጥ አገዛዙ ጣልቃ እየገባ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2010) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትን ለመምረጥ ውድድር ይካሄዳል ቢባልም የሕወሃቱን እጩ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃናን ለማስመረጥ አገዛዙ ጣልቃ እየገባ መሆኑን ምንጮች ገለጹ። ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት 22 እጩዎች ለውድድር ከቀረቡ በኋላ ዘጠኙ ለሁለተኛ ዙር ማለፋቸውን ለማወቅ ተችሏል። በሕወሃት በኩል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ተመራጭ ሲሆኑ መልማይ ኮሚቴው በአገዛዙ በኩል ግፊት እየተደረገበት መሆኑ ተገልጿል። በኦሕዴድ በኩል ...
Read More »ተቃውሞዎች ሲደረጉ ዋሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2010)በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተቃውሞዎች ሲደረጉ መዋላቸው ተገለጸ። የኢህአዴግ መግለጫ ቅዳሜ ከወጣና ዛሬም የእስረኞች እንደሚፈቱ ከተገለጸ በኋላም የህዝብ ተቃውሞ የቀጠለ መሆኑ ታውቋል። በምዕራብ አርሲና በምዕራብ ሸዋ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ተሰምቷል። በአዳማ ጎሮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ታውቋል። በወለጋ አሰንዳቦም አገዛዙን በመቃወም ህዝቡ አደባባይ መውጣቱን መረጃዎች አመልክተዋል። ምዕራብ አርሲ ከሻሸመኔ ጀምሮ ያሉት አካባቢዎች ያለው ውጥረት ...
Read More »ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2010) በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞች እንዲፈቱ መወሰኑን ኢሕአዴግ አስታወቀ። የማዕከላዊ ምርመራ ወህኒ ቤትም ወደ ሙዚየምነት እንደሚቀየር ይፋ ሆኗል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እስረኞቹ መቼ እንደሚፈቱ እንዲሁም እነማን እንደሆኑ አልተገለጸም። በመንግስትና በፓርቲ መገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው አራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በጋራ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ መስማማታቸው ተመልክቷል። በዓቃቢ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ፣ የተፈረደባቸው የተለያዩ ...
Read More »