.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሰላም ባስና ዳሽን ቢራ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተጠራ አድማና ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሰላም ባስና ዳሽን ቢራ አስታወቁ። የቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ያነጋገራቸው የሁለቱ ድርጅቶች ሃላፊዎች እንዳሉት በአድማውና በጥቃቱ ምክንያት ከኪሳራ ባሻገር ህዝቡ በአገልግሎታችን እንዳይጠቀም ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጥሯል። ሰላም ባስ በአራት መስመሮች አገልግሎት ማቋረጡን ሲያሳውቅ ዳሽን ቢራ በተለይ በባህርዳር ከፍተኛ የተቀባይነት ቀውስ እንደገጠመው ገልጿል። ለቢቢሲ አማርኛ ቃለ መጠይቅ የሰጡት የሰላም ...

Read More »

በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተጎዱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በአምቦ ዩኒቨርስቲ በተነሳ ተቃውሞ ተማሪዎች መጎዳታቸው ታወቀ። ባለፈው እሁድ የገና በአል ላይ በምግብ አዳራሽ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ግጭት መፈጠሩ የታወቀ ሲሆን እስከትላንት ድረስም መቀጠሉ ታውቋል። በዩኒቨርስቲው የሰፈረው የአጋዚ ሰራዊት ተማሪዎች ላይ ክፈኛ ድብደባ መፈጸሙን ተከትሎ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ለትምህርት ሚኒስቴር የቅሬታ ደብዳቤ መላካቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የተወሰኑ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወተዋል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ትምህርት ሚኒስቴር ጥቃት የፈጸሙትን ...

Read More »

የፖለቲካ እስረኞች ከ15 እስከ 18 አመታት የእስር ጊዜ ተፈረደባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በኢትዮጵያ 33 የፖለቲካ እስረኞች ከ15 እስከ 18 አመታት የእስር ጊዜ ተፈረደባቸው። የፊደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ሚፍታህ ሼህ ስሩር የክስ መዝገብ  በግንቦት 7 የተከሰሱ 33 ግለሰቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል። ግለሰቦቹ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው በሽብርተኝነት ስም የተከሰሱ መሆናቸው ነው የተነገረው። በክስ መዝገቡ ከተካተቱት ተከሳሾች ቀሪዎቹ ክደው በመከራከራቸው የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ከሀገር ...

Read More »

እነ አቶ በቀለ ገርባ የ6 ወራት ተጨማሪ እስራት ተወሰነባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት የሆኑ ተከሳሾች ፍርድ ቤትን ደፍራችኋል በሚል የ6 ወራት ተጨማሪ የእስራት ቅጣት ተወሰነባቸው። ውሳኔው የተለለፈው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የራሱን ውሳኔ በመሻር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለምስክርነት አይቀርቡም ሲል ውሳኔ ማሳለፉን በመቃወማቸው ነው። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ከዚህ ቀደም በሰጠው ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ...

Read More »

ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤልን የወሲብ ቅሌት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) የሕወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤልን የወሲብ ቅሌት የሚያሳይ ማስረጃ ይፋ ሆነ። ዶክተር ደብረጺዮን በወሲብ ጉዳይ ላይ የኢሜልና የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚያጋልጥ መረጃ ተሰብሮ ወጥቷል። በወጣው መረጃ ላይ ዶክተር ደብረጺዮን ዘወትር የሚጎበኟቸውን የወሲብ ድረገጾች፣ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያደረጓቸውን ግንኙነቶችና ሌሎች ቅሌቶች ይፋ ሆነዋል። የትግራይ ክልልን እንዲመሩ ትላንት የተሰየሙት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የኤሌክትሮኒክስ መልዕክት ሳጥናቸው ተሰብሮ ይፋ የሆነው መረጃ የቴክኖሎጂ ...

Read More »

ሼህ መሃመድ አላሙዲን ከሆቴል ወደ ወህኒ ተሸጋገሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ባለጸጋ ሼህ መሃመድ አላሙዲንን ጨምሮ 60 ያህል እስረኞች ከሆቴል ወደ ወህኒ ቤት መሸጋገራቸው ይፋ ሆነ። የሳውዳረቢያ መንግስት በድርድር እንዲፈቱ የጣለባቸውን የገንዘብ መጠን ለመክፈል ያልፈቀዱት እስረኞች በወህኒ ሆነው የሙስና ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ተመልክቷል። ምግብን ሳይጨምር ለመኝታ ብቻ በቀን 800 ዶላር እየተከፈለላቸው በዘመናዊው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ውስጥ የነበሩት ልኡላንና ባለጸጎች አልሔር ወደ ተባለው ወህኒ ቤት የተዛወሩት ከሶስት ቀናት ...

Read More »

የጎንደር የውሃ ፕሮጀክት ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ሆነበት የተባለውና ሁለት ጊዜ የተመረቀው የጎንደር የውሃ ፕሮጀክት መቋረጡ ተገለጸ። የህዝብ ቁጣ ይቀሰቀሳል በሚል ጉዳዩ በሚስጢር መያዙም ታውቋል። በሌላ በኩል ጎንደርን ጨምሮ በአማራ ክልል በበርካታ ከተሞች የውሃና መብራት አገልግሎት መቋረጡ ታውቋል። ከውሃና መብራት ሌላ ዘይትና ስኳር ከገበያ በመጥፋታቸው ህዝቡ በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኝ በደረሰን መረጃ ላይ ተመልክቷል። የጎንደርን የውሃ ጥም ለአንዴና ለመጨረሻ ...

Read More »

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ደብዳቤ ተጻፈ  

  (ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) የአሜሪካው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማን በአሜሪካ በሚኖሩ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው የስለላ ተግባር እንዲቆም በማሳሰብ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ደብዳቤ መጻፋቸው ታወቀ። ኮንግረስማን ኮፍማን የህወሃት አገዛዝ በውጭ በሚኖሩ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገው የኢንተርኔት የስለላ ተግባር እየተጠናከረ በመምጣቱ አሜሪካ ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል። የኮሚፕውተር ቫይረስ በማሰራጨት የስለላ ተግባር ለመፈጸም በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ የሚያደርገውን የህወሃት አገዛዝ ተጠያቂ በማድረግ ...

Read More »

ኦብነግ የህወሃት ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር ባደረገው ውጊያ በርካታ ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታወቀ። የኦጋዴን የዜና ወኪል የኦብነግን አባል ጠቅሶ እንደዘገበው ውጊያው የተካሄድው ታህሳስ 30/2010 ነው። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው ውጊያ በመንግስት በኩል ማርጋገጫ ባይገኝም የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው ተመልክቷል። በጃሌሎ መንደር ተደረገ በተባለው በዚህ ውጊያ ከወታደሮቹ መገደልና መቁሰል በተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች፣ጥይቶችና የመገናኛ መሳሪያዎች መማረካቸው ተገልጿል። ...

Read More »

በደሴ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) በደሴ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተሰማ። ፒያሳ በሚባለው አካባቢ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የደረሰውን የቦምብ ጥቃት ተከትሎ የእስር ርምጃ በመወሰድ ላይ መሆኑም ታውቋል። በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የትግል ጥሪ ወረቀት ሲበተን አድሯል። በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች በተበተነው በዚሁ የትግል ጥሪ ህዝቡ የህወሃትን አገዛዝ ለማስወገድ እንዲነሳ ተጠይቋል። ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ የደረሰውን የቦምብ ጥቃት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ...

Read More »